#በኢትዮጵያ_ኮቪድ19_እየተባባሰ_ነው😷
የጤና ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተባባሰ መምጣቱን #ለቪኦኤ ተናገሩ።
ዶ/ር ተገኔ ሰው ‘አስገዳጅ መመሪያ ተነስቷል ፤ ኮሮና ቫይረስ የለም’ በሚሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እየተመራ እራሱን ለበሽታው እያጋለጠ መሆኑን ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ አስገዳጅ መመሪያውም አለመነሳቱን፣ የቫይረሱ ሥርጭትም እየተባባሰ መሆኑን ዶክተር ተገኔ አሳስበዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ለትግራይ ጊዜው ያለፈበት ዘይት እና ዱቄት ተልኳል ?
በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው መቐለ "ማይወይኒ" መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ከቀናት በፊት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የስንዴ ዱቄትና የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበት ቀን የታተመበት አጠራጣሪ ዘይት 'ቀይ መስቀል' አቅርቧል በሚል እንደማይጠቀሙ ገልፀው ነበር።
የቀይ መስቀል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን አሊ ፥ በመቐለም ሆነ በሌላ የትኛውም አካባቢ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት ምግብ እንደላቀርቡ እና እንደማያቀርቡ ገልፀዋል።
የጥርጣሬው መነሻ የሀገሪቱ ስንዴ አምራች ኩባንያዎች የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበትን ጊዜ ማሸጊያው ላይ የሚያትም ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ቀይ መስቀል ያቀረበው ስንዴ እና ዘይት የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት አይደለም ብለዋል።
ዶ/ር ሰለሞን #ለቪኦኤ ፦
"የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን በአ/አ እና መቐለ ባለው ተረጋግጧል። እነዚህ ምልክቶች በወረቀት ተለጥፈው ነው የሚሄዱት እነዚህ ምልክቶች የሚያሳስቱ መስሏቸው ስለተጠራጠሩ አንወስድም ፤ ይሄ ተለጥፎ ነው የመጣው፤ ቀኑም ልክ አይደልም ብለዋል።
የእኛ ሀገር ዱቄት ይሄን ሁሉ መንገድ አጓጉዘን፤ ዱቄቶቹ ከቃጫ የሚሰሩ ናቸው ከማሌዢያ ወይም ከፊሊፒንስ የሚመጡ አይደለም ፤ እነዚህን ሲያዩ አንዳንድ ተፈናቃይ ወገኖቻችን እነዚህን ነገሮች ተጠራጥረዋል።
መጠራጠራቸውን ትክክል ነው ፤ እነዚህ ነገሮች ይታዩ ፤ ይፈተሹ ተባለ ፤ ናሙናው ተወስዶ ታዩ ዱቄቱ በሙሉ ንፁህ ነው ፤ ለምግብነት መዋል ይችላል የሚል የፅሁፍ ማረገገጫ ነው ያገኘነው።
ዘይቶቹ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚያገለግሉ ዘይቶች ናቸው። ነገር ግን ምርመራ ሲደረግ የአዮዲን መጠናቸውን አነስተኛ ሆነው ነው የተገኘው"
ያንብቡ : telegra.ph/ERCS-05-05
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" የተላለፈውን ውሳኔ አትቀበልም፤ አታስፈፅምም፤ የትኛውንም አይነት ትብብር አታደርግም " - ኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዙሪያ ያካሄደውን ልዩ ስብሰባና በምክር ቤቱ የጸደቀውን የውሳኔ ሀሳብ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው፥ ኢትዮጵያ ም/ ቤቱ አንዳንድ አገራት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያና መጠቀሚያ መሆኑ እጅጉን እንዳሳዘናት ገልጿል። …
" በህግ ደረጃ ኢትዮጵያ እስካልተስማማች ድረስ ወደ ሀገር የመግባት መብት የላቸውም " - ዶ/ር አደም ካሴ
የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በ08/04/2014 ዓ/ም በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈውን ውሳኔ (ዓለም አቀፍ የመርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ) ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ፤ እንደማታስፈፅም፤ የትኛውም አይነት ትብብር እንደማታደርግ ማሳወቋ ይታወሳል።
የተመርማሪ ሀገር ፍቃድ በሌለበት የመርማሪ ቡድኑ ዕጣ ምን ሊሆን ይችላል ? ኢትዮጵያ ተገዳ መርማሪዎችን የምታስገናግድበት አሰራር ወይም ዓለም አቀፍ ህግ አለ ?
በዚህ ጉዳይ #ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር አደም ካሴ (በተለይ በአፍሪካ የህግ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ) ተከታዩን ብለዋል ፦
" በዓለም አቀፍ ህግ ይሄን ኮሚሽን በሚመለከት አንድ ሀገር ውስጥ ሊገባ የሚችለው / በሀገሪቱ ገብቶ ሊመረምር የሚችለው በሀገሪቱ ፍቃድ ከተሰጠው ብቻ ነው።
ኢትዮጵያን ሊያስገድዳት የሚችል ስርዓት የለም። ምንም እንኳን የህግ ስርዓት ባይኖርም በፖለቲካ ደረጃ ጫና ሊያመጣ የሚችል ፤ ምን የምትደብቁት ነገር አለ ? እየተባለ ፖለቲካዊ ጫናዎችን ሊያመጣብን ይችላል።
በህግ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት እስካልተስማማ ድረስ ወደ ሀገር የመግባት መብት የላቸውም።
ሌላው ጉዳይ በአጠቃላይ በዓለም ደረጃ ከውሳኔ ሰጪ አካላት በተጨማሪ እነዙህ ውሳኔ አካላትን እየተጠቀሙ አንዳንድ ሀገራት እነሱ የሚደግፉትን አቋም ለማራመድ ይጠቀሙበታል።
በተለይ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ኢትዮጵያ ይሄን ቡድን የማታስገባ ከሆነ አንዳንድ ጫናዎች ለማስረግ ለምሳሌ ማዕቀቦችን ለመጫን እና ግፉቶችን ለማድረግ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
ኢትዮጵያ በህግ ደረጃ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የማስገባት ግዴታ ባይኖርባትም በተመድም ከዛም አልፎ ውሳኔውን የሚደግፉ ሀገራት ምዕራባውያን ሀገራትም ያንን ተጠቅመው ጫና ሊያደርጉ ይችላሉ።
ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ አይገቡም ማለት ምርመራውን ማድረግ አይችሉም ማለት አይደለም። ምርመራውን ማካሄድ ይችላሉ፤ ይቀጥላሉ በስልክም በሌላም መንገድ አካሂደው አለ የሚሉትን መረጃ ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ። "