TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JawarMohammed

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በቁጥር በርካታ ታጣቂ ተሰማርቶ እንደነበር በፌስቡክ ግፁ አሳውቋል። ይህን መረጃ ባሰራጨበት ወቅት አቶ ጃዋር ይኸ የታጠቀ ኋይል ከሕግ አግባብ ውጪ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ተቆጥቦ ወደኋላ እንዲመለስ በአጽንኦት እንጠይቀለን ሲልም መልዕክት አስተላልፏል። ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጨለማ ወደ መኖሪያ ግቢያችን ለጥቃት የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ኾነ ቡድን ላይ የጥበቃ አካሉ ሕጋዊ መብቱን ተጠቅሞ የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል ሲል አክሏል። ይኸን ከሕግ አግባብ ውጪ የሚደረግን እንቅስቃሴ ለመከላከል በሚደርሰው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ኋላፊነቱን የሚወስደው ያለምንም ተጨባጭ ምክንያት እና ማሳሰቢያ ኋይል ያሰማራው አካል መሆኑን ሕዝቡ እንዲያውቅልን እንጠይቃለን ሲል ነበር መልዕክት ያስተላለፈው።

ሁኔታው ለሊቱን ሙሉ መነጋገሪያ ነበር፥ ከደቂቃዎች በፊት በራሱ ገፅ ላይ ስልተፈጠረው ሁኔታ ተከታዩን ማብራሪያ አስፍሯል፦

"Around midnight two cars pulled up and told my security details to pack their stuff and leave the compound quitely without alerting me. The security asked them why they're asked to leave. They were told it's for training purposes. The security refused. Then they got a call from commander of VIP protection services who warned them to leave immediately..."

Read More👇
https://telegra.ph/JM-10-23

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#JawarMohammed #DW

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ እንደ ፖለቲከኛ እንዴት እንደሚወዳደር እስካሁን እንዳልወሰነ አስታወቀ። አቶ ጀዋር ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃለ ምልልስ የራሱን ፓርቲ መስርቶ ወይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መወዳደርን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቶ እንደሚወስን ተናግሯል። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።

@tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia
Audio
#JawarMohammed #ETHIOPIA

አቶ ጀዋር #የአሜሪካን ዜግነታቸውን ለመመለስ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊነታቸውን እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JAWARMOHAMMED #OFC

[በዋዜማ ሬድዮ]

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል።

የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት በፊት ገልጿል። ይሁንና የዜግነቱ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲን ተቀላቅሎ መታወቂያም ወስዷል።

ጉዳዩን በተመለከት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ድብዳቤ ፅፎ ማስረጃ የጠየቀ ሲሆን ፓርቲው በበኩሉ ጃዋር ማስረጃ እንዲያቀርብ በደብዳቤ አሳስቧል። የፓርቲው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ይህን መረጃ አረጋግጠዋል። “የኛ አባል ሲሆን ለምን ይህ ጥያቄ እንደተነሳ ባይገባኝም እኛ ደብዳቤ ፅፈንለታል” ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና።

እንዴት ለዜግነቱ ማረጋገጫ ሳያቀርብ በህግ ባልተፈቀደ መልኩ ጃዋር መሀመድ ፓርቲውን እንዲቀላቀልና መታወቂያ እንዲወስድ እንደተፈቀደለት ለተነሳላቸው ጥያቄ መረራ ጉዲና ሲመልሱ ” እኛ የምናውቀው ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው፣ የሀገሩን ቋንቋ ይናገራል፣ ፊቱም ኢትዮጵያዊ ይመስላል፤ መንግስትም ይህን ያውቃል” ሲሉ ቀልድ አዘል ምላሽ ስጥተዋል።

በጃዋር ዜግነት ላይ ከመንግስት የሚነሳው ጥያቄ ፖለቲካዊ ፍላጎትንም ያካተተ ሊሆን ይችላል ያሉት መረራ ጉዲና ጃዋር በቅርብ ዜግነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ እንደሚያደርጉና ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በጊዜው ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

[ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JAWARMOHAMMED #OFC [በዋዜማ ሬድዮ] የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል። የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት…
#JawarMohammed #Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የቀረበ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው። ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት የደብዳቤው ኮፒ ለአቶ ጃዋር መሃመድ ልኮለታል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የተናገሩት፦

"መንግስት ግቡና አግዙን ባለው መሰረት ወደሀገር ቤት የገባን፣ በፓርቲ አመራርነት ያልተቀመጠንና በምርጫ ገና ያልተወዳደረን አካል እንዲህ ማለቱ ግራ የሚያጋባ ነው። ስሙም፣ መልኩም ኢትዮጵያዊ ነው።"

ምንጭ፦ አል-ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JawarMohammed #Election2012 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የቀረበ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው። ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት የደብዳቤው ኮፒ ለአቶ ጃዋር መሃመድ ልኮለታል። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የተናገሩት፦ "መንግስት…
#Election2012 #JawarMohammed

"አቶ ጃዋር የኢትዮጵያ ዜጋ ሆነዋል" - ጠበቃ ገመቹ ጉተማ

በታኅሳስ ወር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን [ኦፌኮ] መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ጃዋር መሐመድ ረቡዕ ጥር 13/2012 ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።

የጃዋር መሐመድ ጠበቃ የሆኑት ገመቹ ጉተማ፤ ጃዋር በዜግነት አዋጁ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን እና በዚህም መሰረት ለሚመለከተው አካል ማስገባታቸውን ገልፀዋል። ‹‹በሕጉ መሰረት ዜግነትን መልሶ ለማግኘት የምንጠብቀው ምንም ዓይነት መልስ የለም። አስፈላጊ ሰነዶችን ግን አስገብተናል›› ሲሉ ተናግረዋል።

[አዲስ ማለዳ ጋዜጣ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#JawarMohammed

ትላንት አዲስ ስታንዳርድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ መረጃዎች የሚያሰራጭ ድረ ገፁ አቶ ጃዋር መሃመድ ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዜግነቱ እንዲመለስለት ያስገባባትን ሁለት ገፅ ማመልከቻ ይዞ ወጥቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot
#JawarMohammed #Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አባል የሆነው ጃዋር ሞሐመድ አሜሪካዊ ዜግነቱን እንደመለሰ የሚገልጹ ሰነዶችን በሙሉ ለኢምግሬሽን እንዳስገባ ትናንት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ ሌሎች የውጭ ዜግነት ያላቸው ፖለቲከኞች ጥያቄ እንዳልተነሳባቸው ጠቅሶ፣ ምርጫ ቦርድ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ እንዳሳዘነው አክሎ ገልጧል፡፡

More https://telegra.ph/JAWAR-02-13

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

ወደወለጋ፣ወደኢሉባቦር ኦፌኮ ድጋፍ የለውም፤መሪዎቹም [ጃዋርን ጨምሮ] ወደዛ ላይሄዱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች አሉ ተብለው 'ኬላ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የተጠየቁት አቶ ጃዋር መሃመድ የሰጡት ምላሽ፦

ምንሄደው ድጋፍ ያለን ቦታ ብቻ አይደለም። ምንሄደው ድጋፍ ለማጠናከር ነው። እኛ በሁሉም ወረዳ ላይ ህዝባችንን ማነጋገር እንፈልጋለን። ግን ሰዉ ይረሳል እንጂ በጣም ነገሮች በተጧጧፉበት እና መንግስት በጣም በተዳከመበት፣ በሌለበት ወቅት እኔና በቀለ እስከ አሶሳ ድረስ ሰው ማንም በማይሄድበት፣ የመንግስት ባለስልጣን ሀገር ጥሎ በጠፋበት ወቅትም ስንሄድ ነበር። አሁንም ወደምዕራብ እንሄዳለን።

ምዕራብና ደቡብ እንደሚታወቀው ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ህጋዊ ያልሆነ ኮማንድ ፖስት አለ። ያ ኮማንድ ፖስት እንዲነሳ በህጉ challenge እናደርጋለን። እኛ ብቻ አይደለንም ጥምረት ፈጥረን እየሰራን ነው ያለነው ከኦነግ ጋር፣ ከኦብፓ ጋር አብረን ወደፊት የምናደርገው እንቅስቃሴ ይኖራል።

የማንሄድበት ዞን አይኖርም። ኦሮሚያ ውስጥ ብቻ አይደለም ወደ ተለያዩ ክልሎች የመሄድ እቅድ አለን። ደፍሮ ለሚለውም የተያያዝነው ትግል እንጂ ዳንስ አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ቦታ እንሄዳለን። ስንሄድ ደግሞ በተጨባጭ ይታያል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሃመድ 'ኬላ' በተሰኘ የአሃዱ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርበው 'ብዙ ኃይል ፖለቲካው ላይ እየባከነ ነው፤ የኢኮኖሚው ጉዳይ ተረስቷል' በሚል እይታቸውን እንዲያጋሩ ተጠይቀው ነበር። የኦፌኮ /KFO/ አባል የሆኑት አቶ ጃዋር ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ፀጥታ ፈፅሞ የማይነጣጠሉ ገዳዮች እንደሆኑ አስረግጠው ተናግረዋል። ቁጭ ተብሎ ፖለቲካውን ማስተካከል ከተቻለ የፀጥታው ሁኔታ ይስተካከላል፣ የፀጥታው ሁኔታ ሲስተካከልም ኢኮኖሚው ይስተካከላል ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia