#update የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው ወቅት አማራ ክልል ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀው በኦፕሬሽን እና በሕዝብ ትብብር 218 የሚሆኑ ‹‹የብርጋዲዬር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጥቃት ተባባሪዎች ናቸው›› የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ 113 ያህሉ በቀላል ደረጃ የተጠረጠሩ በመሆኑ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጣቸው የገለጹት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር አበረ አዳሙ ናቸው፡፡
ቀሪዎቹ 105 ተጠርጣሪዎች ግን ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የማጣራት ሥራው እየተከናወነ እንደሆነ ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት፡፡ ጉዳያቸውን በዋናነት ይዞ እያጣራ የሚገኘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
እንደ ኮሚሽነር አዳሙ መግለጫ በአርሶ አደሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር ሳይቀላቀሉ ለብቻ በማረፊያ ቤት ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቃቱ የተጓደሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ተናግረዋል፡፡ የሚሟሉት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ዝርዝር ጉዳይ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡
Via #አብመድ
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#NewsAlert የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት የነበረው ፈረቃ ከዛሬ ጀምሮ እንደማይኖር ታውቋል፡፡ በበጋና የበልግ ወቅቶች በቂ ዝናብ ባለመጣሉ የኢትዮጵያ የኤሌክተሪክ ኃይል ማመንጫ አንዳንድ ግድቦች የውኃ እጥረት አጋጥሟቸው እንደነበርና የኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011ዓ.ም በፈረቃ እንዲሆን መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ በተገኘው መረጃ መሠረትም ከዚህ በፊት በተሰጠው መግለጫ መሠረት ምንም እንኳ ግድቦች በቂ ውኃ ባይዙም በክረምቱ እንደሚሞሉ ታሳቢ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ፈረቃው እንዲቀር ተደርጓል፡፡
የኢፌዴሪ ውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ግንቦት 09 ቀን 2011ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ከግንቦት 01 ቀን ጀምሮ በውኃ እጥረት ምክንያት ወደ ፈረቃ መገባቱንና ፈረቃው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ሊቀጥል እንደሚችል ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ ከቀኑ 9፡00 ላይ ለመስጠት የመገናኛ ብዙኃንን ጠርቷል።
Via #AMMA/#አብመድ/
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም

ኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት የነበረው #ፈረቃ ከዛሬ ጀምሮ እንደማይኖር ታውቋል፡፡ #አብመድ #AMMA #ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአንድ ቦታ፣ በአንድ ጊዜ አራት የመኪና አደጋ ደረሰ!
በባሕር ዳር ዙሪያ በተከሰተ የመኪና አደጋ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የመኪና አደጋ ተከስቷል።
አደጋው የተከሰተው ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር እየሄደ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ሸዋ ሮቢት ቀበሌ ላይ ዛሬ 8፡20 አካባቢ በመጀመሪያ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው።
አውቶብሱ ከጎንደር አቅጣጫ እየመጣ ከነበረ ሲኖ ትራክ መኪና ጋርም ተጋጭቷል። አደጋው በዚህ አላበቃም፤ ከባሕር ዳር አቅጣጫ በፍጥነት እየተሽከረከረ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ፣ ተጋጭቶ ከቆመው ሲኖ ትራክ ጋር መጋጨቱም አራተኛ አደጋ ፈጥሯል።
በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዘጋቢያችን ተመልክቷል፤ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሰው ህይዎት እንዳላለፈም ነው ዘጋቢያችን መረጃ ያደረሰን።ተጎጅዎችም ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው። የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ከስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን ጥረት ብናደርግም አሁን መረጃ መስጠት የሚችሉበት ደረጃ ላይ አለመሆናቸውን አሳውቀውናል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የወልድያ-ቆቦ መንገድ በደለል ምክንያት መዘጋቱ ተገለፀ! ከወልዲያ ቆቦ የሚወስደው ዋና የአስፓልት መንገድ በጎርፍ ምክንያት በተደጋጋሚ የሚዘጋ ነው። ዛሬም በጣለው ዝናብ ከቀላል እስከ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም። መንገዱ የተዘጋው ከተራራማ ቦታዎች የሚወርድ ደለልን መከላከል የሚያስችል ደጋፊ የግንብ አጥር ባለመኖሩ ነው። በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮምቦልቻ መንገድ ዝርጋታ ዳይሬክተር…
#update ትናንት በደለል ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የወልድያ ቆቦ መንገድ ለጊዜው ደለሉ ተጠርጎ ከትናንት ማታ ጀምሮ ተሽከርካሪዎች እየተላለፉ ነው፤ ነገር ግን ችግሩ በዘላቂነት ካልተፈታ ዛሬም ከበድ ያለ ዝናብ ከጣለ መዘጋቱ አይቀሬ እንደሆነ #አብመድ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ዮሃንስ ቧያለው ሹመቱን አልቀበልም ብለዋል!
አቶ ዮሃንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንትነት ሹመትን እንደማይቀበሉት አስታወቁ።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በትናንትነው ዕለት አቶ ዮሃንስ ቧያለውን የመለስ ስራ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንት እንዲሆኑ መሾሙ ይታወሳል።
ይሁንና አቶ ዮሃንስ ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ ሹመቱን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።
#ኢትዮኤፍኤም #አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አዲስ ለሚገነባው የሀዲስ አለማየው ልዩ አዳሪ ትምህርት ዛሬ ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እየተካሄደ ይገኛል! በአንጋፋው ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ ተሰይሞ በትውልድ መንደራቸው በደብረማርቆስ ከተማ በ100,000 ካሬ ሜትር ላይ ሊገነባ የታሰበውና 2,000 የሚያህሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ለተባለለት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ማስገንቢያ አስመልክቶ ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ…
#UPDATE
ለሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ በመጀመሪያው ዙር ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል ተገባ!
ዛሬ በአዲስ አበባ ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ የመጀመሪያ "ቴሌቶን" ለግንባታው ከሚያስፈልገው 200 ሚሊዮን ብር ውስጥ ከ 72 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል ተገብቷል።
ሁለት ባለሀብቶች ደግሞ ከትምህርት ቤቱ የሁለት ሕንፃዎችን ግንባታ ከነቁሳቁሳቸው እንደሚችሉ ቃል ገብተዋል። ለግንባታው የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መስጠቱም ታውቋል።
ለአጠቃላይ ግንባታው 200 ሚሊዮን ብር ለሚያስፈልገው ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት በቀጣይ በደብረ ማርቆስ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ከተሞች የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እንደሚያዘጋጅ ታውቋል።
#አብመድ
PHOTO : #TikvahFamily

#GERD
በግድቡ ጉዳይ በኢትዮጵያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመመከት ዝግጁ መሆኗን ግብጽ አስታወቀች!
የዓባይ ወንዝን በተመለከተ ሀገራቸው የትኛውንም አማራጭ እንደምትጠቀምና ታሪካዊ ተጠቃሚነቷን እንደምታስቀጥል የግብጽ ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ አስጠነቀቁ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት አሜሪካ ላይ ሊካሄድ በነበረው የሦስትዮሽ ድርድር ኢትዮጵያ አለመገኘቷን ተከትሎ ግብጽ ጉዳዩን በአሉታ እየተመለከተችው ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ ግድቡን በተመለከተ ሰፊ ምክክር ማድረግ እና ብሔራዊ ጥቅሟን በዘላቂነት የሚያስጠብቅ አቋም መያዝ በሚያስችላት ሐሳብ ላይ መምከርን ማስቀደም ስላለባት በድርድሩ እንደማትሳተፍ መግለጧ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም የግብጽ ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሶሊማን ዋድሃን ዛቻ የተሞላበት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል አፈ-ጉባኤው ይህንን ያሉት የግብጽ ውጭ ጉዳይ እና የመስኖ ሚኒስትሮች ‘ኢትዮጵያ በድርድሩ ያልተገኘችው ድርድሩን ሆን ብላ ልታደናቅፍ ነው’ የሚል ሐሳብ ማሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
More https://telegra.ph/GERD-03-03
#አልኣህራም #አብመድ