TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በሀገሪቱ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ቄያቸው #መመለስ መቻሉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተለያዮ ጊዜያት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት አያሌ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለው ለእንግልት #መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡

ግጭቶቹም በዋናነት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል፣ በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ፣ በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በሶማሊያ ክልልና በቡራዮ ከተማ የተከሰቱ ናቸው፡፡

በእነዚህም ግጭቶች ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ነበሩበት አካባቢ መመለስ መቻሉን በብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በመጠለያ ጣቢያ የነበሩ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው #መመለስ ጀመሩ። ባለፉት ጊዘያት በወቅታዊ ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ተፈናቅለው  በአይምባ መጠለያ ጣቢያ ከነበሩት መካከል የነባሩ  ጭልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ወደቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሕዝቡ ወደቀየው #መመለስ ጀምሯል፤ ግን ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡››

‹‹ችግሩን ለመፍጠር ካስፈለገው ምክንያት አንፃር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ሊሠራልን ይገባል፡፡›› የአጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራቆሬ ነዋሪዎች
.
.
.
ሰሞኑን በሰሜን ሽዋ ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራ ቆሬ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት እና ንብረት ጠፍቷል፡፡ በችግሩም ከቀያቸው ውጭ የተሰደዱ ዜጎች እንዳሉ አብመድ ከአካባቢዎቹ ነዋሪዎች አረጋግጧል፡፡

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊው አቶ ሰለሞን አልታየ ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋዱ ድረስ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ዳግም በከተማዋ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በግጭት ስጋት ከቀያቸው ሸሽተው የነበሩ ወገኖቻችንም መመለስ ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ዜጎቹ ቢመለሱም ሀብት ንብረታቸው በመዘረፉ ለዕለት ሊበሉ የሚችሉት እንኳ ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታነቱን እንዲያሳይ እጠይቃለሁ ነው ያሉት፡፡ በአከባቢው የመከላከያ ሠራዊት ሰላም የማስጠበቅ ሥራ እየሠራ ነው፤ በዘላቂነት ከሚነሳው እና ከሚታየው ሐሳብ አንፃር የቀጠናውን ሰላም ለማስጠበቅ እና ከመሰል ድርጊቶች ለመጠበቅ የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ በአቅራቢያው ሊኖር እንደሚገባም አቶ ሰሎሞን ተናረዋል፡፡

በማጀቴ ከተማ ውስጥ በሕመም ምክንያት ከመንደራቸው እንዳልወጡ የነገሩን ወይዘሮ ፋጤ ደሳለኝ ከትናንት ጀምሮ እስከ ርፋዱ ድረስ ያለው የአካባቢው ሁኔታ ሰላማዊእደሆነ ነግረውናል፡፡ ሕዝቡም ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የገለጹልን፡፡

የካራ ቆሬ ነዋሪው አቶ ደንበሬ ገብረማሪያም ደግሞ ‹‹ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ 5፡30 ድረስ አካባቢው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊትም እየተዘዋወሩ ሰላማችን እየጠበቁልን ነው፡፡ ሕዝቡም ስለ አጥፊዎቹ ሙሉ መረጃ ለመስጠት ዝግጁ ነው›› ብለዋል፡፡ አቶ ደንበሩ ከተለያዩ አጎራባች ከተሞች እና በየተራራው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የተመላሾቹ መኖሪያ ቤት እና የንግድ ተቋማት ሙሉ በሙሉ በግጭቱ ቀናት በመዘረፉ እና በመውደሙ የዕለት ጉርስ የላቸውም፤ እነዚህን በዘላቂነት ለማቋቋም መንግሥት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ አስቸኳይ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል›› ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመፍጠር ካስፈለገው ምክንያት አንፃር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ሊሠራልን ይገባልም ብለዋል አቶ ደንበሩ፡፡

በከተማዋ ግጭት ለፈጠሩ ኃይሎች መረጃ አቀባዮች በመኖራቸው የአካባቢው ሕዝብ ወደመደበኛ ሥራው ለመመለስ በመቸገሩ አጥፊዎችን የመያዝ እና ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የማድረግ ኃላፊነት ወስዶ መንግሥት ሊሠራ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ዜና!

ከካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ የተፈናቀሉ #የከምባታ_ጠምባሮ ብሔረሰብ ተወላጆች ወደ ቀያቸው #መመለስ ጀመሩ። የከምባታና ጠምባሮ ብሔረሰብ ተዎላጆች ከወራት በፊት በካፋ ዞን የተከሰተን ግጭት በመሸሽ ነበር ዞኑን ለቀው የሄዱት።

Via #ELU

ሰላም፣ ፍቅር፣ ተስፋ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው...

ከደቡብ ክልል ጎፋ ዞን፣ መሎ ኮዛ ወረዳ ከወራት በፊት በተፈጠረ ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው #መመለስ ጀመሩ። ከአካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ ከ37 ሺ በላይ የባስኬቶ ብሔረሰብ አባላት በመጠለያ ጣቢያዎች በቆዩባቸው ጊዜያት የከፋ ችግር አሳልፈዋል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia