TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለ1439ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

ሕብረተሰቡ በበዓሉ ላይ በአዲስ አበባ ስቴድየም እና በዙሪያው #ፍተሻ መኖሩን ተገንዝቦ ለፍተሻ እንዲተባበር፣ የእምነቱ ተከታዮች ለሶላት ሲመጡ የስለት መሳሪያዎችንና ሌሎች አዋኪ ነገሮችን ይዘው ባለመምጣት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ስቴድየም የሚደረገውን የሶላት ስነስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንምይፋ አድርጓል:-

➢ ከቦሌ- ኦሎምፒያ -ፍላሚንጎ ወደ መስቀል አደባባይ

➢ ከኡራኤል-ባምቢስ ወደ ምስቀል አደባባይ

➢ ከአራት ኪሎ - ብሔራዊ ቤተመንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤተክርስትያ

➢ ካሳንችስ -ብሔራዊ ቤተመንግስት -ፍልውሀ

➢ ከንግድ ማተሚያ ቤት -ኦርማ ጋራዥ- ፍል ውሃ -ሐራምቤ ሆቴል

➢ ከቴድሮስ አደባባይ -ኢምግሬሽን- ሀራምቤ ሆቴል - ስቴድየም

➢ ከጎማ ቁጠባ- ብሄራዊ ትያትር- ስቴድየም

➢ ከሰንጋ ተራ - በድሉ ህንጻ -ስቴድየም

➢ ከሰንጋ ተራ - በለጋሀር- ስቴድየም

➢ ከሜክሲኮ አደባባይ- በለገሀር -ስቴድየም

➢ በቂርቆስ አዲሱ መንገድ -በለገሀር -ስቴድየም

➢ በሀራምቤ ሆቴል -ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ

➢ ከጎተራ - በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ:-

ከቦሌ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች

➢ በኡራኤል -በካሳንችስ-አራት ኪሎ
ከመገናኛ ወደ ጦር ሀይሎች መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች

➢ በኡራኤል -ካሳንችስ -ታላቁ ቤተመንግስት -እሪበከንቱ -ቴዎድሮስ አደባባይ- ኤክስትሪም ሆቴል- ተክለሀይማኖት- ጦር ሀይሎች ከሳሪስ አቅጣጫ ወደ አራትኪሎ እና ፒያሳ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች

➢ ጎተራ -ወሎ ሰፈር - አትላስ ሆቴል - ኡራኤል - ካሳንችስ -አራት ኪሎ ያሉ መንገዶች በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከዛሬ ነሀሴ 14/2010 ማታ ጀምሮ የሶላት ስነስርዓቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በስታድየም ዙሪያ እና አከባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጹም #የተከለከለ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ሕብረትሰቡ ለጸጥታ #አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥሮች

• 011-5- 52-63-03
• 0115-5- 52- 40-77
• 011-5- 52- 63-02
• 011-1- 11-01-11 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

©EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ~ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#በቡድንም ሆነ #በተናጠል የሀዋሳ ከተማ ኀብረተሰብን #ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ሂደቱን ማወክ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣ በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ #የተከለከለ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኝ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ገልጿል።

#ሲዳማሪፈረንደም2011 #ሀዋሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር!

ከነሃሴ ወር መጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ #የተከለከለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ለማድረግ ወላጆችን እያስገደዱ መሆኑንና ምዝገባ በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

የትምህርት ሚኒስቴር የኮምኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ መጨረሻ በፊት ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንማይቻልና ይህንን ወሳኔ አልፈው ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይም አስፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።

የምዝገባው ግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተደረገው የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆችና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
" በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም "

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት የተንዛዛ ድግስንና ያለ እድሜ ጋብቻን ፣ ሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው ያላቸውን ድርጊቶች ለማስቆም አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የተላለፉት አዳዲስ ውሳኔዎች ፦

- ያለ እድሜ ጋብቻ እና የህግ ማእቀፍ ያላቸው ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ በወጣው ህግ መሰረት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆን፤

- ከአለባበስ ባህል አኳያ በዞኑ ስር ያሉ ሁሉም ወረዳዎች የሚመሩት ህዝብ አንድም ሰው በባዶ እግሩ እንዳይሄድና ቁምጣ ለብሶ የሚሄድ ሰው እንዳይኖር እንዲሰሩ፤

- በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም ፤ ስርአተ በቤተክስቲያን በሚያዝዘው መሰረት ስርአተ ፍትሃት ላደረጉ ካህናት አባቶች ብቻ ቤተክርስቲያን ላይ 1 በግ/ፍየል እና 2 ሌማት ብቻ እንዲቀርብ፤

- ጋብቻ አንዱ ባህላዊ እሴት መሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ እና ትውልድ መቀጠል ስላበት " ጋብቻ ይቁም " እንደማይባል የገለፀው ም/ቤቱ ነገር ግን በጋብቻ ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስን በተመለከተ ለአጋቢ ሽማግሌዎችና ለቤተሰብ የሚሆን 1 በግ/ፍየል እና  2 ሌማት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን እና የቀንድ ከብት ማረድ ፍጹም #የተከለከለ መሆኑ አሳውቋል።

በውሳኔው መሰረት በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ከፍትህ ተቋሙ ጋር ተቀናጅተድ ውሳኔዎቹን እንዲያስፈፅሙ ጥብቅ መመሪያ ተሰዝትቷል።

አፈጻጸሙንም በጋራ እየገመገሙ የተገኘውን ውጤት እና የመጣውን ለውጥ እስከ ጥር 15/2015 ዓ/ም እንዲያሳውቁም መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል። በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል። #EOTCTV @tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ?

ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦

➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣

➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ

➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣

➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣

➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል።

#የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

@tikvahethiopia