TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

ሰባት ኪሎግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሃገራት ገንዘብ #መያዙን ገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ። አራት ተጠርጣሪዎችም #በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የገቢዎች ሚኒስቴር #ቶጎ_ውጫሌ ኬላ ላይ ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጪ አገር ገንዘብ መያዙን ገልጿል።

የአሜሪካ፣ የካናዳና የአውስትራሊያ ዶላር፣ ዩሮ፣ ድርሃምና የሌሎች ሃገራት ገንዘብ ነው የተያዘው ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

ትናንት ምሽት ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የውጪ አገር ገንዘብ ከአራት ተጠርጣሪ ኮንትሮባንዲስቶች ጋር በቶጎ ዉጫሌ ኬላ በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስመጪዎች እና ማናጀሮች

በተለያዩ ከተሞች የሚስተዋለው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ህገወጥ ምንዛሬ በትላልቅ አስመጪዎች እና በባንክ ማናጀሮች ዋነኛ ተዋናይነት የሚመራ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገለጸ።

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናንስ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ምንዛሬ ዋነኛ ተዋናዮች አስመጪዎች፣ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች በተለይም የባንክ ማናጀሮች ናቸው።

በየአካባቢው የሚገኙት ዶላር መንዛሬዎች ግን ሶስተኛ ወይንም አራተኛ አካላት ናቸው። እንደ ኮማንደር ታደሰ ገለጻ፣ በየአካባቢው የሚገኙት ዶላር መንዛሬዎች ዋነኛ የህገወጥ ተግባሩ ተዋናዮችን በውል የማያውቁ እና ለእነርሱ የሚሰሩ ናቸው።

ህገወጥ ተግባሩ በተዋረድ (በኔትወርክ) የሚከናወን እና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያላቸው አስመጪዎች የሚያንቀሳቅሱት ነው። በተጨማሪ የባንክ #ማናጀሮች ዶላር ፈልጎ የመጣን ባለሀብት ቢሮክራሲ በማብዛት ዶላር እንደሌለ አስመስለው ያባርራሉ። በጎን ደግሞ ደላሎችን ልከው ወደ ህገወጥ መንገድ እንዲሄዱ በማመቻቸት ገንዘብ ተቀብለው ይሰጧቸዋል።

ኮማንደር ታደሰ እንደተናገሩት፤ በአንድ የአሜሪካን #ዶላር ከ10 ብር እስከ አስራ አራት ብር ትርፍ በመውሰድም #ከደላሎች እና በየደረጃው ካሉ ህገወጦች ጋር ይከፋፈላሉ። በተለይ በሶማሌ ክልል #ቶጎ_ውጫሌ የሚገሹ 16ቱም ባንኮች በህገወጥ የዶላር ምንዛሬ ውስጥ እንደሚሳተፉ መረጃ አለ። በሶማሌ ላንድ ጠረፍ ከተማዋ የሚገኙ እና በተለያዩ ከተሞች የሚሰሩ የባንክ ማናጀሮች በዚህ ህገወጥ ተግባር እንደሚሳተፉ የፌዴራል ፖሊስ መረጃው አለው። በሌላ በኩል በህገወጥ መንገድ ከአገር የዘረፉትን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ለማንቀሳቀስ የሚፈልጉ ሰዎች ሀብታቸውን ወደ ዶላር መንዝረው ከአገር ለማስወጣት ይጠቀሙበታል።

በዚህ ዓመት በመርካቶ እንደተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ አሁንም በቀጣይ እንደሚደረግ የገለጹት ኮማንደር ታደሰ፤ ይሁንና ዋነኞቹ የምንዛሬው ተዋናዮችን ለመያዝ መረጃ ሳይሆን ማስረጃ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ ለዚህ ደግሞ ህብረተሰቡ ተሳታፊ መሆን አለበት። ህብረተሰቡ ደግሞ መረጃ ቢያቀብልም መስካሪ ሆኖ የችግሩን አመንጪዎች ለመከላከል ፍላጎት አያሳይም። ፖሊስ ግን ገንዘብ የያዘን ሁሉ አስሮ መቅጣት ስለማይችል የህብረተሰቡ የማጋለጥ እና የመመስከር ልምድ መጠናከር አለበት። ፌዴራል ፖሊስም ማስረጃ ባጠናቀረ ወቅት ህገወጦችን ለመቅጣት የሚያስችል ስራ ማከናወኑ አይቀርም ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia