TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ለማስፈጸም ከትናንት በስቲያ ጀምሮ መተግበር የጀመረው አሠራር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎችን እያጨናነቀ እና ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆነ እንዳለ ተገልጿል።

ተገልጋዮች ከመጠን በላይ የነዳጅ ግዥ እየፈጸሙ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ማደያዎች የነዳጅ እጥረት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዲጂታል ክፍያ መተግበሪያውን ለመጠቀም የተፈጠረው ብዥታም በብዙ ማደያዎች ረዣዥም ሠልፎች እንዲታዩ ከማድረጉም በላይ ቶሎ ነዳጅ ቀድቶ ለመሄድ አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ አሁን ያለው መጨናነቅ የተፈጠረው አገልግሎቱን ለማስጀመር በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱና አሽከርካሪዎች አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት እንዲዘጋጁ ባለመደረጉ ነው ብሏል።

" ይሄንን ሥጋታችንን ቀደም ብለን  አሳውቀናል " ያለው ማህበሩ " አሁን ብዙዎች ወደ ሲስተሙ እየገቡ ቢሆንም ከሥጋት አንጻር የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " ሲል አሳውቋል።

ድርጊቱ የነዳጅ እጥረት ሊያስከትል ይችላል ተብሎ እንደሚሠጋ የገለፀው  የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆን እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል፥ ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ሲል ማህበሩ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ከዚሁ የነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም አሠራሩን ከመተግበር አንጻር ያለውን መጨናነቅ ለማስቀረት በሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎች #ባለሙያዎችን በማሰማራት ለተገልጋዮች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ደኤታው አቶ ኦዴኦ ሐሰን ፥ ይህን አገልግሎት ለመተግበር #መንገራገጮች ቢኖሩም፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው አዲስ አሠራር ከግንቦት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋጋጠዋል፡፡

የአገልግሎቱ መጀመር ዘመናዊ ግብይትን ከማሳለጥ ባለፈ ከነዳጅ ሥርጭት ጋር በተያያዘ ሲፈጠሩ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችንና ብክነትን ከማስቀረት አኳያ፣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

ይህንን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት መተግበሪያዎቹን ይፋ ባደረገበት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia