#update⬆️ላለፉት 8 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት የቢርመጂ ቱለማ አባ ገዳ #በየነ_ሰንበቶ የአመራር ዘመናቸውን በታላቅ ስኬት በማጠናቀቅ ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ ለሜልባ አባገዳ ጎበና ሆላ እሬሶ አስረክበዋል ፡፡ ሙሉ ስነ-ስርዓቱ ቅዳሜ መስከረም 19/2011 ይካሔዳል።
ምንጭ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መካከል እርቅ ለማውረድ የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ የፊታችን ረቡዕ ወደተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች እንደሚሰማራ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው ወደ ወለጋ ዞኖች፣ ጉጂ ዞኖችና ቦረና ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኢሉ አባቦራና ፈንታሌ ዞኖች እንደሚሰማራ ገልጿል፡፡ ኮሚቴው ከሁለቱም አካላት ጋር ውይይት ማድረጉንና ከዚህ ቀደም ተወስኖ የነበረው ቀነ ገደብ ላይ ተጨማሪ 10 ቀናት መጨመሩን የቀድሞ የቱለማ አባገዳ #በየነ_ሰንበቶ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ:- OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ:- OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቅ ኮሚቴ አባላት ታፍነው ተወሰዱ‼️
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥትን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የግንባሩን ወታደሮች #ለመቀበል ወደ #ቄለም_ወለጋ አቅንተው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት #ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።
የእርቅ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ #በየነ_ሰንበቶ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የኮሚቴው አባላት የሆኑ ሁለት አባ ገዳዎች እና አንዲት ሴት በቄለም ወለጋ #አንፊሎ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ታፍነው እንደተወሰዱ ተናግረዋል።
አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ''ለማግባባት ወጣ እንዳሉ ነው ታፍነው የተወሰዱት፤ ክፉ ነገር #እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህንም ችግር በቅርቡ እንፈታዋለን'' ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
''ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖሩን እየወቅን ነው እርቅ ወደማውረዱ የገባነው። እርቅ ለማምጣት ነው እየሰራን ያለነው። ሰላምም ይሰፍናል። የሚያጋጥሙን ችግሮች ወደ ኋላ አያሰቀሩንም'' ሲሉም ጥረታቸውን በዚህ ምክንያት እንደማያቋርጡም ተናግረዋል።
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያነጋገረው የየኮሚቴው ፀሃፊ #ጀዋር_መሃመድም የእርቅ ኮሚቴ አባላት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ተናግሯል።
''የገጠመ ችግር አለ። በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ከኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለህዝቡ መግለጫ እንሰጣለን'' ሲል ጀዋር ገልጿል።
ጀዋር ሃሙስ ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን አራት ሰዎች ከስም ዝርዝራቸው ጋር አውጥቷል። ታፍነዋል ተወስደዋል የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል።
በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡ ወረዳ የቴክኒክ አባላቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከነዋሪዎች ተሰምቷል። ተፈጸሟል ስለተባለው ድብደባ ግን ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት #ማረጋገጥ አልተቻለም።
የእርቅ ኮሚቴ አባላቱን ማን አፈናቸው?
የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶም ሆኑ የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድ የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ያፈነው ኃይል ይህ ነው በማለት በስም ከመጥቀስ #ተቆጥበዋል።
ጀዋር የአባላቱን መታፈን ይፍ ባደረገበት ጽሁፍ ''እየደረሰብን ያለውን #ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን'' ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።
ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ደለሳ ቡልቻ ለሁለት ቀናት ታፍነው ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸው ይታወሳል። ዶ/ር ደለሳ የገጠማቸውንና ማን እንዳፈናቸው ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ባንኮች በተዘረፉበት ወቅትም የባንክ ሰራተኞችም ታፍነው ተወስደው እንደነበረ ይታወሳል።
ምንጭ፦ BBC አማርኛ