TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ይሄ ካስተማረን...

የመን ውስጥ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 85 ሺ #ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ሴቭዘቺልድረን የተባለው ምግባረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት 14 ሚሊዮን የመናውያን ከባድ ረሃብ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ገልጾ ነበር።

ለዚህ ሀሉ መነሾው ደግሞ ሶስተኛ ዓመቱን የያዘው #የእርስ_በርስ_ጦርነት ሲሆን፤ ያስከተለው ጉዳትም በዓለማችን ካጋጠሙ ሰብዓዊ ቀውሶች ትልቁ አስብሎታል።

እስካሁን 6800 ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ የምግብ እጥረት ደግሞ አብዛኛውን የሃገሬውን ሰው እየፈተነ ያለ ጉዳይ ነው።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከእነዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ፈተናዎች ያለፉት ደግሞ በኮሌራ ወረርሽኝ እየተጠቁ እንደሆነና በበሽታው ምክንያት1.2 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።

85 ሺዎቹ ህጻናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን ለማረጋገጥና መረጃ ለማሰባሰብ እጅግ ፈታኝ እንደነበረ የረድኤት ድርጅቱ ገልጿል።

ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሃገሪቱ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በጦርነቱ መውደማቸው ነው።

ከጦርነቱ የተረፉት የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት ማግኘት እጅግ ውድ ስለሚሆን አብዛኛዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ሲያልፍ እንኳን በተገቢው ሁኔታ አልተመዘገቡም።

85 ሺዎቹ ህጻናት ህይወታቸው ያለፈው እ.አ.አ. ከሚያዚያ 2015 እስከ ጥቅምት 2018 ድረስ እንደሆነ ተጠቁሟል።

#አልቆም ያለው ጦርነት የሃገሪቱን የገንዘብ አቅም እጅግ ያዳከመው ሲሆን፤ የምግብና አስፈላጊ እቃዎች ዋጋ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ነው።

የመን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ምግብ ከውጪ የምታስገባበት ወደብ በአማጺያን ቁጥጥር ሲሆን፤ በሃገሪቱ ያለው የምግብ ክምችት 4.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ብቻ የሚበቃ እንደሆነ ሴቭዘቺልድረን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ethiopia #UNICEF

ስለምስራቅ አፍሪካ ድርቅ እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ስላሳደረው ተፅእኖ ምን ያህል እናውቃለን ?

(የተመድ የህጻናት ተራድኦ ድርጅት - UNICEF)

➤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ምስራቅ አፍሪቃን የመታው ድርቅ ከ10 ሚሊየን በላይ #ህጻናት ለአስከፊ የምግብ እጥረት ዳርጓል። እስካሁን በርሃም አደጋው የሞተ ሰው አላጋጠመም።

➤ በኢትዮጵያ ባጋጠመው 3 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች የዝናብ እጥረት በዓመታት አስከፊ የድርቅ ሁኔታ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፤ አስከፊው ድርቅ ለበርካታ እንስሳት ሞት ፣ የውኃ ምንጮችም ተሟጠው እንዲደርቁ መንስኤ ሆኗል።

➤ በ4 ክልሎች (ሶማሊ፣ ኦሮሚያ ፣ አፋር፣ ደቡብ ) ድርቅ በሰፊው የተከሰተባት ኢትዮጵያ ከችግሩ ለመላቀቅ ቢያንስ 5 ዓመታት ያስፈልጓታል።

➤ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋርና ደቡብ) ድርቁ 10 ሚሊየን ህዝብ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አሳርፏል። ከዚህ ውስጥ 1.5 ያህሉ ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ህጻናት ናቸው፡፡ 

➤ በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ 1.75 ሚሊየን ህዝብን ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቋል።

➤ በሶማሊ ክልል ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 220 ሺ ህጻናት ገደማ የተመጣጠነ ምግብ እጦት አለባቸው፡፡ ከ150 ሺህ በላይ አጥቢና እርጉዝ እናቶች በቂ ምግብ የማያገኙ ናቸው።

➤ ባለፈው ዓመት በችግሩ ሳቢያ ከ400 ሺ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተቆራርጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ ያለዕድሜ ጋብቻን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ምስቅልቅሎችን አሳርፏል።

➤ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ የናረው የስንዴና ሌሎች መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ የድርቅ ተፅእኖውን ምላሽ የመስጠት ጥረቶችን አዳጋች አድርጎታል።

#UNICEF #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
🚨 #ዲላ 🚨

ዛሬ በዲላ ከተማ 10 ሠዓት ገዳማ ንፋስ ቀላቅሎ በዘነበው ከባድ ዝናብ #ሁለት የአንድ ቤተሰብ #ህጻናት ህይወታቸው አልፏል።

2 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውም ሰዎች አሉ።

ንብረት ላይም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

በርካታ ዛፎች እና በርካታ የኤሌክትሪክ ፖሎች ወድቀዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይልም ተቋርጧል።

ነዋሪው የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተካክሎ ወደ ቦታው እስኪመለስ እንዲታገስና እራሱ ከተለያዩ አደጋዎች እንዲጠብቅ የከተማው አስተዳደር አደራ ብሏል።

@Tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኪርጊስታን ውስጥ እንዲታገድ ተወሰነ። ኪርጊስታን " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስናለች። ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱ የባህል ፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ነው። ሚኒስቴሩ ባደረገው ግምገማ መሰረት " ቲክቶክ " ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ መቆጣጠሪያ…
#Update

የ " ቲክቶክ " እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።

ኪርጊስታን " ቲክቶክ " በመላ ሀገሪቱ  እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።

በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።

ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት " Unable to load, please try again." የሚል ነው።

ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።

የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ' ባይት ዳንስ ' ኩባንያ ፥ " #የልጆችን
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም " ብሏል።

በዚህም ምክንያት " ቲክቶክ " በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።

ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው " ማለቱ ይታወሳል።

መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።

በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።

ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን  " ቲክቶክ " ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia