TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"እኛ የዛሬዎቹ መሪዎች ይኸቺን ታሪካዊ አገር ልትሰምጥ ነው ከተባለችበት አዘቅት ውስጥ አውጥተን የልጆቿ ኩራት እና ክብር እናደርጋታለን? ወይስ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ መሆናችንን ዘንግተን እርስ በርሳችን በርስት እና ጉልት #እየተፋጀን የልጆቻችን #ማፈሪያ እና የዓለም #መሳቂያ እናደርጋታለን?"

▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ▪️▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ የግፍ ግፍ ሰርተው እንጦሮጦስ ያወረዷት መሪዎችም ነበሯት:: አንድ አድርገው ከነበሩባት ችግር ያወጧት መሪዎችም ነበሯት፡፡
ቁም ነገሩ አሁን ይህችን ታሪካዊ ሀገር ታሪካዊነቷን እንመልሳለን? ወይስ #ማፈሪያ እደርጋታለን? ወይስ የዓለም ተምሳሌት እናደርጋታለን? የሚለው ሲሆን ምርጫውም በእጃችን ነው፡፡ ሁላችንም በቀና ልቦና ከሰራን ሀገራችንን ወደ ቀደመ ገናናነቷ እንመልሳታለን፡፡"

▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ▪️▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍቅር ከሌለህ የከንቱ ከንቱ ነህ!!

"እውነተኛ #ፍቅር ቀለም፣ ብሄር፣ ጎሳ፣ ክልል፣ ዜግነት፣ ሀገር፣ የኑሮ ደረጃ... አይመርጥም ሁሉንም #ያቅፋል፤ ሁሉንም #ይስማል!"
.
.
እውነተኛ ፍቅር በውስጥህ ሳይኖር ስለሰው ልጅ ክቡርነት ሳትረዳ ስለብሄር፣ ጎሳ፣ ክልል፣ ሀገር፣ ባንዲራ ብታወራ የከንቱ ከንቱ ነህ እልሃለው። አጠገብህ ያሉትን ወንድሞችህንና እህቶችህን ወደው ባላመጡት ብሄራቸው እየለየህ #እያቋሸሽክና #እየሰደብክ፤ እያሳደድክና እያዋረድክ፤ እየገደልክ እና እያፈናቀልክ ስለዴሞክራሲ እየታገልኩ ነው፤ ስለብሄሬ እና ማንነቴ እየታገልኩ ነው ብትል የ ዓለም #ማፈሪያ እልሃለሁ።
.
.
እውነተኛ #ፍቅር ቀለም፣ ብሄር፣ ጎሳ፣ ክልል፣ ዜግነት፣ ሀገር፣ የኑሮ ደረጃ... አይመርጥም ሁሉንም #ያቅፋል፤ ሁሉንም #ይስማል!
.
.
ዶክተር አብይን #ማድነቅ እና #መስማት፤ መደገፍ እና መከተል ብቻ በቂ አይደለም የሚሰራውን እያዩም መማር ትልቅነትና አዋቂነትም ጭምር ነው!

🔹ፀጋአብ ወልዴ ኢትዮጵያ🔹
@tsegabwolde @tikvahethiopia