TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዶክተር አብይ የቅርብ ሰው አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው⬇️

"From The Airport to the State House in #Asmara ’s streets, the Ethiopian delegation was greeted & received with overwhelming joy & love by the kind people of Eritrea. The yearning for peace was palpable & we’ll decidedly move forward for the good of our people. #Ethiopia #Eritrea"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፕሬዘዳንት ኢሳያስ የቅርብ ሰው አምባሳደር ኢስጢፋኖስ በትዊተር ገፃቸው⬇️

"No leader has received such a warm welcome like today in Asmara in the history of #Eritrea extended by the people to PM Abey of #Ethiopia"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-SPORT
#ETHIOPIA #ERITREA

በኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የሚመራና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ደምጻዊያንና የጃኖ ባንድ የተካተቱበት ከ60 በላይ አባላትን የያዘ የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ከሰኞ ታህሳስ 6 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ ወደ ኤርትራ ይጓዛል። የባህል በድኑ የኤርትራ ጉዞ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው። ከውጭ ጉዳይ እንዳገኘነው መረጃ የባህል ቡድኑ በኤርትራ ቆይታው በአስመራ፣ ከረን እና ምጽዋ ከተማዎች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። የኤርትራ የባህል ቡድን በለፈው የካቲት ወር 2011 ዓም በአገራችን በመገኘት ተመሳሳይ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በባህርዳር እና በሀዋሳ ከተማዎች ማቅረቡ ይታወሳል።

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #ERITREA

በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተመራው የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን ዛሬ ከሠዓት በኋላ ወደ ኤርትራ አምርቷል። ቡድኑ ከውጭ ጉዳይና ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ድምጻዊያንና የጃኖ ባንድ የተውጣጡ ከ60 በላይ አባላትን መያዙ ተገልጿል። የባሕል ቡድኑ ጉዞ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነም ተነግሯል። የባሕል ቡድኑ በኤርትራ ቆይታው በአስመራ፣ ከረን እና ምጽዋ ከተሞች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ከውጭ ጉዳይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #ERITREA

በኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተመራው የአገራችን የባህል ቡድን ዛሬ ታህሳስ 6 ቀን 2012 ዓም ከስዓት በኋላ አስመራ ገብቷል። ቡድኑ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በኤርትራ የባህል እና ስፖርት ኮምሽነር አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ፣ በኤርትራ የኢፌዲሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ በአፍሪካ ህብረት የኤርትራ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር አርዓያ ደስታ፣ ታዋቂ የኤርትራ አርቲስቶች፣ የኤርትራ የሴቶች ማህበር እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #ERITREA

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መክረዋል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለአጭር ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#ERITREA

በኤርትራ ተጨማሪ 5 ሰዎች አገገሙ!

የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አምስት (5) ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ በሽታ አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸውን አሳውቋል። በሀገሪቱ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል። እስከዛሬ ድረስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 39 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Eritrea

አንድ ከኢትዮጵያ ወደ አስመራ የተመለሰ ሰውና አስራ አንድ (11) ከሱዳን ተመልሰው በኣዲባራ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአጠቃላይ በኤርትራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ አንድ (121) የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሰላሳ ዘጠኝ (39) ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Eritrea

በኤርትራ ተጨማሪ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም በቅርቡ ከሱዳን የተመለሱና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በአጠቃላይ ኤርትራ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 131 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Eritrea

ከ45 ደቂቃዎች በፊት ኤርትራ ላይ የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን የሚገልፁ ሪፖርቶች ወጥተዋል።

የአስመራ ነዋሪዎችም ምሽቱን የፍንዳታ ድምፅ እንደሰሙ አሳውቀዋል።

ከአስመራ ከተማ ውጭ በደቀምሓረ፣ አዲሃሎ አካባቢ ጥቃት ሳይሰነዘር እንዳልቀረ ተገልጿል።

እስካሁን በጥቃቱ ስለደረሰ ጉዳት የታወቀ ነገር የለም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Eritrea

ጎረቤታችን ኤርትራ ትላንት የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስተናግዳለች።

ሟቹ የ50 ዓመት እድሜ ያለው ወንድ #ደቀምሓረ ሆስፒተል ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና ሲደረግለት የነበረ ነው።

የዛሬ ሪፖርትን ጨምሮ በአጠቃላይ በኤርትራ ውስጥ 877 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ የ1 ሰው ህይወት አልፏል፤ 599 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT