TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ባጃጅ ታግዷል " በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ የካቲት 30 ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ። ከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ አገልግሎት መታገዱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ " የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን…
#ባጃጅ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች / ባጃጅ መታገዱን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አጭር ማብራሪያ ሰጥቷል።

በማብራሪያው ፤ " መንግስት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን #የነዳጅ_ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉ እየታወቀ የባለሶስት ጎማ ወይም በተለምዶ አጠራራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እንዲሁም የተወሰኑት በወንጀል ድርጊቶች ላይ በመሰማራት የከተማችን ነዋሪ የቅሬታ ምንጭ ሆነዋል " ብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ የባጃጅ አገልግሎትን ስርዓት ለማስያዝ የአሰራር ማስተካከያ እያደረገ መሆኑን ገልጾ ይህ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ በከተማድ ሁሉም አካባቢዎች የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት #እንዲቆም መወሰኑን ገልጿል።

የተሸርካሪዎቹ ከስራ መውጣት በነዋሪው ላይ የትራንስፖርት ጫና እንዳያሳድር አስተዳደሩ ሌሎቹ የትራንስፖርት አገልግሎቶች በሙሉ አቅማቸውና በቅንጅት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ መመቻቸቱን አመላክቷል።

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌሎች ጉዳዮችንም ያነሳበት የዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ባጃጅ

" በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንን እንዲሁም ሴቶች እና ሕፃናትን ታሳቢ በማድረግ እገዳውን ማንሳትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያስፈልጋል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሰጥ እገዳ መጣሉና በተለያዩ ሰብአዊ መብቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ገደብ የሚጥል እርምጃ በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው ብሏል።

ኮሚሽኑ ይህንን በተመለከተ በላከልን መግለጫው እገዳውን ተከትሎ የደረሱትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የአ/አ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

ኃላፊዎቹ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በከተማዋ ወደ 10 ሺህ የሚገመቱ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ፈቃድ ያልተሰጣቸው ናቸው።

- እንደ አንድ አገልግሎት ሰጪ በከተማዋ አሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋላቸው መሆኑን፣ ሌሎችም ተዛማጅ ችግሮች አሉ።

- ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ከዋና መንገዶች ውጪ ባሉ ውስጥ ለውስጥ መንገዶች እስከ ሁለት ኪሎ ሜትር ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ማስተካከያ እየተወሰደ ቢቆይም በአንዳንድ አካባቢዎች ባጃጆቹ ከተቀመጠላቸው የእንቅስቃሴ አካባቢ ውጪ በዋና መንገዶች ላይ ሲሠሩ በመታየታቸው እና የከተማው የትራንስፖርት ፍሰት ላይ ጫና ፈጥሯል።

- እገዳው በሁሉም ቦታ የተደረገው ልዩነት እና መድሎ ላለመፍጠር ነው፡ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በማኅበር ተደራጅተው የሚሠሩ በመሆኑ አሠራሩን ስለማሻሻል ከማኅበራቱ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ነበሩ።

ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል እገዳው በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ በመሆኑ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎቹንና ቤተሰባቸውን ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎችንም ችግር ላይ እንደጣለ መረዳት እንደተቻለ ገልጿል።

መንግሥት ሰዎች ሥራቸውን እና የመረጡትን መተዳደሪያ ያለአግባብ እንዳያጡ ማድረግን ጨምሮ የመረጡትን እና የተቀበሉትን ሥራ እንዲሠሩ የማስቻል ኃላፊነት አለበት ያለው ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 41(1) መሠረት “ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት እና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት ” ያለው መሆኑን በንዑስ-አንቀጽ 2 እንደተመለከተው ደግሞ መተዳደሪያውን፣ ሥራውን እና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው ማለቱን ጠቅሷል።

ይህ መተዳደሪያን የመምረጥ/በመረጡት ሥራ የመሰማራት መብት (the right to choose one’s livelihood/work) ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችም የተረጋገጠ መብት ነው ሲል ኮሚሽኑ አስገንዝቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ  በባጃጅ የትራንስፖርት ሥራ የተፈጠሩትን ችግሮች በተገቢው ሕጋዊ እርምጃዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በማስተዳደር እና ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ማድረግ ሲገባ በጠቅላላ ከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ከላይ ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶችን አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው ብለውታል።

በተለይ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንን እንዲሁም ሴቶች እና ሕፃናትን ታሳቢ በማድረግ እገዳውን ማንሳትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባጃጅ

• " ገደቡ ከነገ ጀምሮ ይነሳል "

• " በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል አይቻልም "


በአዲስ አበባ በባጃጅ አገልግሎት ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ጀምሮ እንደሚነሳ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ የባጃጅ አገልግሎት ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 8/2015 ጀምሮ እንደሚነሳ አስታውቋል።

የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል እንደማይችሉ ቢሮው ገልጿል።

ቢሮው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚመራበት መመሪያ መዘጋጀቱን ይፋ ማድረጉን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

@tikvagethiopia
#AddisAbaba #ባጃጅ

በአዲስ አበባ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት በሂደት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ አይቀሬ እንደሆነ ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ የባለሶስት እና አራት እግር ተሽከርካሪ ወይም ባጃጅ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች  የአሰራር ፣ የአጀረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የዲሲፒሊን ቁጥጥር አፈጻጸም መመሪያ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጎ ነበር።
                              
በውይይቱ ላይ ፦
- የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
- የትራፊክ ማናጅመንት ፣
- የትራንስፖርት ቢሮ
- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማዕከልና የክ/ከተሞች ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

በአፈፃፀም መመሪያው የባለ ሶስትና አራት እግር ተሽከርካሪ ወይም ባጃጅ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ካሁን ቀደም ሲያጋጥሙ የነበሩ የሕግ ጥሰቶችንና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል ሲባል አገልግሎት ሰጪዎቹ ፦

የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ፣

የአዲስ አበባ የሠሌዳ ቁጥር

በማህበር መደራጀት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል።

" በአዲስ አበባ፣ የከተማ አስተዳደሩን ታርጋ ለጥፈውና የአዲስ አበባ መታወቂያ ይዘው ከሚሰሩት ይልቅ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ አሽከርካሪዎች መበራከት የፀጥታ ችግር ሆነው ቆይተዋል " ተብሏል።

ይህ ደግሞ በተለይ በወንጀል ድርጊት ላይ ተሳትፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ አዳጋች እንደነበር ተገልጿል።

በዚሁ መድረክ ላይ " የባጃጅ ትራንስፖርት የከተማዋን ዘመናዊ እሳቤ የሚመጥን ስላልሆነ በሂደት ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱ የሚቋረጥ ይሆናል " ተብሏል።

" እስከዚያ ጊዜ ድረስ የባለሶስት እግር አሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ መታወቂያ፣ ታርጋ እና በማህበር መደራጀት ይኖርባቸዋል " ነው የተባለው።

አሁን ላይ በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ሰፊ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት በመኖሩ በነዚህ አካባቢ ያለው ፍላጎት በሌላ አማራጮች እስኪተካ ድረስ አገልግሎቱ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉባቸው እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ሰፈሮች ዜጎች ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን / ባጃጅ ለትራንስፖርት ይጠቀማሉ።

እጅግ በርካታ ዜጎችም በተለይ በተለይ ወጣቶች በዚሁ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ገቢ ያገኛሉ ቤተሰባቸውንም ያስተዳድራሉ።

ከዚህ ቀደም ባጃጆች በተለይ በከተማው ዳርዳር ከዋና ዋና የሚባሉ መንገዶች ወጥተው ውስጥ ለውስጥ ብቻ እንዲሰሩ መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

#AddisAbaba
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia