TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አረንጓዴ አሻራችንን በትላንትናው ዕለት አሳርፈናል ብለዋል። #ASTU


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። #አዳማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia

የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ተደረገ!

#ASTU #AASTU

የአዲስ አበበ እና አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲትዎች መግቢያ ነጥብ ዝቅ አለ!

የተማሪዎችን ፍላጎትና በተደጋጋሚ የሚነሳውን የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ይበልልን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ በማስታወቂያ የተገለጸው ለወንድ፡190 እና ለሴት፡185 ከነበረው ዝቅ ተደርጎ

ለወንድ፡ 176 እና
ለሴት፡166

የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን እያሳወቅን እስከ ነገ መስከረም 20/01/2012 ዓ.ም. ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዚህ መስክ መመደብ የምትፈልጉ የ2011ዓ.ም. የዪኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች፤ ለት/ቤታችሁ ፍላጎታችሁን በመግለጽ ምርጫችሁን ት/ቤታችሁ እንዲያስገባላችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

https://app.neaea.gov.et/

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASTU

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ዛሬ ጠዋት ለ4 ቀናት የሚቆይ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተጀምሯል። የደም ልገሳ ፕሮግራሙን ያዘጋጁት ክለብ 20/25 ከአዳማ ከተማ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ነው። ዛሬ በነበረው የደም ልገሳ ላይ በርካታ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

Via Hiwi(ቲክቫህ አዳማ-ASTU ቤተሰብ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
animation.gif
17.2 KB
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ(ASTU) የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ ዛሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማረጋገጥ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው። በዚህም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ወደ  ተቋሙ የመጡበትን ዓላማ እንዲተዉ የሚገፋፏቸውን አካላት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊነቱን ጠብቆ ለማካሄድ በከተማዋ ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጋር በመሆን የተማሪዎችን ደህንነት  በመጠበቅ  ላይ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

(ኢዜአ)

በሌላ በኩል ከቲክቫህ ቤተሰቦች...

በASTU፣ ሀረማያ፣ ጅማ(JiT)፣ መደወላቡ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቱ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ተማሪዎች ያደረባቸውን ስጋት ዛሬም እየገለፁ ይገኛሉ። ለህይወታችን ሰግተናል ያሉ ተማሪዎች በቤተ እምነት ውስጥ ተጠለልው እንደሚገኙ ገልጸዋል። መልዕክት የላኩት ተማሪዎች ጉዳዩ ይሄ ያህል እስኪከር ድረስ ምንም መፍትሄ ባለመሰጠቱ የፌደራል መንግስቱን ወቅሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዛሬ የህዳር 10/2012 ዓ/ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልት እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰባሰበ መረጃ👇
https://telegra.ph/ETH-11-20-4

(TIKVAH-ETHIOPIA)

#ድሬዳዋ #ሀረማያ #ወልዲያ #መቱ #ASTU
#መደወላቡ #ባህርዳር #ደባርቅ #ደብረታቦር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ(ASTU) ዛሬ ለሶስተኛ ጊዜ ባወጣው ማስታወቂያ የመማር ማስተማ መርሃ ግብር መቆራረጡ እንደቀጠለ እንደሆነ ገልጿል። ከሰኞ ጀምሮ ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በጥብቅ አሳስቧል። ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን በትምህርት ገበታው ላይ ያልተገኘ ተማሪ በራሱ ፍቃድ ትምህርት እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ይህን ቢልም...

መልዕክቶቻቸው "ለቲክቫህ ኢትዮጵያ" የላኩ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ተማሪዎች የሆኑ የቤተሰባችን ዓባላት በግቢው ውስጥ በበራሪ ወረቀት እየተሰራጩ የሚገኙ እንዲሁም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፉ ያሉ የማስፈራሪያ መልዕክቶች ትምህርታችንን በአግባቡ እንዳንከታተል እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ASTU

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ(ASTU) ትናንት ማታ ከለሊቱ 7 ሰዓት በተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት አምስት ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ናቸው፡፡ አጥፊዎቹን የመለየትና በቁጥጥር ስር የማዋል ስራም እየተከናወነ ይገኛል፡፡

(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia