TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀሰተኛ_ዜና

"በአባቴ ህይወት ላይ አታሟርቱ፤ አባቴ አልሞተም" - ጃጋማ ዋሚ

በኖሩበት የምድር ህይወት ፣ እያንዳንዱን ያደረጉትን ተግባር ፣ በቀን ፣ በአመተ ምህረት ፣ በሰዓት ሳያዛንፉ የሚናገሩት ጀግናዉ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የተባለዉ ዉሸት ነዉ።

እባካቹህ መረጃ ሳታረጋግጡ ሰዉን አታሳስቱ።

Via መኳንንት በርሄ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ሀሰተኛ_መረጃ

የመቐለ ጊዜያዊ ከንቲባ የነበሩት አቶ አታኽልቲ አዲስ ሹመት እንደተሰጣቸው ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰተኛ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።

አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ ፥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን አዲስ ሹመት ስለማግኘታቸው የተሰራጨው ዜና #ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል።

የቀድሞው ጊዜያዊ ከንቲባ ፥ "አሁን የመቐለ ነዋሪ ብቻ ነኝ ሲሉ" አስረድተዋል።

ምንጭ፦ www.addiszeyeb.com

@tikvahethiopia
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia
#MoSHE

የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ #ሀሰተኛ ነው አለ።

ዛሬ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ እንደተጻፈ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ነው።

ደብዳቤው “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት” የሚል አርዕስት ያለው ሲሆን ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ምደባ ማካሄዱን እንዲያቆም የሚያስጠነቅቅ ይዘት አለው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶን ለ "ኢትዮጵያ ቼክ" በሰጡት ቃል ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፥ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት የታሕሳስ ወር የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ገና መሰጠት አልተጀመረም ነበር ብለዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከካቲት 19 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው በመጋቢት ወር አጋማሽ እንደነበር አስታውሰዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ በሚያዚያ ወር የተከነወነ መሆኑ በመግለፅ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት ታሕሳስ ወር ምንም አይነት የተማሪዎች ምደባ እንዳልነበር አስረድተዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ደብዳቤውን እርሳቸው እንዳልጻፉት ገልጸዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል በታህሳስ ወር የተማሪዎችን ምደባ የተመለከተ ደብዳቤ ሊጻፍ እንደማይችል አክለዋል።

ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ማምሻው በፌስቡክ ገጹ በለጠፈው አጠር ያለ መልዕክት “ዩኒቨርስቲያችንን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ ወሬዎች አሳሳችና የውሸት መሆናቸውን እንገልጻለን” ብሏል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት "የምርጫ ወቅት እና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት" ላይ ትኩረቱት ያደረገ አጭር ገለፃ በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ይኖረናል። ገለፃው በዋነኝነት በዚህ ለሀገሪቱ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ሊፈጠር የሚችለውን ችግር በማስቀረቱ ረገድ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን። አቅራቢዎቹ : ከመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል…
Audio
AudioLab
#ሀሰተኛ_መረጃ_እና_ምርጫ2013

"የምርጫ ወቅት ላይ ስለሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና እንዴት እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንችላለን" በሚለው ጉዳይ ዛሬ በቀጥታ Voice Chat ለቲክቫህ ቤተሰቦች ገለፃ ተደርጓል/ለጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል።

ገለፃና ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ከCARD በፍቃዱ ኃይሉ ፤ ከኢትዮጵያ ቼክ ደግሞ ኤልያስ መሰረት ነበሩ።

ምናልባት በቀጥታ በVoice Chat ገለፃውን ማዳመጥ ሳትችሉ የቀራችሁ ቤተሰቦቻችን ከላይ የድምፅ ቅጂው ተያይዟል፤ አዳምጡት።

@tikvahethiopia
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ

በየምርጫ ጣቢያዎቹ ውጤት እየተለጠፈ ይገኛል፤ ነገር ግን በርካታ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው።

ውድ አባላት ይፋዊና ቦርዱ ማህተም ያላረፈባቸውን ፤ በተለም ደግሞ በዘፈቀደ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን #በጥንቃቄ እንድትከታተሉ ይሁን።

ከምርጫ በኃላ ችግር የሚፈጥረው እንዲህ አይነት ጉዳይ ስለሆነ ሰላማዊ ሂደቱ እንዲጠበቅ አስተዋጽኦ አድርጉ።

@tikvahethiopia
#Update

"በደሴ 10 በሚሆኑ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ተሞልተው ተገኙ" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

በ10ሩ የምርጫ ጣቢያዎች የተፈጠረውን ጉዳይም ዛሬ በነበራቸው መግለጫ አስረድተዋል።

በምርጫ ጣቢያ ደረጃ የውጤት አገላለፅ እንዲሁም የውጤት አመዘጋገብ በትክክለኛው መንገድ ስለመፈፁ የሚረጋገጥበት የራሱ ደረጃ አለው ይህም በስልጣና ላይ ተሰጥቷል ብለዋል።

ከእንዚህ ደረጃዎች/ሂደቶች መካከል ፦
- የመጀመሪያው በዚያ ጣቢያ ስንት ሰው ነው የሚመዘገበው ?
- በዕለቱ መጥቶ መዝገብ ላይ ፈርሞ ድምፅ የሰጡ ብዛት ስንት ናቸው ? ፊርማቸው ተቆጥሮ መመዝገብ አለበት።
- የመጡት ሰዎች ተመዝግበዋል ከተባሉት ሰዎች ቁጥራቸው መበላለጥ ስለሌለበት ይህም ይረጋገጣል።
- የደረሰው የድምፅ መስጫ ወረቀት ብዛት ስንት ነው ?
- ሳጥን ውስጥ የተገኘው ምን ያህል ነው ?
- የተበላሸ የድምፅ መስጫ ወረቀት ስንት ነው ? የሚሉት ይገኙበታል።

ደሴ የተገኙት 10 ምርጫ ጣቢያዎች ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጡ አካሄዶችን ሳይፈፅሙ ፣ ሂሳቡንም በትክክል ሳይሰሩ በመላካቸው በምርጫ ክልል ደረጃ እንደገና መታየት ስላለበት / ድምፅ ቆጠራው መደገም ስላለበት የምርጫ ክልሉ ለጊዜው ኳራንታይን አድርጎ አስቀምጦታል።

ይህ ሁኔታ ነው የማይሆን ትርጉም ተሰጥቶት #ሀሰተኛ_መረጃ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው ሲሉ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
ይህ ገፅ የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ገፅ ነው ?

ፌስቡክ ላይ ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ዓዴፓ Assimba Democratic party-ADP በሚል ስም የተከፈተ እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ #ሀሰተኛ ነው።

ከትላትን ጀምሮ ይህን ገፅ ዋቢ አድርገው የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም አንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ (ዶቼ ቨለ) መረጃዎችን ሲያጋሩ ተመልክተናል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ከመታሰራቸው ከወራት በፊት ገፁ ሀሰተኛ ስለመሆኑ አሳውቀው ነበር።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዶሪ አስገዶም "ገፁ ሀሰተኛ መሆኑን ፣ በዚሁ ሀሰተኛ ገፅ ላይ የሚወጡ መረጃዎች እና መግለጫዎች ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ)ን የማይወክሉ እንደሆነ" በተደጋጋሚ ገልፀው ነበር።

አቶ ዶሪ አስገዶም ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ በኢሮብ ወረዳ የኤርትራ ወታደሮች ወረራ እየፈጸሙ ነው በማለታቸው ሳቢያ ለእስር ስለመዳረጋቸው ነው ከፓርቲው የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው።

አቶ ዶሪ ታስረው የሚገኙት አዲስ አበባ ውስጥ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

#ሐምሌ_19 የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ይከበራል።

ከመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል) በደረሰን መልዕክት የፊታችን ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል በዓል በደመቀ መልኩ ይከበራል።

"በዓመት 2 ጊዜ ታህሳስ እና ሐምሌ 19 ብቻ" እንደሚነግስ የተገለፀልን ሲሆን የዛሬ ዓመት በኮሮና ወረርሽኝ እና በአንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት ለምዕመናን ውስን ሆኖ ነበር የተከበረው።

በዚህ ዓመት ግን ምዕመናን ራሳቸውን ጠብቀው ከተሟላ ፓርኪንግ ጋር እንዲሁም መንገዱም ስለተከፈተ መጥተው ማክበር ይችላሉ ተብሏል።

በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ገዳሙ እንደተዘጋ ተደርጎ የሚናፈሱ መረጃዎች ፍፁም #ሀሰተኛ ናቸው።

የ124 ዘመን እድሜ ያለው የመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በዳግማዊ ንጉሰ ነገሥት አፄ ምንሊክ መታነጹ ይነገራል።

አድራሻ ፦ ታላቁ ቤተመንግሥት (አንድነት ፓርክ) ጎን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም " - ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የሱዳን ጦር በድንበር አካባቢ በርካታ ወታደሮቼ የኢትዮጵያ ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ተገደሉብኝ ሲል ክስ አሰምቷል። የሱዳን ጦር ትላንት ባወጣው መግለጫ ፤ “በአል-ፋሻቃ የሚገኘውን የመኸር ምርትን ለመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሃይሎቻችን… በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች እና ሚሊሻዎች በቡድን ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ ገበሬዎችን ለማስፈራራት እና የመኸር…
" የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ እየተባለ የሚነዛው ወሬ #ሀሰተኛ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ዶ/ር ለገሰ ፥ " አሸባሪው ኃይል በተለያየ መልኩ ሱዳን ውስጥ የሚያሰለጥናቸውን ሰርጎ ገቦች በተለያየ ቦታ በተለይም በመተማ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜያት ያስገባል ፤ በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ ሰርጎ ገቦች ይገባሉ፤ በዚህ መሰረት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰርጎ ገቦች ፣ ሽፍታዎች እና አሸባሪዎች በዛ መስመር ገብተው ነበር በዛ መስመር የገባውን ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ሚሊሻ መቷቸዋል ፤ ደምስሷቸዋል " ብለዋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚነዙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ፈፅሟል የሚለው መሰረተቢስ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፥ " ቢኖረው ኖሮ የሱዳን ኃይሎች ወረው በግድ የያዙት መሬት አለ ፤ ይሄንንም በሰላማዊ ሁኔታ በውይይት እና በድርድር እንፈተለን ብሎ የተቀመጠ ነው የኢትዮጵያ መንግስት ፤ አዲስ የመጣ የተከሰተ ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን የህወሓትን ተልዕኮ ለማስፈፀም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ሽፍታዎችን ደምስሰናቸዋል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia