TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የቦይንግ ኩባንያ በዛሬው እለት የተከሰከሰውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስኤ ለማጣራት የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ #መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ኩባንያ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለፀ ሲሆን በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች #መፅናናትን ተመኝቷል፡፡ በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት #የአሜሪካን_ብሄራዊ_ትራንስፖርት የደህንነት ቦርድ አቅጣጫን ተከትሎ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ #የቴክኒክ_ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#JawarMohammed #ETHIOPIA

አቶ ጀዋር #የአሜሪካን ዜግነታቸውን ለመመለስ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊነታቸውን እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሜሪካ ዜጎቿን ከካቡል ማስወጣቷን ቀጥላለች።

የአሜሪካ ፕሬዜዳንይ ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ አሜሪካ እስካሁን ድረስ 13,000 ሰዎችን ከአፍጋኒስታን ማስወጣቷን፤ ይህ በታሪክ ትልቁ እንዲሁም አስቸጋሪው እንደሆነ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ አሜሪካ እያካሄደችው ያለው ዜጎቿን በአየር የማስወጣት ዘመቻ በታሊባን እንቅፋት እየገጠመው አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህም ከመከላከያ ኃላፊያቸው ጋር የተቃረነ ንግግር መሆኑ ጥያቄ አስነስቷል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን አርብ ዕለት ለህግ አውጪዎች እንደተናገሩት ፤ አሜሪካውያን አፍጋኒስታንን ለመልቀቅ በሚሞክሩበት ወቅት በታሊባን ታጣቂዎች እንደተደበደቡ ነው ብለው ነበር።

የእረፍት ጊዜያቸውን አቋርጠው ወደ ሥራ የተመለሱት ጆ ባይደን ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ "ወደ አገራችሁ መመለስ የሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ቤታችሁ እንመልሳችኋለን" ብለዋል።

ከአሜሪካዊያን በተጨማሪ ከ50 እስከ 65 ሺ የሚደርሱ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ አፍጋኒስታናውያንንም ለማስወጣት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ባይደን በትላንቱ መግለጫቸው ፥ ታሊባን #የአሜሪካን_ፓስፖርት የያዘ ማንኛውም ሰው ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እንዲገባ እየፈቀደ መሆኑን ጠቅሰው የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ካቡል መላክ አስፈላጊ አይሆንም ብለዋል።

#ቢቢሲ በካቡል የአሜሪካ ዜጎች ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ለመግባት እንቅፋቶች እየገጠማቸው እንደሆነ በርካታ ከካቡል የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA : የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪና ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ ከሚሰሩት መካከል የሕወሃት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ አሜሪካ መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል። አቶ ማሞ ይህን ያሉት ከአል ዓይን አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው። ኢትዮጵያ ከAGOA እንድትወጣ የሚሰሩት እንነማን እንደሆኑ…
#AGOA

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የንግድ ችሮታ (AGOA) ማስወጣታቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸውን ኋይት ሃውስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከንግድ ችሮታው እንዲትወጣ ፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ የጻፉት ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል።

አሜሪካ ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ጥልቅ ውይይቶች ተደርገው እንደነበር ገልጻለች።

ጆ ባይደን ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ጊኒ እና ማሊም ከአሜሪካ የንግድ ችሮታ (አጉአ) እንዲወጡ ደብዳቤ መጻፋቸውንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል።

ሀገራቱ ይህ የተወሰነባቸው #የአሜሪካን_ፍላጎቶች ማሟላት ባለመቻላቸው መሆኑንም አሜሪካ ገልጻለች።

@tikvahethiopia