TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከላሊበላ⬇️

"​​የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የመፍረስ አድጋ ከፊትለፊታቸው ተጋርጧል። ምክንያቱም ሸራ ለመወጠሪያ በሚል ሰበብ ከላያቸው ላይ የተቀመጠው ምሰሶ እንዱ ብቻ 3 ቶን የሚሆን ነው። እናም ከህንፃዎቹ አቅም በላይ ስለሆነ እንዲነሳ የሚል ጥያቄ ከ አካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎቹም ለመንግስት ቢ ያመለክቱም እስካሁን በመንግስት በኩል የተደረገ ምንም ነገር የለም። እናም ሁላችሁም ምዕመናን ይህንን የሀገራችንን እንዲሁም የአለምን ቅርስ ከተጋረጠበት አደጋ ለማላቀቅ እና ተገቢው እድሳት እንዲደግረ በአገኛችሁት አጋጣሚ ለሚመለከተው አካል ይድረስልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሰላ⬆️የ2011 የኢሬቻ በዓል በአሰላ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

@tsegabwolde @tikvahiopia
#ኢሬቻ2011⬆️የመልካ አቴቴ ኢሬቻ በዓል በዛሬው ዕለት ተከብሯል። የኢሬቻ በዓል በቡራዩ መልካ አቴቴ፣ በገላን ጨፌ ቱማና በሰበታ መልካ ሰበታ ነው የተከበረው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ ግጭት በተከሰተባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላለፉት 2 ቀናት በአብዛኛዎቹ #መረጋጋት የታየባቸው ቢሆንም ሆሮ ሊሙና ያሶ በተባሉት ቦታዎች ግን አሁንም የፀጥታ ሥጋት መኖሩን የምሥራቅ ወለጋ ዞን የፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ቶሎሣ ለኢቲቪ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው ያለና #ማንነቱን በግልፅ ለመለየት ያልተቻለ የተደራጀ እና የታጠቀ ኃይል ሕዝቡን ሥጋት ውስጥ ከቶታል ያሉት ኃላፊው ችግሩን ለማስቆም መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በማይናማር እየተካሄደ ባለው በሚስ ግራንድ ኢንተርናሽናል አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ሀገራችንን #ኢትዮጵያን ወክላ እየተወዳደረች ላለችው #ሳምራዊት_አዝመራው ከታች ባለው ዌብሳይት ላይ በሶስት ዘርፍ ኢትዬጵያን በመምረጥ ድምፅ ይስጡ።

Www.missgrandinternationalvote.com

ምንጭ፦ ኢዮሲያስ ምትኩ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከማህበራዊ ህይወታቸው ሳይርቁ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል የመኖሪያ አፓርታማዎች ግንባታ እቅድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ‘‘በነቃ የወጣቶች ተሳትፎ ያጋጠሙንን ፈተናዎች በማለፍ ዕድገታችንን እናስቀጥላለን’’ በሚል መሪ ቃል ዛሬ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ ወቅት እንደገለጹት የከተማዋን ነዋሪ ከማህበራዊ ህይወቱ ሳይርቅ የቤት ባለቤት ማድረግ የሚያስችል የቤት ልማት እቅድ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በቅርቡ ስራ ይጀምራል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አምስተኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ነገ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሙላቱ_ተሾመ በሚያደርጉት ንግግር በይፋ እንደሚጀምር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update ጋምቤላ⬆️

በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረውን ሁከት #ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንደሚያበረክቱ የከተማዋ ወጣቶች ተናግረዋል። በከተማይቱ ህዝባዊ ሰልፍ ተደርጓል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia