TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን ገልፀውልኛል " - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የመንግስትን እና የህወሃትን አመራሮችን ማነጋገራቸውን ካስታወቁ በኋላ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ኦባሳንጆ ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ፍልሚያውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ከመንግስትም ሆነ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህወሃት በኩል የሰላም ፍላጎቶች መኖራቸውን የገለጹት ከፍተኛ ተወካዩ ‘የሰላም መንገዱ ምን ይሁን’ የሚለው ግን ልዩነታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ መሪዎችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ሕብረቱ የጀመረውን የማሸማገል ጥረት እንዲደፉ እና ግጭቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ነገሮች እንዲቆጠብም ኦባሳንጆ ጥሪ አቅርበዋል።

ኦባሳንጆ፥ "ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ ግጭቱን የሚባብሱና ወደከፋ ደረጃ ከሚያደርሱ ንግግሮች መቆጠብ ያስፈልጋል" ብለዋል ።

ኦባሳንጆ፤ ውጊያው ከቆመ የንግግር ዕድል እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ውጊያ እየተደረገ ግን ለመነጋጋር የሚመች እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኦባሳንጆ ፥ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አመራሮችን ማግኘታቸውን በመግለጫቸው ላይ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የአፋር ክልል አመራሮችን እንደሚያገኙ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጂ ይህ የማሸማገል ስራ እንዲሳካ ቁርጠኛ እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን ፦
- #የኬንያ
- #ኡጋንዳ
- #ጅቡቲ
- #ደቡብ_ሱዳን
- #ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎችን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አስማሚ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለሁ ያሉት ኦባሳንጆ ሁለቱም ወገኖች ሰላም፣ ጸጥታና የኢትዮጵያ መረጋጋት ምኞታቸው መሆኑን እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

Credit : #Al_AIN
Pic : AU

@tikvahethiopia