TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አዳዲስ ሹመቶችን መስጠቱ ተገልጿል።

ሹመቶቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው የተሰጠው።

በዚህም ፡-

1. ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ ውበትና ልማት ቢሮ ሃላፊ
2.  አቶ ቢኒያም ምክሩ - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ
3. አቶ አብርሃም ታደሰ - የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ
4. አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን - የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
5. አቶ አደም ኑሪ - የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ
6. አቶ በላይ ደጀን - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
7. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ - የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ
8. አቶ ካሳሁን ጎንፋ - የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ
9. አቶ አያሌው መላኩ - የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና አቤቱታ ሰሚ ጉባዔ ሃላፊ
10. ወ/ሮ እናታለም መለሰ - የአዲስ አበባ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሹመታቸው በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡

ተሿሚዎቹ በምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ።

#MayorOfficeofAddisAbaba

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ #ድንገተኛ_ፍተሻ በተለምዶ #ሰይጣን_ቤት ወይም #ፒራሚድ_አዲስ እና #ባስ_አዲስ_ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ የተደረገው።

በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ፦

- ከ100 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ፣
- በርካታ መዋሰሎች፣
- ከ6 በላይ ሀሺሽ የያዙ እቃዎች እንዲሁም በወቅቱ በቦታው የነበሩ ከ68 በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን እና ወጣቱን በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ እንዲሳተፍ ሲያደርጉ የቆዩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በየአከባቢያቸው አዋኪና ከማህበረሰቡ ወግና ባሕል ያፈነገጡ አስነዋሪ ድርጊቶች ላይ ወጣቱ እንዲሳተፍ የሚያደርጉ ምሽት ቤቶችንና ግለሰቦችን በማጋለጥ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

#MayorOfficeofAddisAbaba

@tikvahethiopia
#Update

ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እንደሚገነባ ጠቁመዋል።

" እስከዛው ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን " ብለዋል።

ከንቲባዋ ፤ " በአካባቢው ያለውን ጥግግትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#MayorOfficeofAddisAbaba #Merkato #ShemaTera

@tikvahethiopia