TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የሹፌሮችድምጽ

" የታገቱትን ሊፈልግ የሚወጣ የጸጥታ ሃይል የለም ሄዱበት በተባለው መንገድ የሚገባ የለም " - ጣና የከባድ መኪና ሹፌሮች ማህበር

በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የከተማ አቋራጭ እና ሃገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች ለእገታ እና ግድያ እየተጋለጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል።

የጣና የከባድ መኪና ሹፌሮች ማህበር በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ከ200 የሚበልጡ አሽከርካሪዎች ቢገደሉም ችግሩን ለመቅረፍ ግን ምንም እንቅስቃሴ እየተደረገ አለመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ  ገልጿል።

" ሰው ታፈነ ሲባል ሰውን ያህል ነገር ታፍኖ የአካባቢው የጸጥታ ሃይል የት፣እንዴት ታፈነ የሚለውን ጠይቆ እና አነፍንፎ የሚንቀሳቀስ መንግስት አጥተናል" ሲሉ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አክለውም " መታገትህን ትናገራለህ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ይባላል የታገቱትን ሊፈልግ የሚወጣ ሃይል የለም ሄዱበት በተባለው መንገድ የሚገባ የለም " ነው ያሉት።

አጋቾች የሚደራደሩት በስልክ ነው ገንዘብም የሚገባው በባንክ ነው ያሉ ሲሆን እገታን እዚህ ደረጃ ያደረሰው መንግስት ለሚታገቱ እና ለሚገደሉ ሰዎች የሰጠው ትኩረት በማነሱ ምክንያት ነው ብለዋል።

እንደ ማህበሩ አመራር ገለጻ ህዳር አንድ ላይ አራት አሽከርካሪዎች መተሃራ እና አዋሽ ሰባት መሃል ታፍነው በታጣቂዎች ተወስደዋል።

በተደጋጋሚ የሹፌሮች መታገት እና መገደል የነበረባቸው አንደ ታች አርማጭሆ ያሉ አካባቢዎች ሚሊሻዎችን በየመንገዱ የማሰማራት እና መንገዱን የመጠበቅ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን የጠቀሱ ሲሆን በተጠቀሰው አካባቢ መሻሻል አለ ብለዋል።

" ከአይከል -ጭልጋ- ገንዳውሃ " ያለው መንገድ ግን አሁንም ለሹፌሮች እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ከመንግሥት ውጪ የሆነ እና በየመንገዱ የሚሰበሰብ እስከ 20 ሺ ብር የሚደርስ ህገወጥ ቀረጥ ሹፌሮችን እያማረረ ነው ብለውናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia