TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የውሃ_ዋጋ 📈

🔹" በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም " - ውሃ አምራች ኩባንያዎች

🔹" ከአከፋፋዮች የሚሸጥልን ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል " - ነጋዴዎች

🔹" የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲቀርብ ጭማሪ ተደርጓል " - አከፋፋዮች

▪️ የታሸገ ውሃ አከፋፋዮች ምን ያህል ዋጋ ነው የጨመራሁት ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ዋጋውን ከመናገር ተቆጥበዋል።

በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ከሰሞኑ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።

በታሸጉ የፕላስቲክ ጠርሙስ ዉሃ ምርቶች ላይ የተደረገዉ የዋጋ ጭማሪ ከጥሬ ዕቃ መወደድ ጋር የተያያዘ መሆኑ አምራቾች ሲገልፁ በአንድ በኩል ደግሞ ከአከፋፋዮች የምንረከበዉ ምርቶች ላይ ጭማሪ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ነጋዴዎች ተናግረዋል።

በተለይ ከሶስት ሳምንታት ወዲህ በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሲሸጡ ከነበረበት ዋጋ ላይ በእያንዳንዱ ምርት የ5 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ካፒታል ጋዜጣ አደረኩት ያለውን ቅኝት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

የዋጋዉን ጭማሪ አስመልክቶ ማን ምን አለ ?

#አምራች_ኩባንያዎች ፦ ጭማሪው ከጥሬ እቃ መወደድ እና በቅንጦት እቃዎች ላይ በሚጣለዉ ኤክሳይስ ታክስ ሳቢያ መሆኑን አንስተዋል። ቢሆንም ግን በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም ሲሉ አሳውቀዋል።

" በሁሉም ምርቶች ላይ ከአንድ ብር በላይ ጭማሪ አልተደረገበትም " የሚሉት የዉሃ አምራች ፋብሪካዎቹ ነገር ግን በገበያ ላይ የሚሸጥበት ዋጋዉ ከእነርሱ እዉቅና ዉጪ መሆኑን አስረድተዋል።

#ነጋዴዎች ፦ ከዚህ ቀደም ሲረከቡበት የነበረዉ የዋጋ ተመን ላይ ጭማሪ መደረጉን ገልፀዉ ከአከፋፋዮች የሚሸጥላቸዉ ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።

#አከፋፋዮች ፦ የዋጋዉ ጭማሪ ከፋብሪካዎቹ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲያቀርብ ጭማሪ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል። ምን ያህል እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ የዉሃ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርዕድ ፤ የዋጋዉ መጨመር መኖሩን አረጋግጠዋል።

ለዚህ በምክንያትነት ያነሱት " ፕላስቲክ ጠርሙሶቹ የሚሰሩት ከነዳጅ ተረፈ ምርት በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች በጦርነቱ ሳቢያ ሊጨምር በመቻሉ ፣ ኤክሳይስ ታክስ ከፍተኛ መሆን ፣ ለአምራቾቹ ለስራ ማስኬጃ የብድር እጥረት መኖር ዋነኛዎቹ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

በገበያ ላይ ያለዉ የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበዉ ምላሻቸዉን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

Credit - #CAPITAL #ካፒታል_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነጋዴዎች #ደረሰኝ #መርካቶ

" ደረሰኝ መቆረጥ አለበት በዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለውም " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በተለይ በግዙፉ የገበያ ማዕከል ' መርካቶ ' በንግድ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ነጋዴዎች ሱቅ የመዝጋትና ስራ የማቆም እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ሰሞነኛውን የመርካቶ ገበያ ሁኔታ በተመለከተም ነጋዴዎቹ ከከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተቀምጠው ነበር።

በውይይቱ በነጋዴዎቹ በኩል በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው ነበር። ለተነሱት ጥያቄዎች የመንግሥት አካላት ምላሽ ሰጥተዋል።

ነጋዴዎች ሃሳባቸው ፣ ጥያቄያቸው፣ ቅሬታቸው ምንድነው ?

➡️ ደረሰኝ መቁረጥ ፣ ግብር መክፈል ለሀገር ወሳኝ ፤ ለራስም ይጠቅማል። ግን አከፋፈሉ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

➡️ እኛ ስንገበያይ ደረሰኝ እናገኛለን ወይ ? አንዳንድ ምርት የሚነሳው ከገበሬ ነው። ከገበሬ ነጋዴ ይሰበስባል ይከፍላል፣ ተረካቢው ይረከባል ይከፍላል፣ ተጭኖ ይመጣል እኛ እንረከባለን ይሄ ሁሉ ይከፍላል ብዙ ነገር ነው ያለው። የቆረጠው ይቆርጥልናል የሌለውን ንግድ ፍቃድ እናያይዛለን። እንዲህ ስንሰራ ነው የቆየነው።

➡️ ሁሉም እየመጣ ባለድርሻ ነኝ ይላል። መርካቶ እንደምንታመስ ያውቃል ሌባው ይገባና " ሄደህ 100 ሺህ ብር ከምትቀጣ ለኔ ይሄን ስጠኝ " ይላል።

➡️ እቃው በደላላ ነው የሚመጣው ፤ ድሮ አስመጪ በእያንዳንዱ ሱቅ ሄዶ እቃ ይበትን ነበር አሁን ግን አስመጪው ለደላላ፣ ለቤተሰብ ፣ ለዘመዱ ፣ ለጎረቤት፣ ለጓደኛ ነው የሚሰጠው። እቃው ይመጣና በተለያየ መጋዘን ይቅመጣል ከዛ በስልክ ነው ልውውጥ የሚደረገው ነጋዴው ደላላውን ' ደረሰኝ ስጠኝ ' ካለው ነገ እቃ አይሰጥም።

➡️ ቁጥጥር እየተባሉ የሚመደቡ ሰዎች ባጅ የላቸው፣ ምናቸውም አይታውቅ፣ ሱቅ የሚገቡት እንደ ሌባ 3 እና 2 እየሆኑ ነው ስለዚህ ህጋዊ ይሁኑ ህገወጥ ምናቸው ይለያል ?

➡️ ባልተማከለ ሲስተም ውስጥ ነው ያለነው። ደረሰኝ አልቆረጣችሁም በሚል መቶ ብር አትርፈን 100 ሺህ ብር ነው የምንጠየቀው።

➡️ እስቲ ኢንዱስትሪውን ተቆጣጠሩ ደረሰኝ ቼክ ይደረግ የሚወጣው አንደርኢንቮይስ ከሆነ በምን አግባብ ነው ነጋዴው የሚጠየቀው ?

➡️ " ደረሰኝ ቁረጡ ደረሰኝ ቁረጡ " ሲባል ሌላ ነገር ነው የሚመስለው ደረሰኝ ይዞት የሚመጣው ገንዘብ ነው። መጀመሪያ የንግድ ስርዓቱ መስተካከል አለበት።

➡️ ለ100 ሺህ ብር ቅጣት በዚህ ፍጥነት ከተሰራ ነጋዴውን ለማገዝ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠቱን ዕድሎች ተፈጻሚ ለማድረግ ለምን አልተቻለም ?

➡️ አሰራሩ እኮ ብዙ ነው። አልታየም። እንደ ከተማ አንድም አስመጪ የለም። አስመጪዎቹ ' መርካቶ መጥተን አንሸጥም ጅግጅጋ መጥታችሁ ግዙ ' ይሉናል። በደረሰኝ ስንት ስቃይ ነው ያለው። እዛ ተኪዶ ነው ሚገዛው ? እሺ እዚህ ስናመጣ ገቢዎች ላይ ብዙ ነገር አለ ፤ ደረሠኝ ይጥላሉ፣ ' አንቀበልም ' ይላሉ የት እንሂድ ?

➡️ አሰራሩ ላይ ትልቅ ችግር አለ።

➡️ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ አስመጪዎች ደረሰኝ ይሰጣሉ ወይ ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።


ለነጋዴዎች ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ምን መለሱ ?

🔴 የገቢዎች የቁጥጥር ሰራተኞችን በተመለከተ መታወቂያ አላቸው፣ 3 እና 4 ሆነው ነው የሚገቡት። መታወቂያ የሌለው ካለ ህገወጥ አጭበርባሪ ነው ተከላከሉት።

🔴 " የገቢዎች ሰራተኛ ነን " ብለው ሲያጭበረብሩ የተያዙ ሰዎች አሉ።

🔴 ለገቢዎች ሰራተኞች መታወቂያ ተሰጥቷል። መታወቂያ ማሳየት አለባቸው። እናተም ጠይቋቸው።

🔴 ደረሰኝ ላለመቁረጥ የሚሰጡትን ምክንያቶች በጋር እየተነጋገርን እንፈታለን እንጂ ደረሰኝ መቁረጥ እንዲቆምላችሁ የምትጠይቁትን ጥያቄ መንግስት መመለስ አይችልም። ይሄን በግልጽ እወቁት።

🔴 በገቢዎች ውስጥ ያሉ ችግሮች ይታወቃሉ መፈታት አለባቸው። ከብልሹ አሰራር፣ ከሌብነት ጋር በተያያዘ የተነሱ ችግሮች ይታረማሉ።

🔴 ቫትን በተመለከተ በአዲሱ አሰራር 7 ሺህ ብር ነው የቀን ግምቱ የተቀመጠው። ቀደም ሲል ቫት የነበረ ወደ ታች ሊወርድ አይችልም። በቀን 7 ሺህ ብር የሚሸጥ ሰው ምን ያክል ነው የሚለውን እናተው ታውቃላችሁ። ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው ቫት ውስጥ መግባት እያለበት ቫት ውስጥ ያልገባው ነጋዴ በተለይ መርካቶ እሱ ባለመግባቱ በሚሸጠው እቃ ላይ የዋጋ ልዩነት እየመጣ ስለሆነ ቫት ውስጥ መግባት ያለበትን ቫት ውስጥ እያስገባን ነው።

🔴 ቫት ውስጥ የነበረ ነጋዴ ልወርድ ይገባል ብሎ ተጨባጭ ማስረጃ ካቀረበ ይታያል። አሁን ባለው የዋጋ ንረት እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እንጂ እላይ የነበረው ወደ ታች አይወርድም።

🔴 የቁጥጥር ስርዓቱ እየጠበቀ ነው የሚሄደው።

🔴 እኛ ስለትላንቱ አለነሳንም አሁን ግን መርካቶ የሚደርገው ግብይት በደረሰኝ እና በደረሰኝ ብቻ መሆን አለበት። ይህን የሚያደርገውን ነጋዴ እንደግፋለን።

🔴 ነጋዴው በህጋዊ መንገድ ይጠቀም አልን እንጂ ነጋዴውን የሚያስቀይም ፣ የሚያሳድድ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈልግ አካል የለም።

🔴 መርካቶ የሚደረገው እንቅስቃሴ በክልል ጥያቄ ያስነሳል። መረካቶ ደረሰኝ ስለማይቆረጥ የንግዱ ማህበረሰብ ክልል ሄዶ ሲነግድ ደረሰኝ አቅርቡ ሲባል " ያለ ደረሰኝ ነው የገዛነው እዛ ደረሰኝ አልተቆረጠም " የሚሉ አሉ።

🔴 የዚህ አመት እቅዳችን ግዙፍ የሆነ ገቢ ለመሰብሰብ አቅደናል። ይህን የምናደርገው የታክስ ቤዛችንን በማስፋት፣ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ በመቀየር ነው።

🔴 ኢ-መደበኛ እናሳድዳለን አላልንም ግን ወደ መደበኛ ይግባ እያልን ነው።

🔴 ብዙዎቻችሁ (
ነጋዴዎች) ያነሳችሁት ጥያቄ ደረሰኝ እንዳይቆረጥ የሚጠይቅ ዝንባሌ አለው። " ደረሰኝ አያስፈልግም " አትሉም ግን ጅምላውን፣ አከፋፋዩን ፣ አምራቹን ቅድሚያ ስጡ ነው የምትሉት። ጅምላውም ላይ፣ አከፋፋዩም ላይ ፣ አምራቹም ላይ እንሰራለን ቸርቻሪም ላይ እንደዛው ይሰራል። ሁሉም ደረሰኝ መቁረጥ አለበት።

🔴 ደረሰኝ ለመቁረጥ የማይስችል ሁኔታ ካለ ማስረዳት ነው እንጂ " ደረሰኝ አንቆርጥ " የሚል እሳቤ ተቀባይነት የለውም።

🔴 በደረሰኝ መቆረጥ አለበት ምንም አይነት ድርድር የለውም በዚህ ጉዳይ። እኛ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ እናስገባለን።

🔴 አቤቱታ ካላችሁ በማንኛውም ጊዜ አቅርቡ። ገቢዎች አካባቢ ያለውን ነገርም እንፈትሻለን።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia