TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Semera : በአፋር ክልል መዲና ሰመራ በአሁን ሰዓት በርካቶች የተገኙበት የውይይት መድረክ እየተካሄደ መሆኑን አፋር ማስ ሚዲያ ዘግቧል።

ውይይቱ #በወቅታዊ_ጉዳይ ዙሪያ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የአፋር ክልል ወጣቶች ፣ ሴቶች እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች ተካፋይ መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 23 የመወያያ አጀንዳዎችን አጽድቆ በመወያየት ልዩልዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ጀምሯል። ዓመታዊው የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በጸሎት ከተጀመረ በኋላ በትላንትናው ዕለት በጠዋቱ መርሐ ግብር…
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን ትላንት ግንቦት 18፣ 17 እና 16 በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

በትላንት የጉባኤው ውሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ አባቶች ያስተላለፉትን መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶበታል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ወቅታዊውን ችግር ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሰጧቸውን መግለጫዎች መመልከቱን ቃላቸውንም ከመገናኛ ብዙኃን ማድመጡ ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጉዳዩ የሃይማኖትና የቀኖና ልዩነት ሳይሆን #የፖለቲካ_ችግር መሆኑን በመረዳት ሰፊ ውይይት ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ሌላው ጉባኤው የሃይማኖት ህጸጽ ተገኝቶባቸው ከቤተክርስቲያንና ምእመናን አንድነት በውግዘት የተለዩ ግለሰቦች ያቀረቡትን የይቅርታ ደብዳቤተመልክቶታል፡፡ በዚህም ምልዓተ ጉባኤው ይቅርታ ጠያቂዎቹ በቃል የተናገሩትን በመጽሐፍ የጻፉትን በተግባር ያደረጉትን የሊቃውንት ጉባኤ መርምሮ ለምልአተ ጉባኤው እንዲያቀርብ ወስኗል፡፡

በሰሜን አሜሪካና በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱ ችግሮች ላይ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን በተጨማሪ በቤተክርስቲያኗ የልማት ሥራ በጀት በሚያስፈልጋቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይት አድርጓል። ጉባኤው በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕክምና ዙርያም ውይይት አድርጓል፡፡

በግንቦት 17 ውሎው በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ልዩ ልዩ አጀንዳዎችን ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ጉባኤው በግንቦት 16 ውሎ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የአ/አ ሀገረ ስብከት አገልጋዮች ያቀረቡትን አቤቱታ ተመልክቷል።

የብፁዓን አባቶች ምደባ ተከናውኗል እንዲሁም #በወቅታዊ ጉዳይ #ለመንግሥት በሚላክ ደብዳቤ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል - telegra.ph/EOTC-TV-05-27-2

@tikvahethiopia
#Update

ጠቅላይ ምክር ቤቱ #በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ጉባዔ ተቀምጧል። 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

አስቸኳይ ጉባዔው በዑማ ሆቴል እየተካሄደ  ሲሆን መርሀ ግብሩን በቁርዓን የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኻጢብ በሆኑት በሼይኽ  ጧሐ ሙሀመድ ሐሩን መከፈቱ ተገልጿል።

የጠቅላላ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህንን ጉባዔ ስናካሂድ በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶች  የፈረሱበት የመስጂዶችን ፈረሳ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች ዉስጥ መስዋት የሆነበት ጊዜ ነው ብለዋል።

" መስጂዶች የአሏህ ቤቶች ናቸው። ይህ ክስተንን ከሚመለከተው  አካል ጋር ለመመካከር የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል " ብለዋል።

" ሙስሊሞች  የሀገር የሰላም ዘብ ናቸው " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " በሸገር ከተማ እየፈረሱ ያሉትን መስጂዶች ጉዳይ በሚመለከት  ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ መቅረቡን አስታውሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ ነገሮችን ወዳልተፈለገ መልኩ በሚወስዱ ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ የሚፅፉ  አንዳንድ  አካላትን ከተግባራቸው  እንዲቆጠቡ  አሳስበዋል።

" በመንግስት ዉስጥ ሆነዉ መንግስትና ሕዝብን የሚያጋጩ አካላት በሕገ ተጠያቂ መሆንን ይኖርባቸዋል "ም ብለዋል።

በትላንትናው  ዕለት  በሸገር ከተማ በ " ሕገ ወጥ " ስም የፈረሱ መስጂዶችን  ለመቃወም ወጥተው መስዋዕት የሆኑ  ወንድሞች አሏህ ጀነተል ፍርዶስ እንዲወፍቃቸው ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናት እንዲሰጣቸው ጉዳት የደረሰባው ወገኖቻችን ከደረሰባቸው ጉዳት አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ፕሬዜዳንቱ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በጉባዔው የኦሮሚያና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ሪፖርታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#EOTC

ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳወቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫው በምን ጉዳይ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ባይገለፅም #በወቅታዊ_ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነ ተነግሯል።

ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ለሚሰጠው መግለጫ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ላልሆኑና በቤተክርስቲያኗ ህዝብ ግንኙነት ለተመዘገቡ መገናኛ ብዙሃን በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

@tikvahethiopia