TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሰኔ 16ቱ ጥቃት⬇️

በሰኔ 16ቱ የቦምብ #ፍንዳታ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዢ #ተስፋዬ_ኡርጌ ፖሊስ በቢሮው አገኘሁት ያለወን #ቦምብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀበትን ምክንያትና የተጠርጣሪውን አስተያየት አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስ ምርመራችንን አጠናቀን ለፌዴራል አቃቢ ህግ ያስረከብን ቢሆንም አቃቢ ህግ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቢሮ ውስጥ ያገኘነውን ቦንብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር በቴክኒክ ለማመሳከር ተጨማሪ ማስረጃ ይቅረብልኝ ማለቱን ተከትሎ ለፌዴራል ፖሊስ ፈንጅ አምካኝ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ደብዳቤ ልከናል ሲል አብራርቷል።

ይህንን የቴክኒክ ምርመራ ምላሽ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል።

ጉዳዩ ያለ አግባብ እየተራዘመ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩላቸው ፍርድቤቱ አጭር ቀጠሮ ሰጥቶ ለመጨረሻ ትዛዝ ይስጥልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

ፍርድቤቱም በተጠየቀው የጊዜ ገደብ የቴክኒክ ምርመራው ለምን #አልተጠናቀቀም የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፥ ፖሊስም ደብዳቤ ልከን ምላሽ ስላልተሰጠ እየጠበቅን ነው ሲል አብራርቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎትም ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራውን ይዞ እንዲቀርብ ለተጨማሪ ስምንት ቀን ቀጠሮ በመስጠት ለጥቅምት አራት(4) ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ሞቃዲሾ በተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የቦምብ #ፍንዳታ የሰው ሕይወት አለፈ።

ፎቶ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በቻይና አንድ የኬሚካል ፋብሪካ ላይ በደረሰ #ፍንዳታ 22 ሰዎች ሞቱ
በቻይና በኬሚካል ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ 22 ሰዎች ሲሞቱ 22 የሚሆኑት ጉዳት ተርሶባቸዋል።

ፍንዳታው የተከሰተው በቻይና ሰሜናዊ የሂቤ ግዛት በሚገኝ ስፍራ ውስጥ ሲሆን በዚሁ አደጋ ሀምሳ የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፡፡

በኬሚካል ፍንዳታው በአካባቢው ዓየር ላይ የጠቆረ ጭስ እና ነበልባል በማስከተል ለብክለት መንስኤ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

እንደ ሀገሪቱ መንግስት ባለስልጣናት ገለፃ 50 ያህል የእሳት አደጋ መከላከያ መኪኖች በማሰማራት ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ 

የሀገሪቱ የዜና አውታር እንደዘገበው ፍንዳታው ነኬቢ የሻንዩ ኬሚካል ኢንዱስትሪ እኩለ ለሊት ላይ መከሰቱን ጠቁማል፡፡

ከቤጂንግ ሰሜን ምዕራብ 156 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ጂንግጂካኩ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 የሚካሄደውን ኦሎምፒክ ውድድር ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ እንደነበረችም ነው የተጠቆመው፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም ነው የአካባቢው ባለስልጣናት ያስታወቁት፡፡

ቻይና ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከፍተኛ እድገት ካዝመዘገቡ ሀገራት ተርታ የምትመደብ ሲሆን በማእድን ማውጫዎች፣ በኢንዱስትሪና ፋብሪካዎቿ አካባቢ ያለውን ደህንነት ሁኔታ የበለጠ ለማሻሻል እየሰራች መሆጓንም ነው የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተናገሩት፡፡

በ2015 ነሀሴ ወር በቲያንጂ ወደብ ከተማ የኬሚካል መጋዘን ፍንዳታ ተከስቶ 165 ሰዎች መሞታቸው ሚታውስ ነው ሲል አልጀዚራ በድረገጹ አስነብቧል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ(ena)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በአንድ ዳቦ መጋገሪያ ቤት ላይ በተፈጠረ #ፍንዳታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ገደማ በተፈጠረው ፍንዳታ ከ50 በላይ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን 12ቱ የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሑበርት የተባለው የዳቦ መጋገሪያ ፍንዳታው በተከሰተበት ቅፅበት ክፍት እንዳልነበር የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል። ፍንዳው በተከሰተበት ወቅት ጋዝ ከዳቦ መጋገሪያው እየወጣ ነው የሚል ጥቆማ የደረሳቸው የእሳት አደጋ ሰራተኞች መፍትሔ ለመፈለግ ወደ ቦታው በመጓዝ ላይ ነበሩ። አደጋው ሲከሰት ቢጫ ለባሾቹ ተቃዋሚዎች መንግሥትን ለመተቸት አደባባይ ወጥተው ነበር።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia