TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች‼️

🔹የተለያዩ መረጃዎች በግቢያችሁ ውስጥ ሲሰራጩ ስለመረጃው ትክክለኝነት በደንብ አረጋግጡ። ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ ሀገሪቷን ለመበታተን እየሞከሩ ያሉ አካላት አሉ።

ሁሌም ጠያቂ እና ምክንያታዊ ሁኑ ከስሜታዊነት ውጡ እና ስለሰማችሁት ነገር በአግባቡ ጠይቁ፦

.ሴት ተደፈረች ስትባሉ (ማን የምትባል?? ስሟ ማነው?? የምን ተማሪ ናት?? ጓደኞቿ እነማን ናቸው?? የት ዶርም ነው የምትኖረው?? ቤተሰቦቿ ሰምተዋል?? ...)

.በሌሎች ጉዳይም ብዙ ጠይቁ። ተባራሪ ወሬ ከምትሰሙ የግቢውን አስተዳደር ለመጠየቅ ሞክሩ። ፕሬዘዳንቱን መጠየቅ ካለባችሁም ወደኃላ እንዳትሉ።

🔹ለታናናሾቻችሁ ትምህርት ሰጥታችሁ የምታልፉት መልካም እና ቀና አስተሳሰብ ሲኖራችሁ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በያላችሁበት ዘውትር ስለሰላም ምንነት አስቡ።

🔹በፍፁም የግለሰቦችን ፀብ ወደቡድን እንዲቀየር አትደግፉ። በእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችንም ለመንግስት አሳልፋችሁ ስጡ። ማንም ከህግ በላይ ሆኖ መኖር አይችልምና።

🔹የሰው ልጅ ሲቸገር፣ ሲጎዳ፣ ሲደበደብ ስታዩ የምን #ብሄር ተወላጅ ነው? የሚለውን ጥያቄ ትታችሁ ሰው ክቡር ነው በማለት አጥፊውን ለመንግስት አሳልፋችሁ ስጡ። የሰውን ስቃይ በብሄር #እየከፈላችሁ የምትወዷት ሀገራችሁን ቁልቁል እንድትጓዝ በፍፁም አትፍቀዱ።

🔹ከፌስቡክ ሀሰተኛ ወሬዎች በቻላችሁት መጠን ራቁ። በፌስቡክ የሚሰራጩ መረጃዎችን እንደወረደ አትቀበሉ። የማያጋጩ የሚመስሉ ነገር ግን ሰዎችን ለግጭት የሚቀሰቅሱ መረጃዎችን ሼር ከማድረግ ተቆጠቡ።

🔹በፍፁም ታዋቂ ግለሰቦችን እንደፈጣሪ አትከተሉ። ግለሰቦቹን እና ሰፊውን ህዝብ ለዩ። ግለሰብ እና ብሄር ለዩ‼️ ግለሰብ ሲያጠፋ ብሄር አጠፋ ከሚል ዝቅተኛ አመለካከት ውጡ።

🔹ዘውትር ስለፍቅር አስቡ፤ ስለሰላም ተነጋገሩ! ሰላም ሲጠፋ የሚደርሰውን የከፋ ጉዳት ዘውትር ከማሰብ ወደኃላ እንዳትሉ።

🔹በህይወት ዘመናችሁ ሁሉ በፍፁም በሰዎች እንዳትነዱ። በመንጋ እንዳታስቡ።

🔹በእምነታችሁ ፅኑ የትኛውም ሀይማኖት ሰዎችን ስለማይከፍል በሀይማኖታችሁ በርቱ! ፈጣሪን ሁሌም ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር እንዲሰጠን ተማፀኑ። እውነተኛ ሰው ሁኑ! ጥዋት ቤተክርስቲያን ከሰዓት ደግሞ እርስ በእርስ ለመጋጨት ሰው ለመጉዳት ከመምከር ተቆጠቡ። መስጂድ ሄዳችሁ አላህ ማስተዋልን ብቻ እንዲሰጣችሁ ተማፀኑ! ሀይማኖት ካላችሁ ስልሰው ክቡርነት ትረዳላችሁ እና በየሀይማኖታችሁ ፅኑ! ተዋደዱ!!

በመጨረሻም፦ ኢትዮጵያን ጠብቋት! ድህነቷን ተመልከቱላት፤ ሳይበላ የሚያድረውን እዩላት፤ ተምራችሁ ወጥታችሁ በቻላችሁት መጠን ሀገራችሁን አገልግሉ።

ዩኒቨርሲቲዎች፦

🔹በዚህ በሰለጠነ ዘመን ኃላቀር አትሁኑ። ፌስቡክ ላይ ወሬ ሲወራ ጉዳዩን በአስቸኳይ አጣርታችሁ ከቻላችሁ በፌስቡክ ካልቻላችሁ በወረቀት ለተማሪው ግለፁ።

🔹ችግር ከደረሰ በኃላ ተማሪ ማወያየት ጥቅም አልባ ነውና በየትምህርት ክፍሉ ስለአንድነት እና ሰላም ውይይት እንዲደረግ አድርጉ።

🔹የተማሪ ህብረት ስራችሁን በአግባቡ ስሩ። በየዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያላችሁ ክበባት ከወሬ ይልቅ በስራ ተጠመዱ።

🔹ጥበቃዎች ስለፈጠራችሁ ተማሪዎን ከፋፍሎ ከማየት ተቆጠቡ። የአካባቢው ልጅ ነው እያሉ ሌሎችን ጥሩ ባልሆነ መልክ ማየቱን አቁሙ። ሀላፊነታችሁን የማትወጡ ከሆነም ስራውን ልቀቁት ምክንያቱም አሁን ኢትዮጵያ የሚሰራላት ሰው ያስፈልጋታል።

🔹ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪውን የሚያቀራርቡ ዝግጅቶች ቢኖሩ መልካም ነው!!

🔹ለሁሉም ተማሪ በቂ ጥበቃ እና ከለላ ሊደረግለት ይገባል።

ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahthiopia