TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰላም፣ አንድነት፣ እኩልነት፣ መተባበር፣ ተስፋ፣ ፍትህ፣ ብልፅግና፣ መዋደድ፣ መቻቻል እና ይቅር ባይነት በእናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ሰፍኖ ማየት የሁል ጊዜ ምኞቴ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም! ደም የፈሰሰበት አጥንት የተከሰከሰበት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን ለዘላለም ከፍ ብሎ ይውለብለብ!

ቲክቫህ ማለት ተስፋ ማለት ነው! በእናታችን ተስፋ አንቆርጥም!

#ቲክቫህ #ተስፋ #አንድነት #ሰላም #ኢትዮጵያዊነት #ፍትህ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጊዜው የለውጥ ነው! እንደ ኢትዮጵያ የምናስብበት ወቅት ነው። እኔ በበኩሌ ወደ ክልል የማወርደው ጉዳይ የለኝም። ስንት አመት ወደኋላ እንጓዛለን?? መሬት የፈጣሪ ነው። እኔ ባለ ክልል አይደለሁም የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ የኔ ነው።

ኦሮሚያ የኔ ናት! ሲዳማ የኔ ናት! ሀረሪ የኔ ናት! ትግራይ የኔ ናት! አማራ የኔ ናት! ወላይታ የኔ ናት!

የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ የኔ ነው!
.
.
.
ምክንያቱም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ!

አንተስ? አንቺስ? እናተስ?

#ኢትዮጵያዊነት_ይፋፋም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ እና #ኢትዮጵያዊነት ፍጹም መስፈሪያ የሌላቸው፣ ተነግሮና ተጽፎ የማያልቅ፣ ከአንገት ሳይሆን ከአንጀት የሚወደድና የሚያኮራ ስጦታችን ነው። ኢትዮጵያዊነት አልፋና ኦሜጋ ነው!!!

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ባህር ዳር⬇️

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋር ሙሃመድ በባሕር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ተገኝቶ ከወጣቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

• በራሳችን መፋቀድ በዚህ ፍጥነት ተቀራርበን በመስራታችን መሰረት ለሆኑ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ታላቅ ምስጋና አለኝ።

• ለውጡን እውን ለማድረግ ተቀራርበን መስራት ይስፈልጋል። ለዚህም ነው ለለውጡ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉ ህዝቦች ጋር ለመወያየት የመጣሁት ።

• ባለፉት ዓመታት አማራ እና ኦሮሚያን ለመከፋፈል እሳት እና ጭድ ያቀበሉን ሙተንም ቢሆን አሁን የምንፈልገው #ኢትዮጵያዊነት ላይ ደርሰናል።

• የሁለቱ ህዝቦች መቀራረብ እንደ አባት እና ልጅ ነው። ምሁራን እና አክቲቭስቶች ህዝቡን ለማቀራረብ መስራት የሚያስፍገን ጊዜ ነው።

©AMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ላደረግነው ሹመት መስፈርቱ ብቃትና #ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው" የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊ #ማንነት ድሮ የነበረ አሁንም ያለ ወደፊትም የሚኖር ነው። #ኢትዮጵያዊነት ደም ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️በነገው እለት አዲስ አበባ የሚገባውን የኦነግ አመራር ለመቀበል ከምሽት ጀምሮ አብዮት አደባባይ የሚገኙት #ቄሮዎች ምግብና መጠጥ እንዳላገኙ መገለጹን ተከትሎ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከላይ በምስሉ በምትመለከቱት መልኩ ዳቦና ውኃ ይዘው እየሄዱ ይገኛሉ። #ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው፤ ሌሎችም የከተማችን ወጣቶች አብዮት ለሚገኙት ወገኖቻችን እንድረስላቸው።

©ኤርሚያስ ቶኩማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2011 እንኳን ለ2011 የኢሬቻ በአል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
Baga Ayyaana Irreechaa 2011'n isiin ga'e baga geessan.

#ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
#ኢሬቻ የኔም ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀረር🔝

"ፀግሽ ዛሬ ሀረር ፈዲስ የሚባል አካባቢ የስላሴ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ የሙስሊም አባቶች ተገኝተው ነበር። #ኢትዮጵያዊነት" ሶል ከሀረር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ለመጀመሪያ ጊዜ "የኢትዮጵያ ቀን" በአደስ አበባ ከተማ ሊከበር ነው። ቀኑ ህዳር 27 በርካታ ሰዎች በተገኙበት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ዝግጅት ላይ እውቅ እና ታዋቂ አርቲስቶች ስራቸውን ያቀርባሉ። ሀሙስ ህዳር 27 በኢትዮጵያ የባህላዊ ልብሶች እና ባህላዊ ስርዓቶች #ኢትዮጵያዊነት ደምቆ ይውላል። ይህን ዝግጅት ያዘጋጀው በመዲናይቱ ትልቅቅ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው Jorka Event Oranizer ከፈታ ሾው ጋር በመተባበር መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ከሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ጋር ተወያዩ።

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በውይይታቸው ለሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እንደተናገሩት #ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ነው ብለዋል።

የከፍታችን ዋና ምሰሶው ፍቅር ሲሆን፥ ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በመተሳሰብ እና በመፈቃቀድ ከፍታቸውን ጠብቀው በጋራ የሚኖሩባትና በምሳሌነትም የምትጠቀስ ከተማ ነች ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ይህን አረዓያነት የማስቀጠል ኃላፊነት እንደለባቸውም አሳስበዋል።

ወጣቱ ትውልድ ተራራ ለመውጣት ብሎም አስፈለጊ ሆኖ ሲገኝ መናድ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ከፍታውን ሲጠብቅ ብቻ ነውም ብለዋል።

አልፎ አልፎ ከዚህ ከፍታችን የሚያወርዱ ትርክቶች ተከትሎ የሚፈጠሩ ችግሮች ለችግር የሚዳርጉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ደግሞ አብሮነት፣ ፍቅር መተሳሰብ፣ መፈቃቀድ መሆኑን ነው ያመላከቱት።

አባቶቻችን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር በማስከበር የተዋደቁት የኢትዮጵያን ከፍታ ለዚህ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ጉዞ ዓድዋ 6 ተጀመረ!! ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ የዘንድሮ ጉዞ መነሻ ተደርጋ ተመርጣለች።

"ፍቅር ለኢትዮጵያ" የሚል መርሕ የያዘው የዘንድሮ የእግር ጉዞ መነሻውን ከሀረር ከተማ በማድረግ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን በመቀላቀል የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ ይጠናቀቃል።

በትናትናው ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተካሔደው የመሸኛ ስነሥርዓት ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ባደረጉት ንግግር "ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን ህብረት ያታየበት ሁላችንም የምንኮራበት ድላችን መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚዘጋጀውን የጉዞ ዓድዋ እንቅስቃሴ የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚያግዝ አረጋግጠው የዘንድሮው 123ኛ የዓድዋ ድል በዓል አከባበር መጀመሩን በይፋ አብስረው፤ ለተጓዦች መልካም መንገድ ተመኝተዋል።

በታላቁ የዓድዋ ጦርነት ወቅት የምስራቅ ኢትዮጵያን ጦር የመሩት የቀዳሚው ጦር አዝማች ልዑል ራስ መኮንን ከተነሱበት የሐረር ከተማ በ5 ተጓዦች የተጀመረው የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ በተለያዩ ደማቅ ሥነስርዓቶች ለመካሔድ በዛሬው እለት ታህሳስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለጉዞ ዓድዋ አዘጋጆች በስልክ እንዳረጋገጡት የከተማ አስተዳደሩ ከሀረር የተነሱ ተጓዦችን ተቀብሎ በመሸኘት እና ከአዲስ አበባ የሚነሱ ተጓዦችን አሰፈላጊውን ስንቅ አሟልቶ በመሸኘት የከተማ አስተዳደሩ አጋርነቱን ያሳያል።

፨፨፨
የፍቅር ዘመቻው ሠላምን እና አብሮነትን ሰንቆ በዓድዋ ተራሮች አናት ላይ የካቲት 23 ቀን በድል ይጠናቀቃል።
የጉዞ ዓድዋ አስተባባሪዎች
መሐመድ ካሳ
ያሬድ ሹመቴ
#ፍቅር_ለኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም !!
#ጉዞ_ዓድዋ_6
#ከሐረር_አዲስ_አበባ_ዓድዋ
#1540ኪ .ሜ

ምንጭ፦ ያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝

ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።

ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"

#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via Yared Shumete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል~ሀዋሳ🔝

"ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር!" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ የተካሄከው ሰለማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ ላይ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ፦ “ህገ መንግስቱ እንዲከበር፤ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ እንዲሰጠው፤ የሪፈረንደም ቀን በአስቸኳይ ተወስኖ ለህዝብ እንዲነገር ጠይቀዋል።

በሰልፉ ላይ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፦

•ሲዳማነት ከሌለ #ኢትዮጵያዊነት የለም!

•ለውጡን እንደግፋለን!

•በኮሚሽን የሚመለስ ጥያቄ የለንም!

•ለማንም ዘረኛ የማንበረከክ በባህላችን የምንኮራ ህዝን ነን!

•ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር!

•የሪፈረንደም ቀን #ተቆርጦ ይነገረን!

•የሲዳማ ህዝብ መንግስትን እንዳከበረ መንግስትም የሲዳማን ህዝብ ያክብር!

•ሁሉንም #ብሄር እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•ሁሉንም #ሀይማኖት እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•የሁሉንም #ባህል እንወዳለን፤ እናከብራለን! የሚሉት ይገኙበታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጉዞ_ዓድዋ_6

በፈጣሪ ፍቃድ ከሐረር 61 ቀናት ከአዲስ አበባ ደግሞ 47 ቀናት ፈጅተን ከባዱን የእግር ጉዞ በድል ፈጽመን ማርያም ሸዊቶ #ሶሎዳ_ተራራ ግርጌ ዓድዋ ደርሰናል።

ፍቅር ለሆነው ህዝባችን ያለ አንዳች ችግር አብልቶ አጠጥቶ እዚህ ላደረሰን ደጉ ደራገሩ የገጠሩና የከተማው ወገናችን ቸር አምላክ ብድሩን ይክፈልልን።

ከሐረር እስከ አዲስ አበባ፣ ከለገጣፎ እስከ ሸኖ፣ ከደብረ ብርሐን እስከ ቆቦ ከአላማጣ እስከ ዓድዋ፤ ፍቅርን ለመገባችሁን፣ በኢትዮጵያዊነታችን ዳግም እንድንኮራፕ ላደረጋችሁን ብሩካን እናቶችና አባቶቻችን እህቶችና ወድሞቻችን ክብር ይግባችሁ።

"እምዬ አዝምቶ አንስቶ ጋሻ
ድል ባያመጣ አትኖር እንዳሻህ
በእቴጌ ብልሐል ጦር ባይፈታ
ሐገር የለችም የዚያኔው ሞታ
ሚካኤል ብጡል መንገሻ አሉላ
ሐገር የላቸው ከኢትዮጵያ ሌላ"
ፈለግ ተከትለን!!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ።
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via ያሬድ ሹመቴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምስጋና ለአፋር ህዝብ፣ ለአፋር ፖሊስ እና ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት!

"በትላንትናው እለት በአፋር ክልል #አልዲአር ወረዳ ወደ መሀል አገር ለማስገባት የትሞከረ 21 ክላሽንኮቭና ብዛት ያላቸው ጥይቶች በአፋር ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል። ከኛ አልፎ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን #አይገልም አሉ አፋሮች!! ከዚህ በላይ #ኢትዮጵያዊነት ከየት ይምጣ?" GASS AMHEMED

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት ዳግም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ድርጅቱ በላከልን አጭር መግለጫ ግጭቱ ዳግም መቀስቀሱን አውግዟል።

በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላት ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጡ አሳስቧል።

ከዚህም በተጨማሪ በግጭቱ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የንፀሐንን ዜጎች ህይወት እና ሰብዓዊ መብት በመጠበቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia