TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርባ ምንጭ⬆️

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ የሚገኙትን አርባዎቹ ምንጮች ተፈጥሯዊ ውበት፣ ንጽህናና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል የግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ። ሰሞኑን ምንጮች እየደረቁ ነው ተብሎ በሚዲያ የቀረበው ዘገባ #ስህተት መሆኑ ተጠቁሟል የጋሞ ጎፋ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮንን ንጋቱ አርባ ምንጮቹ ለአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ህልውና መሆኑን ተናግረው እነዚህ ምንጮችን ከቆሻሻ፣ ከአፈር እና ከመሳሰሉ ነገሮች በመከላከል ተፈጥሯዊ ውበታቸው ሳይነካ ንጽህናቸውንና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል የግንባታ ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጋሞ ጎፋ ዞን መንግስት ኮሚ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከታቹ‼️

(ከፂዮን ግርማ)

ለመምከር አይደለም-የተሰማችኝን ለማካፈል ነው። ዕድሜ ብዙ ነገር ያስተምራል። በዕድሜያችን ላይ የሚጨምረው ሰዓትና የተጓዝንበት ሂደት ለሚቀጥለው ጊዜ #ስህተት እንዳንሠራ ሊታደገን ይገባል።

ጤናማ ባልሆነ ውድድርና #በብሽሽቅ ውስጥ፤ ከተወዳዳሪውና ከተበሻሻቂው ውጪ በማያውቀው ነገር በፅኑ #የሚጎዳ አካል (ሕዝብ) አለ።

ከችግርና ችጋር ጋር እየታገለ ምንም በማያውቀው ነገር ድንገት መከራ የሚወርድበትን አካል ለመታደግ የምታስፈልገው ነገር “ትንሽ” ናት "ጨዋ" #ቃላትን መጠቀም።

ስድብ፣ ማዋረድና ማንቋሸሽ ከታከለበት ውድድርና በብሽሽቅ ወጥቶ በሐሳብና በጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ አስተያየት መስጠት። #በጨዋ ቋንቋ እየታገዙ የሐሳብ ድርና ማግን መሸመን ከልካይ አይኖረውም።

አንደበታችን ለበጎ፣ ጣቶቻችንን ደግሞ #ለመልካም ሥራ እናውላቸው። ተመልሰን #ለማንመጣባት ምድር መጥፎ ነገር ጥለን አንለፍ። #ጤናማ የአደባባይ ላይ ክርክርና የውይይት ባህልን እናዳብር፣ #ቴክኖሎጂን ከመጥፎ ነገር ይልቅ ለጥሩ ነገር እንጠቀም። እጆቻችንን #ለስድብ አናታትራቸው።

#ሼር - በፌስቡክ ገፃቹ ላይ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንጋ⬆️ዛሬም ለተከታታይ ቀን በቦንጋ ከተማ የተቃውሞ #ሰልፍ ሲደረግ ተስተውሏል። በከተማይቱ የንግድ አገልግሎት እንደቆም እንዲሁም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደተቋረጠ ነው። የቡና መገኛነታችን ይከበር በሚል ነው ተቃውሞው እየተካሄድ ያለው። ከአንድ የከተማይቱ ነዋሪ ጋር በስልክ ባደረኩት ቆይታ በቡና መገኛነት ዙሪያ የተሰራጨው መረጃ #ስህተት በመሆኑ የሚመለከተው አካል በሚዲያ ወጥቶ በግልፅ #ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ብሎኛል። ችግሩ ከዚህ ሳይሰፋም የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ሊፈቱት ይገባል ሲል አክሏል።

©ESA(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

ዶክተር #አርከበ_እቁባይ "ከህወሀት ጋር #ተለያይተዋል" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አረጋገጠ። ጋዜጠኛው በማዕበራዊ ሚዲያ በተሰራጨው መረጃ ዙሪያ ከዶ/ር #አርከበ ጋር በኢሜይል በተለዋወጠው መልዕክት "ዶ/ር አርከበ ከህወሀት ጋር ተለያይተዋል!" የሚለው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። ዶ/ር አርከበ በጉዳዩ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ በፅሁፍ የሰጡት አጭር ምላሽ፦ "አመሰግናለሁ! ይህ #ስህተት ነው"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ አዲሱ አረጋ‼️

"...ሰሞኑን #እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ካሉ ከተሞች አንዱ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያም ጭምር ህገ ወጥ ግንባታ ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ በለገጣፎ ለገዳዲ ብቻ እየተደረገ ያለ እና #ብሄር ለይቶ #እርምጃ አስመስሎ እየቀረበ መሆኑን አስተዉለናል፡፡ ይህ #ስህተት ነዉ፡፡ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 25 ከተሞች በተደረገ እንቅስቃሴም ህግን ብቻ ባማከለ 36,117 ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡"

https://telegra.ph/ህገ-ወጥ-ግንባታን-በተመለከተ-አቶ-አዲሱ-አረጋ-02-22
ዶ/ር ኣርከበ #በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ...

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር #ኣርከበ_እቁባይ በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሎ በፌስቡክ እና መሰል ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ስህተት እንደሆነ የዶክተር ኣርከበ የቅርብ ሰውና የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ ሰው ከደቂቃዎች በፊት በላኩልኝ የፅሁፍ መልዕክት አሳውቀውኛል። ዶክተር ኣርከበ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለህዝቡ ንገርልኝ ብለዋል።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሀሰት መሆኑ ተገለጸ፡፡ በዛሬው እለት አቶ ንጉሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሁነው እንደተሾሙ በማህበራዊ የትስስር ገጾች በስፋት የተሰራጨው መረጃ #ስህተት መሆኑን አሐዱ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ከአቅርብ ምንጮቼ አረጋግጫለሁ ብሏል። አቶ ንግሱ ጥላሁን የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ባለመሆናቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የመሆን እድላቸው ጠባብ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ስህተት ታርሟል!

ኤጀንሲው በፌስቡክ ገፁ የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሰጠው ሰኔ 3-5 ብሎ ያወጣው መረጃ #ስህተት ነው ታርሟል። ፈተናው የተሰጠው ከሰኔ 6 ጀምሮ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ!

በተማሪዎች ውጤት ላይ የታየው #ስህተት የተቋሙን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት መገለጹንና ተማሪዎችና ወላጆች ቅሬታ ማቅረባቸውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ቢሮው በመግለጫው እንዳስታወቀውም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የተወሰኑት ውጤታቸው አልተለቀቀም፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ የፈተና ውጤቱን የሚያስታካክልበትን ግልጽ መስፈርት ሊያሳውቅ እንደሚገባም ቢሮው ጠይቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፈ ጉባኤዋ ይቅርታ ጠየቁ!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት #ዋና_አፈ_ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት #ይቅርታ ያድርግልኝ ሲሉ በይፋ ጠየቁ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረውን የክልሉን አምስተኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ላለፉት አስራ አንድ ወራት የምክር ቤቱን መደበኛ ጉባኤዎች ባለመጥራቴ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ይቅርታ ያድርጉልኝ ሲሉ ተማፅነዋል።

የህዝብ ውክልና ያለው ምክር ቤት በየጊዜው ማከናወን የነበረበትን ስብሰባ አለማድረጉ በየትኛውም መመዘኛ #ትክክል አይደለም ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ በቀጣይ ተመሳሳይ #ስህተት እንደማይደገም በምክር ቤቱ ፊት ቃል እገባለሁ ብለዋል። በእርግጥ እንደምክንያት ማቅረብ ባይቻልም ምክር ቤቱ ማድረግ የነበረበትን መደበኛ ጉባኤዎች ሳያካሂድ የቀረው ክልሉ አጋጥሞት ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ የተነሳ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዓመት #አራት መደበኛ ጉባኤዎችን ማድረግ የሚገባው ቢሆንም ባለፈው የጥቅምት ወር የመጀመሪያውን ስብስባ ካደረገ ወዲህ ዳግም ሳይሰበሰብ ነው የበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው። በዚህም ምክንያት የክልሉ ዓመታዊ በጀት እስከአሁን ባለመፅደቁ የአስፈጻሚ ቢሮዎች ከሀምሌ 1 2012 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስራዎቻቸውን በምክር ቤት ባልጸደቀ በጀት ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

የአዲስ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ማስተካከያ⬆️

"በምትመለከቱት ማስታወቂያ ላይ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥቅምት 28 እና 29 የሚለው የፅሁፍ #ስህተት ስለሆነ መስከረም 28 እና 29 ተብሎ ይስተካከል። በተጨማሪም አዲስ በዱራሜ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን ጥቅምት 5 እና 6 መሆኑን እንገልፃለን።" ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

#share #ሼር

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮችን በስፋት በTIKVAH-MAGAZINE ታገኛላችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ