TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተናገሩት መካከል ፦ " ... ዋናው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ሥራ አጥነት ነው። አብዛኛው ሰው cause ኖሮት አይደለም። ሥራ ፍለጋ ይሄዳል ያግታል ብር ይጠይቃል። ዓላማ መር ትግል ሳይሆን እገታ መር ትግል ነው ያለው። ይሄን ደግሞ በርከት አድርጎ ሥራ በመፍጠር ወጣቱ ወደ ሥራ እንዲሄድ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ተግባሩ…
" በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ የዜጎች #እስር ጉዳይ ነው።

" እስር በዝቷል " በሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው መልስ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እውነቱን ለመናገር አሁን እንዳለው anarchy ፣ ስድብ ፣ጥፋት እስር ቢበዛ ኖሮ ፓርክ ሳይሆን እስር ቤት ነበር የምንገነባው " ያሉ ሲሆን " በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ " ብለዋል።

ምሳሌ ብለውም ፤ ሸራተን ጀርባ ብዙ ተለፍቶበት ተሰርቷል ያሉትና ስራ ከጀመረ 15 ቀን ገደማ በሆነው መንገድ ላይ ቆመው ሽንት የሚሸኑ ሰዎች ጠቅሰዋል።

" እነዚህ ሰዎች ቢታሰሩ አገባብ አይደለም ወይ ? " ሲሉ ጠይቀው " ለማጥፋት ነው የሚመስለው እንጂ ካልጠፋ ቦታ እንደዛ አይነት ቦታ ላይ ሄዶ እንደዛ አይደረግም " ብለዋል።

" እኛ እስር ቤት ሳይሆን ፓርክ ነው እየገነባን ያለነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ከሆነ የእስር ጉዳይ የተነሳው ... ከተያዘው አብዛኛው ሰው ተምሮ ወጥቷል። " ብለዋል።

በሺህ የሚቆጠር ሰው ከእስር እንደወጣ የገለፁት ዶ/ር ዐቢይ " አሁን በጣም በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው እስር ቤት ያሉት። እነሱም እየተጣሩ፣ እየተማሩ ሊፈቱ ይገባል ፤ ሰው እስር ቤት አቆይቶ መቀለብ ለድሃ መንግሥት አያዋጣም። አስተምሮ መመለስ ያስፈልጋል " ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " የታሰሩ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ " ያሉ ሲሆን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚመራው ኃይል እየመረመረ እያወያየ እያሰለጠነ አብዛኛዎችን ይፈታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መሆንም ያለበት እንደዛ ነው። " ብለዋል።

" ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ከዚያ ጋር አብሮ የሚጨፈለቅ ፣አብሮ የሚታይ ነገር ካለ መፈተሽ ጥሩ ነው " ብለዋል።

" እንደው እንከን የለውም የመንግስት አሰራር ብሎ መሄድ ጥሩ አይደለም። የምንፈጥረው ስህተት ካለ እየመረመርን ማስተካከል አለብን። ካጠፋን ይቅርታ መጠየቅ አለብን። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ሀገር ሲፈርስ ዝም ብለን አናይም፤ ስራችን መጠበቅ ስለሆነ ሀገር ጠባቂ ነን ብለን ደግሞ ጥፋት የምናመጣ ከሆነ መጠየቅ አለብን። በጣም በርካታ ሰዎች እኛ ውስጥ ሆነው የሚሰርቁ የሚያጠፉ አሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" #መለዮ ለብሰው ሰላም ማስከበር ሲገባቸው ጥፋት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች አሉ " በማለት የተናገሩት ጠ/ሚኒስትሩ " ብዙዎቹ ይያዛሉ እነሱም ይጠየቃሉ። 100% የተሟላ ባይሆንም በውስጥ የእርማት ስራዎች በስፋት ይሰራሉ " ብለዋል።

@tikvahethiopia