TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፌደራል ፖሊስ‼️

ባለፉት 6 ወራት በርካታ ሽጉጥ፤ ክላሽ፤ በርካታ ጥይቶች፤ቦንብ እና የቡድን መሳሪያ መትረጊስ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በደቡብ ሞያሌ፤ በምስራቅ ቶጎ ውጫሌ፤ በምዕራብ ጋንቤላ ሱዳን አዋሳኝ፤በሰሜን ከሱዳን መተማ ፤ እና በቤንሻጉል ጉምዝ አካባቢ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባና ቱርክ ሰራሽ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

ይህ ህገ ወጥ መሳሪያም በፌደራል ፖለስ ኮሚሽን፤ የሀገር መከላከያ ሚንስቴር፤ የቢሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት እና ከጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም ከሰፊው ሰላም ወዳድ ህዝብ ጋር በመቀናጀት ከበፊቱ ጋር ሲነጸጸር ቀንሷል፡፡ሌላው ሊቀንስ የቻለበት ምክንያት ደግሞ በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትና በተቋሙ ሚዲየሞች አማካኝነት ህብረተሰቡ ስለ ህገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር አስከፊነት በፌደራልና በክልሎች ደረጃ በማስተማር የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ መቀነስ ተችሏል፡፡

በፍተሻ ኬላዎቹም ጥብቅ ፍተሻ ቢደረግም ከዋናው መንገድ ውጭ ባሉ መንገዶች በጋማ ከብትና በሞተር እያጓጓዙ ወደ አራቱም አቅጣጫዎች እንደሚያስገቡ ተገጸል። ይህን የሃገር ሰላም የሚያናጋ ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ግጭት እንዳይባባስ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ያለውን ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ሰላም የሰፈነባትና #የተረጋጋች ኢትዮጵያን መፍጠር ይኖርበታል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከላይ ያለውን የድምፅ ፋይል ይክፈቱት🔝

የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ዘገባ~የሲዳማ ዞን ከተሞች!

የሲዳማን ክልል እንሁን ጥያቄ ተከትሎ በዞኑ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሁከት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ በሁከቱ እስከ አሁን የዘጠኝ ሰው ህይወት አልፋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፤ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል፡፡ የሁከቱ ሰለባ የሆኑ እንደሚናገሩት በአንዳንድ በሲዳማ ዞን ከተሞች ተቃውሞው ዛሬ መልኩን ቀይሮ ማንነትን በመለየት፣ የመኖሪያ ቤትና ንብረት ላይ ጥቃት ደርሷል፡፡ መንግሥት ተጨማሪ ኃይል በማስገባት ሰላማችንና ደኅንነታችንን ያረጋግጥ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፣ ዛሬ ሀዋሳ #የተረጋጋች መሆኑ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ሲአን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከአስር በላይ ሰዎች በመልጋ ወረዳና አካቢው ሞተዋል ብለዋል፡፡ በግጭቱ ማዘናቸውን የገለፁት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ህዝቡ #እንዲረጋጋ ጠይቀዋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ችግሩን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፀጥታ ኃይል እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሶሳ የሰላም አየር እየነፈሰ ነው!

አሁን በስራ ምክንያት ያለሁት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ #አሶሳ ነው። ሞቃት የአየር ንብረት የሚስተዋልባት፣ አረንጓዴ፣ እና ቀይ ለም አፈር ያለው መሬት ያላት። አሶሳ ከመጣሁ እነሆ ሶስተኛ ቀኔ አለፈ።

አንዳንድ ጓደኞቼ እንዲሁም ቤተሰቦቼ ጋር ተደዋውዬ በስልክ ሳወራ ከኔ ሁኔታ ይልቅ ስላለሁበት ቦታ #አሶሳ አብዝተው ይጠይቃሉ። ገና ለመምጣት በነበርኩበት ግዜ እራሱ ምነው ወደዛ መሄድህ... ? በሰላም ነው? እያሉ በጥያቄ ያጨናነቁኝ ቁጥራቸው ብዙ ነው። መጠየቃቸውን እንደ መጥፎ ነገር ባልቆጥረውም አንድ ነገር ግን በአእምሮዬ ብቅ እንዲል ሆኗል። እኔ ባለሁበት ሰዐት አሶሳ እጅግ #የተረጋጋች፣ ሰላማዊ እና የዕለተ ቀን እንቅስቃሴዋን የምትከውን ከተማ ነች።

ምናልባት የሰዎች ጥያቄ የመጣው ከጊዜያት በፊት በክልሉ በመተከል፣ ካማሺ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በነበረው አለመረጋጋት እና ግጭት ይመስለኛል። እስካሁን ድረስ ግን ብዙ ሰዎች በክልሉ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ሰላማዊ ሁኔታ ያለ #አይመስላቸውም

ሰላም እና መረጋጋትም የማይመቻቸው እና እንቅልፍ የሚነሳቸው አካላት በየማህበራዊ ሚዲያው በሚፈጥሩት ዉዥንብር ምክንያት እና በማይረቡ ተናፋሽ ወሬዎች ማለቴ ነው እና አሁን በአሶሳ ፍፁም #የሰላም አየር ነው እየነፈሰ ያለው ያለው። እንዲሁ በሌሎች ክልሎችም እንዳጣራሁት ከሆነ በብዛት የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የኢትዮጵያ ሰላም እየተመለሰ ነው። ይመለሳልም። ኢትዮጵያ በሰላም፣ እስከዘላለም ትኑር።

Y ነኝ ቤተሰባችሁ ከአሶሳ!

ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia