TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያዊ ነኝ ዘረኝነትን ተጠይፌ ከፍቅር ጋር ተደምሬ ሀገሬን ለመለወጥ ተነስቻለሁ!

#ETHIOPIA ሼር!
#ኢትዮጵያዊ ነኝ ዘረኝነትን ተጠይፌ ከፍቅር ጋር ተደምሬ ሀገሬን ለመለወጥ ተነስቻለሁ!

#ETHIOPIA ሼር!
#update አዲስ አበባ⬇️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ #ብሔር_የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የተሻሻለው መመርያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማነዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡

ይህንን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ በክፍላተ ከተሞችና በወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን ያካተተ ሥልጠና፣ ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ብሔርን የሚጠቅስ በመሆኑ፣ ይህም ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎላ ስለሆነ በተገኘው አጋጣሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በያዙ ማግሥት ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደገለጹት፣ የመታወቂያ ጉዳይ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ እየተነሳበት በመሆኑ አሰጣጡን ማስተካከል ይገባል፡፡

በዚህ መሠረት መመርያው የተሻሻለ በመሆኑ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ለውጥ ያመጣል ተብሏል፡፡

የመጀመሪያው በመታወቂያ ላይ ከብሔር ስያሜ ይልቅ #ኢትዮጵያዊ ሲባል፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሰጣጡ ዲጂታል ስለሚሆን ሕገወጦችን መለየት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ በተለይ ሕገወጥ ጥቅም የሚሹ ግለሰቦች፣ በተለያዩ ዘዴዎች መታወቂያ በማውጣት ሲያገኙ የቆዩትን ጥቅም እንደሚያስቀር ታምኗል፡፡

ለአብነት በክልል ከተሞች የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው በሕገወጥ መንገድ  የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ኮንዶሚኒየም ቤት የተቀራመቱትን ዕርምጃ መውሰድ ያስችላል ተብሏል፡፡

የተሻሻለው መመርያ የኮምፒዩተር አመዘጋገብ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ ሒደት፣ የነዋሪዎች መታወቂያ ይዘትና የመሸኛ ጉዳይን በዝርዝር ይዟል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏆የሰላም እና ወዳጅነት ዋንጫ🏆

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወጣት ብሔራዊ ቡድኖችን የሚያገናኝ ውድድር በቅርቡ አስመራ ላይ ይደረጋል።

“የሰላም እና ወዳጅነት ዋንጫ” በሚል ስያሜ በየካቲት ወር መጀመሪያ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ውድድር የ10 ቀናት እድሜ የሚኖረው ሲሆን የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖችን ያሳትፋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ #ኢሳይያስ_ጅራን ጨምሮ የቀጠናው የእግርኳስ አመራሮች ከሳምንት በፊት በአስመራ በነበራቸው ስብሰባ ውድድሩ በሚደረግበት ሂደት ላይ ተነጋግረዋል።

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በበኩሉ 25,000 ዶላር ለኤርትራው ፌዴሬሽን በመስጠት ዝግጅቱን ለማገዝ ተስማምቷል።

የኤርትራ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለዚህ ውድድር ከወዲሁ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ #ኢትዮጵያዊ ዳኞች በሚመሩት የወዳጅነት ጨዋታ የሱዳን አቻውን ያስተናግዳል።

ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ ሰላማዊ ግንኙነት ከቀጠሉ በኋላ በብሔራዊ ቡድን እና በክለቦች ደረጃ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ቢታሰብም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ እንደቀረ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴላቪቭ‼️

በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን አንድ #ኢትዮጵያዊ በእስራኤል ፖሊስ መገደሉን በመቃወም ቴላቪቭ ውስጥ ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። የ24 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ይሁዳ ባይድጋ ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር በፖሊስ ተተኩሶበት #የተገደለው#ሰልፈኞቹ የቴላቪቭ ዋና ጎዳናን #በመዝጋት እና በዋና ዋና መንገዶች በማለፍ ባካሄዱት ሰልፍ በእሥራኤል ዘረኝነትን እና ፖሊስ የሚፈጽመውን ከመጠን ያለፈ ጥቃት እና አድልዎ #ተቃውመዋል። በእስራኤል ምክር ቤት የሰብአዊ ሐብት ሎጂስቲክ አስተባባሪ አቶ ዮናታን ታከለ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊውን የገደለው ፖሊስ አሁንም በስራ ላይ ነው። ይህም ቤተ እስራኤላውያንን በእጅጉ አስቆጥቷል። የዐአእምሮ ህመምተኛው ልጃቸው ይሁዳ ከቤቱ ስለት ይዞ ሲወጣ ፣እንዲደርስላቸው እናቱ ደውለው የነገሩት ፖሊስ ተኩሶ እንደገደለው ተዘግቧል። በእሥራኤል ጦር ውስጥ ማገልገሉ የተነገረውን የይሁዳን አሟሟት የእስራኤል የፍትህ ሚኒስቴር እያጣራሁ ነው ብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 23/2011 ዓ.ም.

ከትራንስፓርት ሚንስቴርና ከሌሎች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የሉኡካን ቡድን የጅቡቲ ወደብን ጎብኝቷል።
.
.
ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል።
.
.
ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል።
.
.
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የፀደቀውን #የስደተኞች_አዋጅ በመቃወም ነገ በጋምቤላ ከተማ ሊደረግ ለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ #ከልክሏል
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ሺህ ነጋዴዎች ግብር ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ግብር ስረዛው ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከፍተኛ የግብር ተመን ተጥሎባቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩትን ነጋዴዎች ያካትታል፡፡
.
.
4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትንላንት ጀምሮ ዳግም #ያገረሸው #አለመረጋጋት ዛሬም ቀጥሏል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ ውሏል። ከተማዋ በፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ደረጃ እየተጠበቀች ነው።
.
.
ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ  ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል።
.
.
ጅቡቲ በተካሄደው 15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ ልዑካን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተዋል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
.
.
#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናብቷል።
.
.
የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
.
.
በሱማሌ ክልል ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰዓት ዕላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡ የአደባባይ ስብሰባም ተከልክሏል፡፡
.
.
#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ለሚያልፉ ዐለም ዐቀፍ መንገደኞች #የነጻ ጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበር እና #የሰላም_ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሰላም ሚዲያ ህብረት ትስሰር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ዛሬ ማምሻውን አካሂደዋል።
.
.
የሐረሪ ክልል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ #መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ  አስታውቋል።
.
.
#ብሄሬን መሰረት ተደርጎ ጥቃት ተፈፅሞብኛል በሚል በሀሰት የሽንት መሽኛ #ብልቱን በፋሻና ፕላስተር በመጠቅለል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከረው ግለስብ ድሬ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ በዳቦ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ አግባብነት የሌለውና ህብረተሰቡን ያላማከለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
.
.
በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን አንድ #ኢትዮጵያዊ በእስራኤል ፖሊስ መገደሉን በመቃወም ቴላቪቭ ውስጥ ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
.
.
በአሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ቅዝቃዜ እስካሁን ቢያንስ ስምንት ሰዎች #መሞታቸው ተገለጸ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ሜድ ዌስት የተከሰተው ቅዝቃዜ በአስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አደገኛ ነው፡፡
.
.
ምንጭ፦ etv፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ራድዮ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ bbc፣ VOA፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አና ጎሜዝ🔝

ሁሉም #ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ አስተዋጽኦ ስላለው አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ነኝ ብሎ ማሰብ እንደሌለበት #አና_ጎሜዝ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በ1997 ዓ/ም በተደረገ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጎሜዝ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስለአንድነት እንጂ ስለመከፋፈል ማሰብ የለባቸውም ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት አባል የሆኑት ጎሜዝ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ መጥቷልም ብለዋል። ይሁንና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች ሚሊዮኖች #እንዲፈናቀሉ አድርገዋል ብለዋል። አና ጎሜዝ ኢትዮጵያውያን አንድነት ላይ ከሰሩ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ዕምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በበርኒግሀም የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር በሴቶች 3 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቁ፡፡ በዚህም #አልማዝ_ሳሙኤል በ8 ደቂቃ 54 ሰከንድ 60 ማይክሮሰከንድ አንደኛ ደረጃን በመያዝ  አጠናቅቃለች፡፡ #አክሱማዊት_እምባየ በ8 ደቂቃ 54 ሰከንድ ከ97 ማይክሮሰከንድ እና #መስከረም_ማሞ በ8 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ03 ማይክሮሰከንድ በመግባት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ ሌላኛዋ #ኢትዮጵያዊ አትሌት #እጅጋየሁ_ታየ በ8 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ28 ማይክሮሰከንድ በመግባት የአራተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉዞ ሉሲ~ለሰላምና ለፍቅር!

‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር መርሀ-ግብር›› ትላንት ምሽት በሚሊኒዬም ተጀምሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ካሰው ‹‹ዘረኝነት፣ መለያዬት፣ ማግለልና ንፉግነት የኛ የኢትዮጵያዊነት ባሕል አይደለም፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የነበረንን መተዛዘን፣ #ፍቅርና #አንድነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለውጥ የሚጀምረው ከራስ ነውና ለለውጥ እዘጋጃለሁ፤ ለለውጥ እንዘጋጅ›› በሚል #የአንድነት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በመርሀ-ግብሩ ከአፋር ክልል ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ሉሲ የአምስት ቀናት ቆይታ እያደረገች ሕዝቡ #በአንድነቱ ዙሪያ እንደሚወያይ የገለጹት ሚኒስትሯ ‹‹ሉሲንና ሌሎች አንድ የሚያደርጉን በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶችን በታላቅ ክብር ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ ፓርላማ አጓጉዘን ወደ አፋር በመሸኘት ይጀመራል›› ነው ያሉት፡፡

ሉሲ የእገሌ የሚባል ሃይማኖት፣ ብሔር፣ አስተሳሰብ ወይም ሌላ #ወካይ_ያልሆነች የሁሉም የሰው ዘር ግንድ መሆኗን የጠቀሱት ሚንስትሯ ‹‹ደግነትና አብሮነት ስላልተለየን በጎ ትሩፋት ሳይሠራ የሚውል #ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ የተራበ ሳያበላ፣ የተጠማ ሳያጠጣ፣ የወደቀ ሳያነሳ፣ የሞተ ሳይቀብር አይውልም፤ ኢትዮጵያዊነትም ይህ ነው›› ብለዋል፡፡ እንኳን እርስ በእርስ ከሌላውም ዓለም ጋርም ኢትዮጵያዊ በሉሲ የተዛመደ መሆኑንና #ዘረኝነት የኢትዮጵያዊነት ባሕል አለመሆኑን ነው ዶክተር ሂሩት ያስገነዘቡት፡፡

በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ አንጋፋና ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታዳሚውን ያስለቀሰው የብሩክ የሺጥላ ንግግር...

"ከዛሬ ጀምሮ ይህቺ ምደገፍባት ነገር አታስፈልገኝም ለምን መሰላችሁ ሲደክመኝ ሚደግፈኝ #ኢትዮጵያዊ_ወንድም አለኝ፤ ሲርበኝ አይዞህ ብሎ የሚያበላኝ እህትና ወንድም አለኝ፤ እኔ ማውቃት ኢትዮጵያ ይህቺን ነው፤ እኔ #የኖርኩባት ኢትዮጵያ ይህቺ ነች፤ ልጄም ይህንን እውነት እንዲኖረው እፈልጋለሁ፤ #ልጆቻችንም ይሄንን እውነት የሆነ ኢትዮጵያ ኖረው እንዲያልፉ ሁሉንም ነገር #እናመቻችላቸው፤ ችግርን ከመፍጠር ይልቅ ብዙ ችግሮች አሉብን ስለ ችግሮቻችን ካወራን ችግሮቻችን አያልቁም። መሪዎቻችን ደግሞ ገና #በተመቻቸ ሁኔታ ላይ አይደሉም፤ እነሱ ላይ ብዙ ችግር አንፍጠርባቸው፤ እኛ የምንችለውን ችግር እንፍታ እነሱም ደግሞ መፍታት የሚችሉትን ያህል ችግር ይፍቱልን። የሚቀጥለው መሪ የተሻለ ወንበር እንዲያገኝ፤ የተመቻቸ ወንበር እንዲያገኝ፤ እኛንም ከዚህ በተሻለ በደንብ መምራት እንዲችል ሁሉን ነገር እኛ እናመቻችለት።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#GERD🇪🇹

"...በሚመጣው ነገር ሁሉ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን" - የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ሙሌት እንዲሁም አጠቃላይ ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገለፁ።

የሰራዊቱ አባላት ይህን ሲገልፁ የተሰማው ሀገር መከላከያ ባሰራጨው የ1 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ርዝማኔ ባለው ቪድዮ ላይ ነው።

የመከላከያ አባላት የግድቡ ስራ ለሰከንድም ሳይቆም ይሰራል፣ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌትም ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

"እኛ በህይወት እስካለን የግድባችን ስራ ለሰከንድ አይደናቀፍም" ብለዋል።

ሁሉም #ኢትዮጵያዊ ከጫፍ ጫፍ ሆ ብሎ በመነሳት የገነባው ግድብ መሆኑን የተናገሩት የሰራዊቱ አባላት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሚመጣው ነገር ሁሉ ቀድመን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን በዚህም ህዝቡ በምንም መልኩ ሊጠራጠር አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት - የአማራ ክልል ባለስልጣናት - የህወሓት አመራሮች - የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order) የትግራይ…
#DrAbiyAhmed #JoBiden

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ግልፅ ደብዳቤ ✉️ ፃፉ።

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፃፉላቸው ግልፅ ደብዳቤ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ 🇪🇹 ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፥ ሕወሓት በአፋርና አማራ ያፈናቀላቸው ንፁሃን ዜጎች በከፋ ችግር ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን ቡድኑ ቤተሰቦቻቸውን እንደገደለባቸው እንዲሁም የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጨምሮ ንብረት እንዳወደመ አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ላይ እየደረሱ ያሉ የውጭ ጫናዎች ተገቢ አለመሆናቸውንም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ በቅርቡ የተመሰረተው አዲሱ የባይደን አስተዳደር ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ እንደሚሆን ኢትጵያውያን ተስፋ እንደነበራቸው አውስተዋል።

አሜሪካ ሌሎች ሃገራት ላይ በነበራት የተሳሳተ የውጭ ፖሊሲ በሃገራቱ ላይ ያስከተለውን ቀውስ አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተስፋ በቆረጡ እና ስልጣን ከሚሊዮኖች ደህንነት በላይ በሚያሳስባቸው ግለሰቦች አትሸነፍም ሲሉም ገልጸዋል፡፡ #ኢትዮጵያዊ እንዲሁም #አፍሪካዊ ማንነታችን እንዚህ ግለሰቦች እንዲያሸንፉ አይፈቅድልንም ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#Kenya

የኬንያ ፖሊስ 41 ኢትዮጵያውያንን ናይሮቢ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።

ግለሰቦቹ ወደ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች አገራት ለመዘዋወር በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ቀናት ያህል ሲጠባበቁ ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም መያዛቸውን ገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑን በሕገ ወጥ መንገድ ሊያዘዋውሩ ነበሩ የተባሉ ሁለት አዘዋዋሪዎችም በዚሁ አጋጣሚ የተያዙ ሲሆን አንደኛው #ኢትዮጵያዊ መሆኑም ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው እነዚህ የሕገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች በርካታ ዝውውሮች ጀርባ እንዳሉበት ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ በዚህ ሳምንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ወደ ኬንያ እንዴት እንደገቡ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት በእስር እንዲቆዩ መታዘዙን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia