TIKVAH-ETHIOPIA
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር የማለም ተግዳሮቶች ገጥመዋል " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በማለም ፤ ከተማዋንም ወደ አለመረጋጋት የማስገባት ተግዳሮቶች ገጥመዋል ሲሉ ገለፁ። ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህንን…
#Update
ዛሬ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ተከትሎ፤ ከም/ቤት አባላት ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።
የም/ቤት አባል ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ " ከአንዳንድ ክልሎች በከፍተኛ መጠን ወደ ከተማዋ ይገባሉ " የተባሉ " ፍልሰተኞችን " በተመለከተ "ከአንዳንድ ክልሎች " የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? ክልሎቹ ቢገለጹ " ሲሉ ጠይቀዋል።
" ከአንዳንድ ክልሎች የሚመጡ ሰዎች እንደዚሁ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር አስበው ወይም ህጋዊውን መንግስት ለመገልበጥ አሲረው " በሚል የተቀመጠው ሃሳብ ያልተብራራ መሆኑንም አንስተዋል።
• የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተከያዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦
- የአደባባይ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ረብሻ እና ሁከት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች አሉ።
- በአደባባይ በዓላት ላይ ለመፍጠር የሚፈለገው ችግር በተቀናጀ መንገድ የሚመራ ነው፤ ለዚሁ ሲባል ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ኃይሎች አሉ።
- ፍልሰቱ የተለመደ ነው ከሁሉም አካባቢ ሰው ይመጣል። ነገር ግን በዓላት ሲቃረቡ የተለያየ ተልዕኮም ተሰጥቷቸው የሚመጡ አሉ። ባሳለፍነው 2 እና 3 ዓመታት የምናውቃቸው ተጨባጭ የሆኑ መረጃዎች አሉ፤ ይህ ጉዳይ በዚህ ዓመት ብቻ የታየ አይደለም።
- ሰዎች በብዛት ወደ አዲስ አበባ የሚገቡት 64 ፐርሰንት የሚሆኑ ከአማራ ክልል አካባቢ ነው፤ 21 ፐርሰንት የሚሆኑት ከደቡብ አካባቢ ነው። 14 ፐርሰንት ከኦሮሚያ ነው።
• የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ተከታዮቹ ነጥቦች አንስተዋል ፦
- በርከት ያሉ ኃይሎች ሰላም እና ጸጥታ ለማደፍረስ ወደ ከተማ ይገባሉ የመጀመሪያውን ስፍራውን የሚይዙት ከአማራ ክልል የሚገቡ ኃይሎች ናቸው፤ ከደቡብ እና ከኦሮሚያ አጎራባች ክልሎች አካባቢ ወደ ከተማዋ የሚገቡ ሰዎች በተከታታይ ደረጃ ይቀመጣሉ።
- ችግሩን በተደራጀ መልኩ ይዞ መጥቶ፤ ከተማዋን ለመበጥበጥ የሚፈልግ ኃይል አለ።
- አዲስ አበባ ውስጥ ሃይማኖት፣ ብሔር፣ ፖለቲካ እና መደበኛ ወንጀል መከላከልን ማዕከል ያደረጉ ፤ የጸጥታ መደፍረሶች አሉ። ከእነዚህ የፀጥታ ችግር መነሻዎች ውስጥ ከተማዋን በተደጋጋሚ እየፈተናት ያለው በዓላትን መነሻ ባደረጉ እና የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ኃይሎች የሚፈጸመው ነው።
• ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ፦
- በዓላትን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በተመለከተ ዳታው ቅድም የተገለፀው (በፖሊስ ኮሚሽን) ነው።
- ወደ ከተማዋ የሚፈልሱት ሰዎች የሚመጡባቸውን አካባቢዎች ላይ በጣም ከፍተኛ፣ አንጻራዊ ያልሆነ መበላለጥ አለ።
- በከተማዋ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች በሙሉ ከከተማዋ ውጪ በሚመጡ ሰዎች የተፈጸሙ አይደሉም። ከተማው ውስጥ ባለው ኔትወርክ ነው። የተለያየ ጥቅም እና የፖለቲካ ትርፍን ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ለዚሁ ቅስቀሳ አድርገዋል።
- የመንግስት ስልጣንን በህጋዊ መንገድ ያላገኙ አካላት፤ በተለያየ መንገድ እነኚህን በተለየ ሁኔታ በመቀስቀስ እና ተልዕኮ በመስጠት ወጣቶችን ወደ ጥፋት በመማገድ ላይ ተሰማርተው ታይተዋል።
- ችግሮች በሚፈጠሩበት ጊዜ የም/ቤት አባላት በምታስተላልፏቸው መልዕክቶች ላይ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል። ችግሮች በሚፈጸሙበት ሰዓት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በመጻፍ፣ አነቃቂ ንግግር በሚመስል፣ በተለያየ መንገድ፤ እኛ ልንሞገስበት ህዝቡ ግን ዋጋ ሊከፍልበት የሚደረገው ድርጊት መታረም ያለበት። የምታደርጉት የምትናገሩትና የምትፈፅሙት ነገሮች የህዝብን ሰላምና ደህንነትን ያገናዘበ መሆን አለበት።
#EthiopianInsider
@tikvahethiopia

#Ethiopia የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበው 236.7 ቢሊዮን ብር ነው። አጠቃላይ የ2017 በጀት (971.2 ቢሊዮን) በ2016 በጀት ዓመት ከጸደቀው የወጪ በጀት አንጻር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ተገልጿል። ዛሬ ከሰዓት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ምክር…
#ብር #ዶላር
የፌዴራል መንግሥት #የ2017_በጀት ሲዘጋጅ ብርን ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሬ ተመን #የሚያዳክም ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል በሚል ታሳቢነት እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለተወካዮች ም/ ቤት ተናግረዋል።
በኢ-መደበኛው እና በባንኮች በሚደረግ ይፋዊ ምንዛሬ (official exchange) መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ እርምጃን አስመልክቶ " ምንም የቀረበ ነገር የለም " ብለዋል።
አቶ አህመድ ፥ የፌዴራል መንግሥት በጀት የተዘጋጀው " የነበረው አካሄድ #እንደሚቀጥል ታሳቢ ተደርጎ " ሲሉ ገልጸዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ " ዘንድሮ የነበረውን ይፋዊ የውጭ ምንዛሬ መጠን (official exchnage rate) ታሳቢ አድርጎ ነው በጀቱ የቀረበው " ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህን ማብራሪያ የሰጡት በም/ቤቱ የኢዜማ ተወካይ ዶ/ር አብርሃም በርታ ፥ " ህጋዊውን እና ኢ-መደበኛውን የውጭ ምንዛሬ ገበያ እኩል ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች እንዳሉ ከአንዳንድ ወገኖች እየሰማን ነው ፤ ... የውጭ መንግስታት #በብድር_ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር ይህንኑ ለማስፈጸም እንደሚንቀሳቀሱ የሚገልጹ መረጃዎችም አሉ ፤ እንዲህ አይነቱ እርምጃ የማንወጣው ችግር ውስጥ ይከተናል የሚል የባለሙያዎች ትንታኔ አለ " በማለት ላነሱት ሀሳብ ነው።
#EthiopianInsider #HoPR #TikvahEthiopia

ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።
ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው።
ተጨማሪ በጀቱ ፦
➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣
➡️ ለነዳጅ ድጎማ፣
➡️ ለዘይት ድጎማ፣
➡️ ለማዳበሪያ እና መድኃኒት ድጎማ የሚውል መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ፎቶ፦ ፋይል
#EthiopianInsider #HoPR #Ethiopia