TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 24/2011 ዓ.ም.

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ።
.
.
የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰድስት ወራት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ገልጿል።
.
.
ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀነራል #ጥጋቡ_ይልማ_ወንድማገኝ በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ አዛዥ በመሆን ተሹመዋል።
.
.
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል #ግብር አሰባሰብ ችግር በፈጠሩ 75 ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ #እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በተለያየ ጊዜ ለልማት መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ122 ኢንተርፕራይዞች ላይ #እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
.
.
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
.
.
የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
.
.
24 የአልሸባብ ቡድን አባላት በአየር ድብደባ #መሞታቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታውቋል።
.
.
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
.
.
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
.
.
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ #ሊከለስ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንደገለጹት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲ በማስፈለጉ ነው ክለሳ የሚደረግበት፡፡
.
.
16ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡
.
.
የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት፣ ላፓልማ እና ባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበር #የሙስና_ወንጀል ጋር በተያያዘ ከጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መካከል አራቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
.
.
የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።
.
.
የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር #ዳዊት_ዮሐንስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን ይፈፀማል፡፡
.
.
የጎፋ ዞን ዛሬ #በይፋ ተመስርቷል። የዞኑ ይፋዊ የምስረታ በዓል በሳውላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዞኑ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከብሯል፡፡
.
.
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ #ባቢሌ ከተማ ላይ #በመዘጋቱ መቸገራቸውን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣etv፣fbc፣ ዋዜማ ራድዮ፣ BBC አማርኛ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስልጤ ዞን ዛሬ ቢያንስ 2 ሰዎች የገደሉ‼️

በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ገርቤ በር ወረዳ ባሎቀሪሶ በተባለ ቦታ በዛሬው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች እና በጸጥታ አስከባሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የዐይን ዕማኞች ተናገሩ። በግጭቱ የቆሰሉ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ተወስደዋል። የጀርመን ራድዮ ያነጋገራቸው ሶስት የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ሁለት ሰዎች የተገደሉት የጸጥታ አስከባሪዎች በተኮሱት ጥይት ነው። ግጭቱ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ገደማ መቀስቀሱን የተናገሩ የዐይን እማኝ "የሞተ ሁለት ነው። ግን በርካታ ቆስሏል። የቆሰለውን ይኸን ያህል አልለውም። በርካታ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

አንድ ሌላ የዐይን ዕማኝ የሟቾቹ ቁጥር ሁለት መሆኑን #አረጋግጠው የግጭቱ መነሾ ለኢንቨስትመንት የታጠረ ቦታ ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ በወጣቶች በመቅረቡ እንደሆነ አስረድተዋል። የዐይን እማኙ የአካባቢው ወጣቶች ታጥሮ የተቀመጠን ቦታ ለማፅዳት ሲሞክሩ "ግብግብ ተፈጥሮ አንድ ሁለት ሰው ሞቷል" ብለዋል። "ከዚህ በፊት ለኢንቨስትመንት የተሰጠ መሬት ነበር። የተሰጠው ባለሐብት ሶስት አመት ሙሉ አጥሮት ነው ቁጭ ያለው። ምንም የሰራው ነገር የለም" የሚሉት የዐይን እማኝ የአካባቢው ወጣቶች በተደጋጋሚ ቦታው ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ ከወረዳ እስከ ክልል አቅርበው ነበር ብለዋል።

"ጠዋት ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ቤቶችም ተቃጥለዋል" ያሉ ሶስተኛ የዐይን እማኝ በበኩላቸው በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎች ወደ #ወራቤ_ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተናግረዋል። ከቆሰሉ መካከል የጸጥታ አስከባሪዎች ይገኙበታል ተብሏል። የዐይን ዕማኞቹ የጸጥታ ኃይሎች ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ የመረጋጋት አዝማሚያ ይታያል ብለዋል።ወጣቱ ተጭኖ ተጭኖ እየሔደ ነው። ግጭት የተቀሰቀሰባት የገርቤ በር ወረዳ በስልጤ ዞን ከወራቤ ከተማ በ13 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ትገኛለች።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱዓ እና ምህላ እየተደርገ ነው!

የሰዎች ህይዎት ላይ እየደረሰ ያለው በደል #እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች አስታወቁ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው #ግጭት ምክንያት በሰዎች ህይዎት እየደረሰ ያለው ጉዳት #ምህረት እንዲያገኝ ነው #ምህላ እና #ዱዓ እየተደረገ የሚገኘው። በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች #ሞት#መፈናቀል እና #መሰደድ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶች አውግዘዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይሄ ፊልም አይደለም!! የግጭት እና የጦርነት ውጤት መሬት ላይ ያለው እውነታ ነው!! ጦርነት እና ግጭት #ፌስቡክ ላይ #ተዘፍዝፎ እንደመለፍለፍ ቀላል ከመሰለህ ሶሪያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን ጎራ በል በጥይት ድምፅ ስትሳቀቅ፤ ያቀረብከውን ምግብ ለመብላት ሲያቅትህ፤ ብር ኖሮህ ምግብ ለመግዛት ከቤትህ ለመውጣት ሲከብድህ፤ መብራቱና ኔትዎርኩ ተቋርጦ ጨለማ ውስጥ ስትቀመጥ ያኔ #ግጭት እና #ጦርነት ትርፉ ምን እንደሆነ ይገባሃል!!
.
.
#ሰላም_ብቻዋን_ታዋጣለች!!
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update በምዕራብ ወለጋና ካማሺ ዞን ለረጅም ወራት ዘልቆ የቆየው #ግጭት በዘላቂነት እንዲፈታ ተቋርጦ የነበረ የሕዝብ፣ ለሕዝብ የጋራ ውይይትና የባህላዊ ዕርቅ ሥነ ስርዓት ተካሄደ። በሥነ ስርዓቱ ላይ የታደሙ የሁለቱም ዞን ተወካዮች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የነበረው እንቅስቃሴ እንዲጀመር ተግባብተዋል፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዳንሻ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታ‼️

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው #ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የትግራይ ክልል መንግሥት አስታውቋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ የትግራይ ክልል መንግስት ዐስታውቋል፡፡ የከተማዋ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሽከርካሪዎች ላይ እየወሰዱት ያለው #እርምጃ የተቃወሙ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተው እንደሰነበቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ግጭቱ በመስጋት የዳንሻ ነዋሪዎች ከተማዋ ለቀው በአቅራብያቸው ወደሚገኙ አካባቢዎች #መሰደዳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ የምትገኘው ዳንሻ ከተማ ካሳለፍተው ሳምንት ጀምሮ ግጭት ስታስተናግድ ሰንብታለች፡፡ የአካባቢው ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች «ሕገ ወጥ» ያልዋቸው ሞተር ብስክሌቶችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መያዝ መጀመራቸው ተከትሎ በተከሰተው አለመግባባት ወደ ሁከት ገብታ የሰነበተችው ዳንሻ ከረቡዕ የካቲት 20 ጀምሮ በከተማዋ በተስተዋለ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ከሞቱት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች እየታከሙ መሆኑ ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ በፖሊስና እርምጃው በተቃወሙ ወጣቶች መካከል የተከሰተው ግጭቱ እየተባባሰ መቀጠሉ ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ዳንሻን እየለቀቁ መሆኑ ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር የነበረው በድህንነት ስጋት ምክንያት ከተማዋ ለቆ አሁን ሑመራ እንዳለ የሚናገረው ፀሐዬ የተባለ አስተያየት ሰጪ በግል ንብረቱ ጨምሮ በብዙዎች ሀብት ላይ ውድመት መድረሱ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል፡፡

እንደ ጀርመን ራድዮ ምንጮች መረጃ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የከተማዋ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት አቋርጠው ሰንብተዋል፡፡ በከተማዋ ቅኝት ማድረጉ የሚናገረው ተመስገን ካሳሁን የተባለ የአይን እማኝ፡ ዳንሻ ዛሬ በአንፃራዊነት #ተረጋግታ ውላለች ብሏል፡፡ የተወሰነ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መመልከቱም ተናግሯል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግጭቱ ለማብረድ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ የትግራይ ልዩ ሐይል ፖሊሶች በቦታው #ተተክተዋል፡፡

የዳንሻን ጉዳይ አስመልክተን የተጠየቁት የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊዋ ወይዘሮ #ሊያ_ካሳ የክልሉ መንግስት ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተናግረዋል፡፡ ግጭት የፈጠሩ አካላትም "ሕግ የማስከበር ተግባር የማይዋጥላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው" ብለዋል፡፡ በከተማዋ ትራፋክ ተቆጣጣሪዎች የተወሰድ እርምጃ ክልል የለየ እንዳልሆነና ሕግ የማስከበር ተግባር ብቻ መሆኑ ሐላፊዋ ለጀርመን ራድዮ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ

ዛሬ በሀዋሳ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ የተፈፀመው #ድብደባ!

ከደቂቃዎች በፊት አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከደቡብ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ከሆኑት ከዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ጋር በስልክ ቆይታ አድርጎ ነበር ስለጉዳዩ ይህ ብለዋል፦

"በመጀመርያ በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው። ጠዋት እኔ ስመራው የነበረው ስብሰባ ሌላ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ወጣቶች መጥተው ስብሰባው ይቁም ሲሉ confront ሳናረጋቸው አመራሮችን ወዲያው #በትነናል። የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን ላይ ግን #ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ስብሰባ ይካሄድበት የነበረው አዳራሽ ውስጥ ከመጡት ወጣቶች ጋር #ግጭት ነበር። ዝርዝሩን አላውቅም። አሁን ሰላም ነው። አቶ ፀጋ ለህክምና ሶዶ ደርሷል። ከትንሽ ደቂቃ በፊትም አናግሬዋለሁ።"

ማነው ድብደባውን የፈፀመው ተብለው በጋዜጠኛው ለቀረበላቸው ጥያቄ፦

"እከሌ ኤጄቶ ነው እከሌ አይደለም ለማለት አልችልም። ግን ሶሻል ሚድያ ላይ ኤጄቶ ስብሰባው እንዲበተን ይፈልጋል የሚል መልእክት ጠዋት ስብሰባ ከመግባቴ በፊት አንብቤ ነበር።"

የሶሻል ሚድያ ምስል: አቶ ፀጋ ስምኦን

Via Elias Mesret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ጎንደር ተከስቶ በነበረው #ግጭት ምክንያት ወደ ሱዳን #ተሰደው የነበሩ 838 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው መመላሳቸው ተገልጿል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia