#መከላከያ_ሰራዊት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገ-ወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታወቀ፡፡ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደዋል፡፡ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ አተኩሮ የተካሄደውን ውይይት ያስጀመሩት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሀመድ ናቸው፡፡ ከፍተኛ አመራሮቹ በቅርቡ በተቋሙና በአማራ ክልል አመራሮች ላይ የደረሰው አደጋ ታላቅ ቁጭት መፍጠሩን በመግለጽ በቀጣይ ድርጊቱ እንዳይደገም እንደሚሰሩ በውይይቱ ማጠቃለያ ባወጡት ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱና ለህዝቦች ሰላም መስዕዋትነት እየከፈለ የመጣ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው በቀጣይም የተለያዮ #ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገ-ወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፡ ሰራዊቱ ከምንጊዜም በላይ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት በሚያስችለው ቁመና ላይ እንደሚገኝና የተሰውት ጓዶች ህልፈት አባላቱን ለበለጠ #ጀግንነትና መስዋዕትነት የሚያነሳሳ እንጂ #የሚያዳክም እንዳልሆነ ገልጿል፡፡
ምንጭ፦ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት
@tsegabwolde @tikvahethiopia