TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ🔝በሀዋሳ ከተማ #የነዳጅ_እጥረት በመከሰቱ አሽከርካሪዎች መቸገራቸውን ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

በሀዋሳ ከተማ የተከሰተው #የነዳጅ_እጥረት መፍትሄ አላገኘም። ዛሬም በከተማይቱ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ይታያሉ።

በሀዋሳ ከተማ የሚገኝ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ስለ ነዳጅ እጥረቱ እንዲህ ብሏል...

"ከሌሊቱ 10 ሰአት #ተሰልፈን እስከ አሁን 1:45 ነዳጅ መቅዳት አልተጀመረም ከተማው ወስጥ 3 ማደያዎች ቤንዚል ቢኖራቸው #ማኔጅ የሚያደርግ አካል የለም በጣም ተቸግረናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝በከተማይቱ ያለው #የነዳጅ እጥረት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። ዛሬ ከማለዳው አንስቶ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች በተለያዩ ነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ለማየት ተችሏል።

#TIKVAHETHIOPIA(የሀዋሳ ቤተሰብ አባላት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

በወላይታ ሶዶ ከተማ ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ተቃሎ የነበረው #የነዳጅ_እጥረት ዳግም ማገርሸቱን በከተማይቱ የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። መንግስት ችግሩ የሚቃለልበትን መንገድም እንዲፈልግ ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የነዳጅ እጥረት በአዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው #የነዳጅ_እጥረት በአሽከርካሪዎች ላይ ጫና መፍጠሩን የታክሲና የባጃጅ አሽከርካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያጋጠመውን ወቅታዊ የነዳጅ አቅርቦት ችግር በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንደሚፈታ አመልክቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) አሽከርካሪዎች ከነዳጅ ማደያ ቤንዚን ለማግኘት በመቸገራቸው በእለት ኑሯቸው ላይ ጫና ማሳደሩን ጠቁመዋል። የእለት ገቢ እያገኙ ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ በመሆኑ ረጅም ሰዓት በነዳጅ ማደያ ተሰልፈው በማሳለፋቸው ገቢ እያገኙ እንዳልሆነ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ🔝በጅማ ከተማ #የነዳጅ_እጥረት መከሱትን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። መንግስት ችግሩን እንዲቀርፍም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ~ድሬዳዋ ቅርንጫፍ‼️

በሕገ-ወጥ መንገድ ከድሬዳዋ ተጭኖ ወደ ሐርጌሌ ሊጓጓዝ የነበረ ነዳጅና አምስት #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ አቶ #ሞገስ_አያሌው ለኢዜአ እንዳመለከቱት ከከተማው ሊወጣ ሲል የተያዘው 20ሺህ ሊትር ናፍጣ፣ 16 ጀሪካን የሞተር ዘይትና በድርጊቱ የተጠረጠሩት ግለሰቦች ናቸው፡፡ በተለይ ነዳጁ የተያዘው በአንድ የጭነት መኪና ከነተሳቢው በጄሪካን ተጭኖ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ነዳጁን በከተማው ከሚገኝ አንድ ነዳጅ ማደያ ገዝተው ሊያጓጓዙ የነበሩት ግለሰብና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ለግለሰቡ  ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ መሰጠቱ አግባብ  አለመሆኑን ያስረዱት ባለሙያው፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ነዳጅን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚከናወነውን እንቅስቃሴ በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም ሕገ-ወጥ ተግባር ለፖሊስ በማሳወቅ ትብብሩን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ነዳጁ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ጥቆማ ከሰጡት አንዱ ለኢ ዜ አ  እንዳስታወቁት በከተማዋ #የነዳጅ_እጥረት የሚከሰተው በሕገ ወጥ መንገድ በሚካሄደው ንግድ ነው፡፡ ”የቤንዚኑ ችግር ሳይፈታ ናፍጣ ቢወደድ ሌላ ችግር ስለሚፈጥር ጉዳዩን ጠርጥረን ለፖሊስ አሳውቀናል። ትብብራችንም ይቀጥላል”ብሏል፡፡

#ሐርጌሌ በሶማሌ ክልል ከድሬዳዋ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ መንገድ ሊጓዝ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia