TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጀርመን ለምትገኙ‼️

በነገዉ እለት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ በፍራንክፉርት «ኮሜርስ አሬና» በተባለዉ ስቴዲየም ከኢትዮጵያዉያንና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ይገናኛሉ። ተሳታፍዎቹ ከጀርመን ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የአዉሮጳ አገራት በዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ። በዚህ ዝግጅት በግምት 25 ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ወደፊት የኢትዮጵያ ጉዞም ወሳኝ በአዉሮጳ ዉስጥ
በርካታ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን እና የፖለቲካ አዋቂዎች በመኖራቸዉና አንድ አንዶች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፊት ለፊት መወያየት ባለመቻላቸዉ ብዙዎችን አስኮርፎአል። የፓሪስ ፈረንሳይና የበርሊን ጀርመን ጉብኝት በዋናነት በሁለት አገሮች የሚደረግ መንግስታዊ ጉዳይ መሆኑን የፍራንክፉርት ጉብኝት አስተባባሪ ድያቆን ዳንኤል ክብረት ተናግረዋል። ይሁን እንጅ በነገ እለት በፍራንክፉርት ከኢትዮጵያዉያንና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመገናኘት ተጨማሪ ቀን መያዙን ድያቆን ዳንኤል ገልፀዋል።

በነገዉ ሥነ-ስረዓት ላይ ታዳሚዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸዉም እንደ #ማሳሳብያ የሚከተሉትን ነጥቦች ዝርዝረዋል፤

- የፍተሻዉን ጊዜ በጣም ለማሳጠር ትልልቅ ሻንጣዎችን ይዞ ከመምጣት ታዳሚዎች መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

- ቀጠሮዉን አክብሮ በግዜ መገኘት አስፈላጊ ነዉ።

- ሕጻናትና ልጆችን የያዙ ቤተሴቦች የሕጻናት መቀመጫ ጋሪዎቻቸዉ የሚሆኑበት የተወሰነ ቦታ ተዘጋጅቶአል። ቦታዉ ግን ይህን ያህል ብዙ አይደለም።

- ከሕፃናት ምግብ በስተቀር ምግብ ይዞ ወደ ስታድዮም መግባት አይቻልም። በአንጻሩ ምግብ መጠጥ መሸጫ ቦታ በቂ ተዘጋጅቶአል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia