TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 22-23 ተብሎ የነበር ቢሆንም የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። 24/01/2011

©Birh
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሰልጠን አለብን‼️
.
.
በአውሮፓ እና አሜሪካ ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ስጋት #መጤ ናችሁ ሳይባሉ፤ ነገ ከዚህ ልቀቁ እንባላለን ብለው ሳይሸማቀቁ ይኖራሉ፥ እኛ የእለት ጉርሳችንን በአግባቡ ሳንሞላ የራሳችንን ወገን ጠልተን #በመሀይምነት ታውረን ሰዎችን ከቄያቸው እናፈናቅላለን!
.
.
ሁሉም አካል ከዚህ ከወረደ አስተሳሰብ የምንወጣበትን መንገድ ሊያመቻች ይገባል! በተለይ የሀይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና መምህራን ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ።

ሁላችንም በየቤታችን ስለሰውነት ክቡርነት ልንነጋገር ይገባል። የሌሎች እድገት እና ከኛ ርቀው መሄዳቸው ሊቆጨን እና ሊያስቀናን ይገባል።

"#እናስተውል ወደፊት አንድ እርምጃ መራመድ ቢያቅተን ባለንበት ለመቆም እንሞክር ወደ ኋላ እንደመመለስ #ውድቀት የለምና።"

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ ኢንዲስትሪ ፓርክ⬆️

"ሀይ ፀግሽ በአሁን ሰዓት የተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሀዋሳ ኢንድስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ይገኛሉ። ሳሚ ነኝ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የሲዳማ ብሄራዊ ንቅናቄ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተቀብሎ ዛሬ ወደ ሀገር #ገብቷል፡፡ ከለንደን እና ከአሜሪካ የገቡት የግንቅናቄው ስራ አስፈፃሚ አባላት ዛሬ ከማለዳው 1 ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ #የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን እሁድ መስከረም 27 መርቀው ይከፍታሉ፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ‼️ሀያትን ለመታደግ ቴኬቶቹን በዚህ ስልክ ቁጥር በመደወል መግዛት ትችላላችሁ 0989986759

ከኢትዮጵያ ቡና የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች!

#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬆️

በእዩ ፒክቸርስ የሚዘጋጀው ዳላክ አካታች #የአካል_ጉዳተኞች ፋሽን ሾውና ውድድር መስከረም 12 እና 13 የመክፈቻ ፕሮግራሙን በጁፒተር ሆቴል አካሂዷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፦
+2519 3667 6365
@DFWBYEYOU

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰኔ 16ቱ ጥቃት⬇️

በሰኔ 16ቱ የቦምብ #ፍንዳታ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዢ #ተስፋዬ_ኡርጌ ፖሊስ በቢሮው አገኘሁት ያለወን #ቦምብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር ለማመሳከር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀበትን ምክንያትና የተጠርጣሪውን አስተያየት አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስ ምርመራችንን አጠናቀን ለፌዴራል አቃቢ ህግ ያስረከብን ቢሆንም አቃቢ ህግ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቢሮ ውስጥ ያገኘነውን ቦንብ መስቀል አደባባይ ከፈነዳው ቦምብ ቅሪት አካል ጋር በቴክኒክ ለማመሳከር ተጨማሪ ማስረጃ ይቅረብልኝ ማለቱን ተከትሎ ለፌዴራል ፖሊስ ፈንጅ አምካኝ ኦፕሬሽን ዲቪዢን ደብዳቤ ልከናል ሲል አብራርቷል።

ይህንን የቴክኒክ ምርመራ ምላሽ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል።

ጉዳዩ ያለ አግባብ እየተራዘመ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በበኩላቸው ፍርድቤቱ አጭር ቀጠሮ ሰጥቶ ለመጨረሻ ትዛዝ ይስጥልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

ፍርድቤቱም በተጠየቀው የጊዜ ገደብ የቴክኒክ ምርመራው ለምን #አልተጠናቀቀም የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፥ ፖሊስም ደብዳቤ ልከን ምላሽ ስላልተሰጠ እየጠበቅን ነው ሲል አብራርቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎትም ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራውን ይዞ እንዲቀርብ ለተጨማሪ ስምንት ቀን ቀጠሮ በመስጠት ለጥቅምት አራት(4) ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ⬆️በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2011 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ሪዝደንሲ የመግቢያ ጊዜ October 15/2018 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ያዘጋጀው ተቋማዊ መዋቅር በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ መህመድ (ዶ/ር) #በመፅደቁ፣ በድጋሚ የሠራተኞች #ድልድል ሊያካሂድ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሰኞ መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሚኒስቴሩ ማኔጅመንት ካውንስል በሰጡት መመርያ፣ ድልድሉ ከሌሎች መመዘኛዎች በተጨማሪ ብቃትና ክህሎት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የሠራተኛ ምደባውን ለማካሄድ የማኔጅመንት አባላትና የሠራተኛ ተወካዮች የያዘ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ማቋቋሙን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia