TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

ቦሌ መንገድ በሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሚኖሩበት ሕንፃ አካባቢ መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ሌሊት በነበረ ተኩስ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የፓርላማ አባላቱ በሚኖሩበት ሕንፃ በጥበቃ ላይ የነበረ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ባልታወቀ ምክንያት ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ በከፈተው ተኩስ የሦስት ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ፣ ሌሎች የፀጥታ አስከባሪዎች #ጥቃቱን በፈጸመው የፖሊስ አባል ላይ #ዕምርጃ በመውሰድ የአባሉ ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ አባሉ የሦስቱን ሰዎች ሕይወት ከማጥፋቱ ባሻገር፣ አሥር ያህል የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላትም በፌዴራል ፖሊስ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑ ታውቋል፡፡

ጥቃቱን የፈጸመው የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሊቱን ሙሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች #ሲተኩስ ስለነበር፣ አካባቢው #ውጥረት ነግሶበት ማደሩ ታውቋል፡፡ በጥቃቱ ምክንያትም የቦሌ ዋና መንገድ እስከ ማለዳው 3፡00 ሰዓት ድረስ ተዘግቶ ቆይቷል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia