TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ማሳሰቢያ

በያዝነው ክረምት በተከዜ ወንዝ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድባችን እየገባ ያለው የውኃ መጠን የሞላ በመሆኑ ለግድቡ ደህንነት ሲባል የውኃውን መጠን ከነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ መቀነስ አስፈልጓል፡፡

ስለሆነም ከግድቡ በታችኛው እና በላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ማለትም በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር በመሃከለኛው ዞን የሚገኙ ወረዳዎች ማለትም በጣንቋአበርገሌ፣ በቆላ ተንቤን፣ በላዕላይማይጨው፣ በታህታይ ማይጨው፣ በመረብ ለሄ በሰሜን ምዕራባዊ ዞን ደግሞ በአሰገደ ጺምበላ፣ በላዕላይ አዲያቦ፣ በመደባይ ዛና፣ በታህታይ አዲያቦ፣ በታህታይ ኾራሮ፣ በፀለምቲ እንዲሁም በምዕራባዊ ዞን በካፍታ ሁመራ፣ በፀገዴ፣ በወልቃይት በተያያዘ ሁኔታም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር በዋግኽምራ ዞን ስር በአበርገሌ ወረዳ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በፀለምት ወረዳ በአጠቃላይ የተከዜ ወንዝ አዋሳኝ ቀበሌዎች እና በአካባቢው ነዋሪ ህዝቦች ከወዲሁ ይህንኑ #በመገንዘብ በሰውም ሆነ በእንሰሳት ላይ በሚለቀቀው #ደራሽ ውሃ #ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን #ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ለማሳሰብ ይወዳል፡፡

📌ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዳውሮ ዞን⬆️

በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ዛሬ ማለዳ ላይ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ12 ሰዎች #ህይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከፍተኛ #ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የወረዳዉ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የመሬት መንሸራተቱ በወረዳዉ ጉዛ ቀበሌ ዘማ መንደር በሶስት መኖርያ ቤቶች ላይ መከሰቱን የጽህፈት ቤቱ ኃለፊ ሻምበል አልታዬ አለሙ ገልፀዋል፡፡

በአደጋው ከሞቱት 12 ሰዎች መካከል በህብረተሰቡ ተሳትፎ የ10ሩ አስክሬን የተገኘ ሲሆን፥ የሁለቱ አስክሬን ባለመገኘቱ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉን አራት ግለሰቦች ወደ ተርጫ ሆስፒታል በመውሰድ የህክምና ዕርዳት እንዲያገኙም እየተደረገ ነዉ፡፡

በአደጋዉ ወደ 1 ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን፥ በቀጣይ ጊዜያትም በስፍራዉ ያሉ ቤቶች ጥንቃቄ ካልተደረገላቸዉ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክላሲ ውሀ⬆️

ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ #ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ በመረጋገጡ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውለው የንግድ ሚኒስቴር አሳሰበ።

የሚኒስቴሩ የገበያና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት እንደተናገሩት፥ በላይ ኢንዱስትሪያል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚያመርተው ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ ተረጋግጧል።

ከ2007 እስከ 2009 ዓመተ ምህረት በተደረገ የጥራት ፍተሻ ምርቱ በተደጋጋሚ የጥራት ጉድለት የታየበት በመሆኑ እንዲታገድና ከገበያ #እንዲሰበሰብ መደረጉንም ነው ዳይሬክተሩ ያስታወሱት።

ድርጅቱ የምርት ጥራቱን እንዲያስተካክል የውዴታ ግዴታ እንዲፈርም በመደረጉ ማስተካከሉ ተረጋግጦ ታህሳስ 2009 ዓ.ም እገዳው ተነስቶለት ወደ ስራ ገብቷል።

ሚያዚያ 2010 ዓመተ ምህረት በተደረገ የገበያ ኢንስፔክሽን ስራ የምርቱ ናሙና ተወስዶ በተደረገው የቤተ ሙከራ ፍተሻ የታሸገ ውሃው በድጋሚ የጥራት ደረጃውን ያላሟላ ሆኖ ተገኝቷል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ክላሲ የታሸገ ውሃን ከመጠቀም #እንዲቆጠብ የንግድ ሚኒስቴር ለfbc በላከው መግለጫ አሳስቧል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ📌ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ #ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ በመረጋገጡ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውለው የንግድ ሚኒስቴር አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢሕአፓ⬇️

በነገው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች በቀይ ሽብር ወቅት #ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች እንደሚጎበኙ አስታወቁ፡፡ ከጉዳተኞች ጋር በቋሚነት የሚያገናኝ ኮሚቴ የመመስረት ዕቅድ እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡ ቡድኑ ነገ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረግለት አቀባበል እንደተጠናቀቀ በቀጥታ ወደ ቀይ ሽብር ሠማዕታት ሙዚየም ያመራል፡፡ የኢሕአፓ አመራሮች በሀገር ቤት ቆይታቸው በትግሉ የተሰዉ የኢሕአፓ አባላት ገድል የሚዘከርበትን መንገድ ያመቻቻሉ ተብሏል፤ ከመንግስት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

©ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች #የጸጥታ ችግር መከሰቱ ተገለጸ።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞንና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች በተከሰተው የጸጥታ ችግር በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡

አሁን ለተከሰተው የጸጥታ ችግር መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች በምዕራብ ወለጋ ዞን ቢላ አሙማ አገሎ በተባለው ስፍራ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የከማሺ ዞን አመራሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት 4 የከማሺ ዞን አመራሮች #መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡

በእነዚህ ታጣቂዎች ግድያ የተፈጸመባቸው የከማሺ ዞን አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ከተላኩ አመራሮች ጋር ከዚህ ቀደም ከክልሉ #ተፈናቅለው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ወደነበሩበት #በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ በአሶሳ ከተማ ተወያይተው ወደ ከማሺ ዞን በመመለስ ላይ እያሉ ነበር ተብሏል፡፡

በከማሺ ዞንና እንዲሁም በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞን ስር በሚገኙት የሳስጋ፣ ድጋ፣ ሐሮ ሊሙ፣ ሊሙ፣ ቦጂ ብርመጂ ወረዳዎችና በሌሎች አከባቢዎች በተከሰተው በዚህ ግጭት ከነቀምቴ ሆስፒታል በተገኘው መረጃ መሰረት እስከ አሁን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ በርካቶች ቆስለዋል፣ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል፡፡

በተከሰተው ችግር ሳቢያ በቤንሻንጉል ክልል ሲኖሩ የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ተፈናቅለው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ወሰን አካባቢ ወደሚገኙት የኦሮሚያ ወረዳዎችና ወደ ነቀምቴ ከተማ መሰደዳቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በአከባቢው የተከሰተውን ችግር #ለማረጋጋት የጸጥታ ኃይሎችና የአስተዳደር አካላት፣ የፌዴራል መንግስትና ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ቢሮው ገልጿል፡፡

በዜጎች ላይ ለደረሰው ጉዳት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ገልጿል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላላም ጃለታ በበኩላቸው፣ በአከባቢው የጸጥታ ችግር መከሰቱን አምነው፣ በከማሺ ዞን የሚገኙት ነዋሪዎች ጥቃት ይደርስብናል በሚል ፍርሃት የጉሙዝ ተወላጆች ቤታቸውንና ንብረታቸውን ትተው ወደ ጫካ #እየተሰደዱ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ደግሞ ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች እየተሰደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር በርካታ የኦሮሞ ማህበረሰብና የጉሙዝ ተወላጆች ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ራያ አላማጣ⬇️

የራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ #ሊታፈን እንደማይገባ የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።

የራያ አላማጣ ነዋሪዎች ማንነታችን አማራ በመሆኑ ሊከበርልን ይገባል ሲሉ በተደጋጋሚ እየጠየቁ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ እንግልት እና ወከባ እየደረሰባቸው መሆኑን ነው የሚናገሩት። አላማጣ ላይ ከትናንት ምሽት ጀምሮ የፀጥታ ችግር መኖሩንና #ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውንም ከአካባቢው የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በአካባቢው ስለሌሉ መረጃ መስጠት እንደማይችሉ ነው የተናገሩት።

የቆቦ ከተማ ነዋሪዎችም ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ድርጊቱን አውግዘዋል። "ማንነታቸውን ስለጠየቁ መብታቸው ሊታፈን፣ ሊንገላቱ እና ሊዋከቡ አይገባም" ሲሉ ነው የጠየቁት።

ከዚህ በፊት ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው የትግራይ ክልል መንግስት "ጥያቄው ከማንነት ጋር አይያያዝም" ማለቱ ይታወሳል።

ነዋሪዎቹ ግን ጥያቄያቸው የማንነት እና የነፃነት መሆኑን ነው የሚያስረዱት። በሰልፉ "ጣናና ላል ይበላን እንታደግ!" የሚሉ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።

የሰሞኑን የሚኒስትሮች ሹመት አሰጣጥም ተቃውመዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አራት ኪሎ በግንባታ ላይ ያለ ህንጻ #ተደርምሶ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።

በተለምዶ አራት ኪሎ እሪ በከንቱ በሚባለው አካባቢ በግንባታ ላይ ያለ ህንጻ መጠነኛ የመደርመስ አደጋ ደርሶበት በሰራተኞች ላይ #ጉዳት ደረሰ።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በደረሰው በዚሁ አደጋ በግንባታ ስራው ላይ በነበሩ #ስድስት ሰራተኞች ላይ ጉዳት ደርሶ ወደሆስፒትል መወሰዳቸው ታውቋል።

የአካባቢው ፓሊሶች ለኢትዮጵያ ፕሬሥ ድርጅት እንደገለጹት በአደጋው ህይወቱ ያለፈ ሰው የለም። የአደጋውም መንስኤ እየተጣራ ነው።

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
ፎቶ እና ቪድዮ፦ TikvahEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደብረማርቆስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ #ጉዳት በመድረሱ ደብረ ማርቆስ ፣ፍኖተ ሰላምና ብቸና ከትናንት ጀምሮ ኃይል ተቋርጧል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አባያ ሀይቅን እንታደግ‼️በአባያ ሀይቅ ላይ እየደረሰ ያለውን #ጉዳት ለህዝብ ለማስገንዘብ እና ትኩረት እንዲሰጠው እየተደረገ የሚገኘው የ3 ቀን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ 2ኛ ቀኑን ይዟል።

"የእንቦጭ አረምን ከሃይቁ እናስወግድ"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወላይታ ሶዶ⬇️

በወላይታ ሶዶ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ችግር  ንብረት ለወደመባቸውና #ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች በክልሉ መንግስት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ #ድጋፍ ተደረገ፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ተጎጂዎችም ድጋፉ ተስፋ ከመቁረጥ እንዳዳናቸው ተናግረዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ #ባታላ_ባራና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር የንብረት ጉዳት መድረሱን አስታወሰዋል፡፡

ከተጎጂዎች መካከል አብዛኞቹ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች የተሰማሩ ሲሆን በንግድ ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤቶችና በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት የማጣራትና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መሰራቱን ገልጸው በተገኘው መረጃ መሰረት ለ89 ተጎጂ ግለሰቦች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተጎጂዎቹ ራሳቸው ባቀረቡትና ከአካባቢው ህብረተሰብ በተሰበሰበ መረጃ እንዲሁም በንግድ ፈቃዳቸው ላይ ያስመዘገቡት ካፒታልና የገቢ ግብር ማህደርን መነሻ በማድረግ የማጣራት ሥራው መከናወኑንም አቶ ባታላ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት የክልሉ መንግስት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎ ከ11 ሚሊዮን 478 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤና የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ታልጎሬ ታደሰ በበኩላቸው የተሰበሰበውን መረጃ መሰርት በማድረግ እንደጉዳታቸው መጠን ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

“እስከ 10 ሺህ ብር ጉዳት ያቀረቡ 34 ተጎጂዎች ገንዛባቸው ሙሉ በሙሉ እንዲተካላቸው የተደረገ ሲሆን ቀሪዎቹ 55ቱ የጉዳታቸውን 50 በመቶ እንዲያገኙ ተደርጓል” ብለዋል፡፡

ባለሁለት ጎማ የሞተር ብስክሌት ለተቃጠለባቸው ወገኖች ምትክ እንዲገዛ መወሰኑንና በመኖሪያ ቤታቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ደግሞ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው ተጎጂዎች መካከል ወይዘሮ ምህረት መሸሻ በከተማዋ ጤና ጣቢያ ሰፈር የህጻናት አልባሳትና ኮስሞቲክስ ይነግዱ እንደነበረና በዕለቱ በድንገት በተፈጠረው ችግር መዘረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ወይዘሮ ምህረት ችግሩ ከደረሰ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ቢቆዩም ድጋፉ ሥራቸውን ዳግም ለመጀመር የሚያስችልና ተስፋ ከመቁረጥ እንደታደጋቸው ገልጸዋል፡፡

በሶዶ ከተማ መሃል ከተማ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ ኑሪ ባዲ በበኩላቸው ድንገት በተፈጠረው ችግር  በህገ-ወጦች ቢዘረፉም የመንግስት ድጋፍ ዳግም ወደስራቸው ለመመለስ እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡

ችግሩ ሰላም የማይፈልጉና በሁከት ሰበብ ለዘረፋ የተዘጋጁ ነውጠኞች ያደረጉት መሆኑን ጠቁመው የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ ነዋሪውና የከተማው ጸጥታ ኃይል ያደረገው ርብርብ የማይረሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማዋ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች መንግስትና የከተማዋ አስተዳደር ከቃል ባለፈ ተጨባጭ ድጋፍ ባለማድረጋቸው ተቸግረናል ሲሉ ያቀረቡትን ቅሬታ ኢዜአ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምስራቅ ወለጋ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው #ህይወትና ንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለfbc አንደተናገሩት፥ በግጭቱ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስን ጨምሮ የበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አልፏል።

እንዲሁም ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ በርካታ ንብረት መውደሙንም ነው አቶ ዴሬሳ የተናገሩት።

ችግሩ ያጋጠመውም ባሳለፍነው ማክሰኞ ህዳር 18 2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ አርቁምቤ በሚባል አካባቢ መሆኑንም ነው የቢሮው ምክትል ኃላፊ ያስታወቁት።

በግጭቱም በአካባቢው ነዋሪዎች እና በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ላይ አሰቃቂ ወንጀል ተፈጽሟል ያሉት አቶ ዴሬሳ፥ በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይደረጋልም ብለዋል።

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስክሬን በትናንትናው እለት ነቀምቴ ከተማ ሲገባ ህዝቡ ሰልፍ በመውጣት #ስሜታዊ በመሆኑ የአንድ ሰው #ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል።

ምክትል ኃላፊው አቶ ዴሬሳ ተረፈ፥ በምእራብ ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዋነኛ ምክንያት የክልሉን እና የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ እንዲሁም አሁን በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሯሯጡ አካላት ናቸው ብለዋል።

የእነዚህ አካላት እቅድም እንደ ኦሮሚያ ክልል እና እንደ ሀገር እየመጣ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍ በመሆኑ፤ ህዝቡ ከስሜታዊነት በመውጣት መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚወስደውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዶች ተከፍተዋል‼️

በአፋር የነበረው የመንገድ መዝጋት #አድማ #እንደተጠናቀቀና መንገዶች #እንደተከፈቱ ተገልጿል፡፡ ሶማሊ ነዋሪዎች የሚበዛባቸው ሶስት ቀበሌዎች ላይ እየተፈጠረ ያለውን #ግጭት ለማርገብ በሚል ከቀበሌዎቹ የአፋር ክልል ልዩ ሃይል #እንዲወጣ መደረጉን #በመቃወም ነበር የክልሉ ወጣቶች ተቃውሞ የጀመሩት፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ተጓዦችንም ሆነ ንብረቶቻቸው ላይ ምንም አይነት #ጉዳት_ያላደረሰ ነበር፡፡ከአዋሽ ወደትግራይ የሚወስደው መንገድ ትላንት ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተከፈተ ሲሆን ከመሃል አገር ወደምስራቅ ኢትዮጵያና ወደ ጂቡቲ የሚወስዱት መንገዶችም ተከፍተዋል፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀላባ ከተማ‼️

በደቡብ ክልል ሀላባ ከተማ ትናንት በተሰራጨ #ሀሰተኛ_ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች በከተማው በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ላይ #ጉዳት ማድረሳቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉት በከተማው #የማቃጠልና የንብረት #ማውደም ድርጊቱ የተፈጸመው ሌንዳ በር እና ዋጃ በር በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ በሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት ላይ ነው፡፡ በስፍራው ነበርኩ ያሉ እንድ የከተማው አዛውንት ጥቃቱ የተጀመረው በድራሜ ከተማ መስኪድ መቃጠሉንና ኢማም መገደሉን የሚገልጹ ወሬዎች ከተናፈሱ በኋላ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በቤተክርስቲያናቱ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ መመልከታቸውን ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል፡፡

የጀርመን ድምፅ ራድዮ በሥልክ ያነጋገራቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ #ዓለሙ_ሌንቢሶ ደግሞ በከተማው በተሳሳተ ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች አንድ ቤተክርስቲያን በእሳት ያቃጠሉ ሲሆን በሌሎች ሰባት ቤተክርስቲያናት ላይ ደግሞ ንብረቶችን የማውደም ድርጊት መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እጅ ከፍንጅ የተያዙ 20 ግለሰቦችን ጨምሮ 63 ተጠረጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆሙት ሃላፊው የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽነርም ጥቃቱን ለመከላከል ጥረት ባለማድረጋቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምንጫቸው ባልተረጋገጡ ወሬዎች በመነሳሳት የሚፈጸሙ የደቦ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ በቅርቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቀደም ባሉት ጊዚያት ደቦ እርሻን በህብረት ለመሥራት ይውል እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ጸብም በደቦ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ኮተቤ ዩኒ ቨርሲቲ አካባቢ በግንባታ ላይ የነበረ #ድልድይ አርማታ #ተደርምሶ 12 ሰዎች #ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ #ሆስፒታል ተወስደዋል። በአደጋው #ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ #የታወቀ ነገር የለም።

Via EBC
ፎቶ፦m & jes(tikvahethiopia)
@tsegabwolde @tikvahethiopia