TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሐረር⬆️ሐረር ከተማ ላለፉት ስድስት ወራት #ውሃ ተጠምታለች፣ በቆሻሻም ታፍናለች - የዚህ ምክንያቱ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች በ5 ቀን ውስጥ 10 ሚሊየን ብር እንዲከፈላቸው በመጠየቅ የውሃ መስመሩን በመስበራቸውና ቆሻሻም አናስደፋም በማለታቸው ነው። እስካሁን ድረስ ከምሰራቅ ኦሮሚያ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ቄሮዎች ጋር ምክክር ቢደረግም መፍትሄ አልተገኘም። ወጣቶቹ ከውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ሰራተኛው ቁልፉን #ነጥቀው ወስደዋል፣ ሞተሮቹን አጥፍተዋል፣ የውሃ መስመሩንም ሰብረው ውሃው በከንቱ እየፈሰሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐረር⬆️ሐረር ከተማ ላለፉት ስድስት ወራት #ውሃ ተጠምታለች፣ በቆሻሻም ታፍናለች - የዚህ ምክንያቱ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች በ5 ቀን ውስጥ 10 ሚሊየን ብር እንዲከፈላቸው በመጠየቅ የውሃ መስመሩን በመስበራቸውና ቆሻሻም አናስደፋም በማለታቸው ነው። እስካሁን ድረስ ከምሰራቅ ኦሮሚያ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ቄሮዎች ጋር ምክክር ቢደረግም መፍትሄ አልተገኘም። ወጣቶቹ ከውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ሰራተኛው ቁልፉን #ነጥቀው ወስደዋል፣ ሞተሮቹን አጥፍተዋል፣ የውሃ መስመሩንም ሰብረው ውሃው በከንቱ እየፈሰሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀሰት ዋጋው‼️

እሳት፣ ውሃ፣ እውነትና ሃሰት የሚባሉ ጓደኛሞች ነበሩ። በዚህ ጓደኝነታቸው ግን ሃሰት ብዙም አልተደሰተም። ጥምረቱም ደስተኛ አላደረገውም። ስለዚህም #አንድነታቸውን ማበላሸት ፈልጎ እንዲህ አለ፤ «ለምን ወደ አንድ ስፍራ ተጉዘን እያንዳንዳችን የራሳችንን ግዛት አንመሰርትም? ስለዚህ ተነስተን አብረን እንጓዝ።»

ሁሉም በሃሳቡ ተስማምተው ሲሄዱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ #ሀሰት ወደ #ውሃ ጠጋ ብሎ «እሳት ሳሩን፣ ደኑንና ቁጥቋጦውን የሚያቃጥል ቀንደኛ ጠላታችን ስለሆነ ለምንድነው ከእርሱ ጋር ግዛት ፍለጋ የምንሄደው?» አለው። ውሃም «ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?» ሲል መልሶ ጠየቀው።

ሃሰትም ቀበል አድርጎ «ልንገድለው እንደሚገባ ግልፅ ነው፤ እሳትን የማጥፋት ብቸኛ ኃይል ያለህ ደግሞ አንተ ነህ። እናም ቁጭ ሲል ጠብቀህ እላዩ ላይ ራስህን በመርጨት አጥፋው» አለው። ውሃም «ራሴን መሬቱ ላይ ከረጨሁ ተመልሼ ውሃ መሆን አልችልም» አለ። ሀሰትም «ችግር የለውም፤ ተረጭተህ እንዳትበታተን የተወሰኑ ድንጋዮች በዙሪያህ አኖርና በኋላ እሰበስብሃለሁ» አለው።

በዚህ ጊዜ የተሸረበበትን ተንኮል ያልጠረጠረው እሳት ቁጭ ሲል፤ ውሃው አንድ ጊዜ በላዩ ላይ ሲረጭ ሃሰት ድንጋዮች ዙሪያውን አድርጎ ውሃውን ከሰበሰበውና እሳትን ካስወገዱ በኋላ አብረው መጓዝ ጀመሩ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሃሰት ውሃውን «ለምን እዚህ ገደል አፋፍ ላይ ቁጭ ብለህ በተፈጥሮ ውበት አትዝናናም?» አለው። ውሃም አፋፉ ላይ ቁጭ ሲል ሃሰት ቀስ ብሎ ተነስቶ ውሃ የተቀመጠባቸውን ድንጋዮች ከስሩ ሲለቅማቸው ውሃው በዚያው ተበታትኖ ጠፋ።

በመጨረሻም ሃሰት እውነትን ማጥፋት ነበረበትና ወደ አንድ ትልቅ ተራራ በተቃረቡ ጊዜ ሃሰት እውነትን ከተራራው ግርጌ ቁጭ በል ብሎት ከተራራው አናት ላይ ትልቅ አለት ቁልቁል በመልቀቅ እውነትን ሊጨፈልቀው ሲል እውነት ቀልጠፍ ብሎ ማምለጥ በመቻሉ አለቱ ተንከባሎ ሲፈረካከስ ከውስጡ አልማዝ፣ ወርቅና ልዩ ልዩ የከበሩ ማዕድናት ወጡ። ሃሰትም የእውነትን አስከሬን ሊመለከት በመጣ ጊዜ እነዚህን ሁሉ የከበሩ ድንጋዮች አየ። እናም «እነዚህ ሁሉ ከየት መጡ?» ብሎ ጠየቀ። እውነትም «አለቱ እላዬ ላይ ሲወድቅ እነዚህ ማዕድናት ወጡ» ሲል መለሰለት። በዚህ ጊዜ ሃሰት «አሁን ደግሞ እኔ ከተራራው ግርጌ ልቀመጥና አንተ አለቱን በላዬ ላይ ልቀቅብኝ» አለው። እናም እውነት ወደ ተራራው ጫፍ ወጥቶ ትልቅ አለት ወደታች በለቀቀ ጊዜ አለቱ የሃሰት አናት ላይ አርፎ ሃሰትን ጨፈላልቆ ገደለው። ይህ የሚያሳየው ሀሰት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍልና እውነት ፈተና ቢገጥመውም በመጨረሻ አሸናፊ እንደሚሆን ነው። በተለይ አሁን በሀገራችን የሀሰት መረጃ እያደረሰ ካለው ጉዳት ጋር ስናነጻጽረው ትልቅ መልዕክት ይሰጠናል።
የማገናዘብና ትክክለኛውን መረጃ አውቆ ወደ ተግባር መግባት ላይ ብዙዎች ችግር አለባቸው። ለዚህ ደግሞ መሰረቱ የሀሰት ወሬ ነው። ይህንን አድርግና ይህንን ታገኛለህ የሚለው የተሳሳተ መስመር ብዙዎችን ባልተገባ መንገድ እንዲጓዙ አድርጓቸዋል። ሰው በሰው ላይ በክፋት አስነስቷል። እውነቱ እንደ እውነትነቱ መጨረሻ ማሸነፉን የሚዘነጋ ሰው አይጠፋም።

በእርግጥ በሌሎች ስህተት ውስጥ አለመሳተፍ ዋጋ ይኖረው ይሆናል። ልክ እንደ እሳት ማለት ነው። ነገር ግን እንደ በሀሰት ዝም ብሎ ሰዎችን ማባላትና ማገዳደል መጨረሻው ራስን ለጉዳት ይዳርጋል፡፡ የህግ ተጠያቂነትም ያስከትላል። በአገሪቱ ውስጥ እሳትን የሆኑ፣ ሀሰትን የሆኑ እንዲሁም እውነትን የሆኑ ሰዎች አሉ።

እሳትን የሆኑት የሚደረገውን የማያውቁ የራሳቸውን አለም ብቻ የሚኖሩ ናቸው። ሀሰትን የሆኑት ደግሞ የሰዎች ሰላም ማጣትና መባላት የሚያስደስታቸው፤ ሁሉ ነገር የእኔ ብቻ የሚሉ፤ ‹‹እኔ ከሌለሁ ሰርዶ አይብቀል›› እንዳለችው እንስሳ ናቸው። እውነትን የሆኑት ግን ለአንዲት አገር ለውጥ የቆሙና የአገር መለወጥ የእኔ ለውጥ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው።

በአንድ አገር ውስጥ የተለያየ ፍላጎት፣ የተለያየ ርዕዮተ አለምና፣ የተለያየ የትግል ስልት ይኖራል። ሆኖም አንድ ነገር ላይ ግን መግባባት ያስፈልጋል። የሁሉም ጥረት እውነትን ለመገንባት መስራት መሆን አለበት። ምናልባት አንዳንዶቹ ይህ እውነት ተግባራዊ ሆኖ ላያዩት ይችላሉ። ግን አሻራቸው ይኖርበታል። ለቀጣይ ትውልድም መልካም ታሪክ ማስተላለፍ ይችላሉ። በእውነት ለመኖርና ሃገርን ለመገንባት እውነትን መስራት ነው የሚያስፈልገው።

«ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ መጀመሪያ አንተው ራስህ ሁነው» እንዲል ማኅተመ ጋንዲ፤ ለለውጥ በቆረጡ፣ መለወጥ እንችላለን ብለውም በሚያስቡ፣ ከዕለት ጉዳይ አልፈው ታላቁን ሥዕል ለማየት በሚችሉ ሰዎች እውነትን ገንብቶ አገርን በለውጥ ጎዳና ውስጥ ለማስኬድ መጣር ይገባል። ለዚህ ደግሞ ስለ እውነት ሁሉም በእኩል ደረጃ፣ አቅም፣ ችሎታ፣ ዕውቀት እና ሥልጣን መሟገትና መስራት አለበት። ምክንያቱም ሀሰተኞች ለራሳቸውም ሆነ ለአገር አይጠቅሙም፤ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታቸው በእውነት መረታት ነው፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጥሪ ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፦

•ዲላ ከተማ እና አከባቢው ነዋሪዎች
•ዲላ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም ካምፓስ ተማሪዎች

#የTIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት በጌዴኦ ላሉ ተፈናቃዮች ከዲላ ከተማ ወጣቶች ጋር በመሆን እግዛ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረግን እንገኛል።

በመሆኑም...

በዲላ ከተማ እና አካባቢዋ የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የድጋፍ አይነቶች ድጋፍ እንድታደርጉ በትህትና እንለምናችኃለን፦

#ምግብ

•ሩዝ
•ፓስት
•ማካሮኒ
•የተለያዩ ዱቄቶች
•ጥራጥሬዎች

#አልባሳት

•የተለያዩ አልባሳትን(ለህፃናት፣ ለሴቶች...)

#የመኝታ_ቁሳቁሶች

•ፍራሽ
•አንሶላ
•ትራሳ

#የንፅህና_መጠበቂያዎች

•ሞዴስ
•ዳይፐር
•ሳሙና
•አሞ

#ውሃ

የዲላ ወጣቶች በያላችሁበት ይመጣሉ፦

1. ቢኒይም ሽፈራው፦ 0911-991503
2. ሰብስቤ ጌታሁን፦ 0949-162551
3. ነፃነት ሰዪም፦ 0911-736545
4. እዮኤል ሰብስቤ፦ 0916-177279
5. ሜላት እንደሻው፦ 0942-078911
6. ማሙሽ ረጋሳ፦ 0916-445167
7. ዳንኤል ፀጋዬ፦ 0926-499567
8. ነብዩ ዶዬ፦ 0937-218667
9. ወገኔ ወረቅነህ፦ 0916-862236
10. አንዋር ከድር፦0930-655275

እንዲሁም፦ ሰናይት ሱፐር ማርኬት በመሄድ ማስቀመጥ ትችላላችሁ!

የሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግር የኔም፣የንተም፣ የንቺም፣ የናንተም ችግር ነው!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Wolkite ዛሬ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ደቡብ ክልል፣ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ስለማድረጋቸው አሳውቀዋል። ውይይቱን ተከትሎ ፤ " የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው። " ያሉ ሲሆን " በዛሬው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል። በየደረጃው…
ምን ተጠየቁ ?

ዛሬ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከህብረተሰቡ ጋር የተወያዩት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተሳታፊዎች በክልል መደራጀት ጥያቄ፣ የልማት ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

የክልልነት ጉዳይን በተመለከተ አንድ ተሳታፊ አባት "የክልሉ ጉዳይ መቼ፣ እንዴት፣ በምን አይነት ሁኔታ ምላሽ ያገኛል የሚለው ቢቀመጥ" ሲሉ ዶ/ር ዐቢይን ጠይቀዋል።

አንድ ሌላ ተሳታፊ (ሴት) የክልልነት ጥያቄው የተጠየቀው "ማንነታችንን፣ ባህላችንን ለማሳደግ ታሳቢ በማድረግ ነው፤ ይሄን ብልፅግና ይመልስልናል ባህላችን፣ ቋንቋችን ያደገበት ሁኔታ የለም ፤ ቋንቋችንን፣ ባህላችንን ለማሳደግ የቱሪዝም ስራዎችን ወደ አካባቢያችን ለመሳብ እንዲሁም የልማት የጠቃሚ እንድንሆን በተለይም የውሃ፣ የመብራት ፣ መንገድ ችግሮችን ክልል ብንሆን መመለስ ይቻል ይሆናል በሚል ታሳቢ በማድረግ ነው የተጠየቀው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ምን ምላሽ ሰጡ ?

የክልልነት ጥያቄው በህግ አግባብ ብቻ ምላሽ ያገኛል ብለዋል። ጥያቄው ከተነሳ ጊዜ አንስቶ ምላሽ ለመስጠት በተሰራበት የህግ አግባብ ዛሬና ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቢስተናገድ የተሻለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ክልል የሚባለው ቢመለስ በ6 ወር ደመወዝ ባትከፍሉ ጭቅጭቅ ይቀራል ? አይቀርም፤ ክልል ያልነው እኮ ለልማት ብለን ነው እንጂ 10 ሰው ኮብራ እንዲይዝ አይደለም ትላላችሁ አይቀርም። አሁን መክረን ዘክረን የነገውንም ታሳቢ አድርገን መወሰን ይጠቅማል "

በሌላ በኩል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከልማት ጥያቄዎች ጋር በተየያያዘ በተለይም የውሃ፣ መንገድ፣ ሆስፒታል፣ ት/ቤት ጥያቄ ቀርቦላቸው መልሰዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ባለፉት ዓመታት መንግስት በዞኑ ያለውን ችግር ለመፍታት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው አሁንም ያሉ ችግሮችን በእርጋታና ንግግር ይመለሳል ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ "ውሃ እየጠየቅን የቧንቧ መስመር የምንሰብር ከሆነ፣ መንገድ እየጠየቅን ድልድይ የምናፈርስ ከሆነ ወደምንፈልገው ነገር አያደርስም፤ ወደምንፈልገው የሚያደርሰን በተረጋጋ መንገድ ተወያይተን፣ ተመካክረን፣ ጊዜ ወስደን ምላሽ መስጠት ስንችል ነው" ብለዋል።

ፌዴራሉ መንግስት ከክልል ጋር በመመካከር አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ይፈልጋል ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " በምንችለው ልክ አጣዳፊ የሆኑ እንደ #ውሃ ያለውን ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ያለፉትንን ዓመታት ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደነበረች ሊዘነጋ አይገባም ያሉት ዶ/ር ዐቢይ በሁሉም ቦታ የልማት ጥያቄዎች አሉ እንደ ሀገር ያለንን አቅም በውጤታማነት ጊዜን በመጠበቅ ከመጠቀም ያለፈ አማራጭ የለም ብለዋል።

ከልማት ስራ ጋር በተያያዘ መንገድን ያነሱት ዶ/ር ዐቢይ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የተጀመሩ የመንገድ ስራዎችን ለማስጨረስ የሚያስፈልገው ገንዘብ 1 ትሪሊዮን መድረሱን ገልፀዋል።

"የኢትዮጵያ መንግስት የአንድ አመት በጀት እዛ አልደረሰም" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ሙሉ በጀት መንገድ ላይ ቢውል እንኳን አዲስ ሊሰራ ቀርቶ የተጀመረውን አይጨርስም ስለዚህ ጊዜ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ "ጦርነት ውስጥ ነበርን፣ የዓለም መንግስታት ባይናገሩትም በብዙ መንገድ መደገፍ በሚገባቸው ልክ ሳይደግፉን የያዙን ጊዜ ነበር፣ ድርቅ ያጋጠመን ጊዜ ነበር፣ ብዙ ወጀቦች ያለበት ጊዜ ነው እንደዛም ሆኖ በየቦታው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተስፋ የሚሰጡ እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጡ አይደሉም" ብለዋል።

አክለው "ትንሽ ጊዜ መረጋጋት ከቻልን ነገሮች ወደ ሰላም እየሄዱ ስለሆነ በውስጥ ያለንን አቅም ከውጭም የምናገኛቸውን ድጋፎች ጨምረን በርካታ የልማት ስራዎችን ለመስራት እንሞክራለን" ሲሉ ተናግረዋል። /fbc/

@tikvahethiopia