TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ ዓርብ መስከረም 21 ቀን 2014  ከጧቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ በመስቀል አደባባይ እና ዙሪያው በሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት፦ • ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል…
#Update

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !

የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲከበር መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኗል፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚውስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
- ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ በፓርላማ መብራት
- በቸርችር ጎዳና ፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
- ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
- ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሳር ቤት አደባባይ
- ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ
- ከቦሌ ፣ በአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ኤድናሞል አደባባይ
- ከአዋሬ ወደ ካሳንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
- ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ አካባቢ
#ከዛሬ_ከቀኑ_10_ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜዉ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው።

@tikvahethiopia