TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኒፕሲ ሐስል ተገደለ‼️

ትውልደ ኤርትራዊው የሎስ አንጀለሱ ታዋቂ ራፐር፣ #ኤርምያስ_አስገዶም (ኒፕሲ ሐስል) በተከፈተበት ተኩስ ሎስ አንደለስ ውስጥ መገደሉን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

የ33 ዓመቱ ራፐር በርካታ ቦታዎች ላይ በጥይት መመታቱን እና ሆስፒታል እንደደረሰ ሕይወቱ ማለፉን ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘግቧል። ሌሎች ሁለት ሰዎችም በተተኮሰባቸው ጥይት #ቆስለዋል

ከኤርትራዊ አባት እና ጥቁር አሜሪካዊ እናት የተወለደው ኤርሚያስ አስገዶም በዚህ ዓመት ለሽያጭ ያበቃው አልበሙ በግራሚ የምርጥ ራፕ አልበሞች ምርጫ ላይ እጩ ለመሆን በቅቶ ነበር።

ሞቱ ካስደነገጣቸው ታዋቂ ሰዎች መካከል አንዷ ሪሃና ስትሆን "በዚህ ዜና መንፈሴ ታውኳል" ስትል የቲውተር ገጿ ላይ አስፍራለች።

ኤርሚያስ አስገዶም ተወልዶ ያደገው በደቡባዊ ሎስ አንጀለስ ሲሆን በተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችና በኪነጥበብ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል።

"ያደኩት በውንብድና ቡድኖች ውስጥ ነው" ሲል ለሎስ አንጀለስ ታይምስ በአንድ ወቅት ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ ነበር "... ሞት፣ ግድያ የየእለት ትዕይንቶቻችን ነበሩ። በጦርነት ቀጠና ውስጥ እንደመኖር ነው፤ ከዚህ መንደር ሰዎች ሲሞቱ ከቁብ አይቆጠርም ነበር።"

ኤርሚያስ ከመገደሉ በፊት በነበረ አንድ እሁድ "አምርሮ የሚጠላህ ሲኖር መባረክ ነው" በማለት በቲውተር ገፁ ላይ አስፍሯል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia