TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከእስር ያመለጠው ግለሰብ ከ28 ዓመታት በኃላ ተላልፎ ተሰጠ።

#ፓናማ ከእስር ካመለጠ 28 ዓመታት ያለፈውን #የእስራኤል እስረኛ አሳልፋ ሰጥታለች።

ፓናማ የእስራኤል እስረኛ የሆነውን ዮሲ ቤን-ኤሪን አሳልፋ መስጠቷን KAN ሪፖርት አድርጓል።

ቤን-ኤሪ የተባለው ግለሰብ 5 ኪሎግራም የሚጠጋ #ሄሮይን ከኔዘርላንድ ወደ እስራኤል በማስገባቱ ጥፋተኛ ተብሎ 12 ዓመት እንዲታሰር ተፈርዶበት ነበር።

ይህ ግለሰብ ከ28 ዓመት በፊት ነበር ከእስር ያመለጠው ፤ እንሆ ከ28 ዓመት በኃላ ፓናማ እስረኛውን አሳልፋ ለእስራኤል ሰጥታለች።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጉዳዩን የሰሙ ሰዎች ማንም ግለሰብ ጥፋተኛ ከሆነ የፈጀውን ጊዜ ይፈጃል እንጂ ከህግ እንደማያመልጥ ማሳያነው ሲሉ ገልፀውታል።

@tikvahethiopia