TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፦

ለሁሉም ነገር መሰራት ያለበት ከአዕምሯችን ነው። መልካም እና ገንቢ ሀሳብ ካልተዘራብን አፍራሽና ጠባብ አስተሳሰብ ይዘን የትም መራመድ አንችልም። የያዝነው ክፉ ሀሳብ ከኛ አልፎ ለሌሎችም እንቅፋት ነውና ነቅለን ጥለን በፍቅር፥በተስፋ እንዲሁም በእምነት ለዚህች ሀገር የግላችንን አበርክቶት እናኑር። ከራስ ቅላችን በላይ እናስብ። ተስፋዬ ፈለቀ @UoG GONDAR"
.
.
ከእኔነት እሳቤ መላቀቅ! አያቶቻችን ለሠሩት ስህተት(ምናልባት ከሰሩ) ይሄን ትውልድ እዳ ከፋይ አለማድረግ። እኛ ብሎ ማሰብ መጀመር ያስፈልገናል። ከሁሉ በፊት ሰው መሆናችንን ማመን። ሕገ መንግስቱን ማሻሻል። ፓርቲዎች ክርክራቸውን ከሕገመንግሥቱ ይልቅ ፖሊሲዎች ላይ ቢያደርጉ መልካም ነው።
.
.
የተሰራን ነገር ማፍረስ እንደመገንባት አይከብድም..ጦርነት ቀላል የሰላም መንገድ ረጅም ነው፡፡... ሁላችንም እንደ መንጋ ሳይሆን እንደ ግለሰብ ቆም ብለን ነገአችንን ማሰብ ካልቻልን ዘመናችንን በሙሉ ከድህነታችን ጋር ተጣብቀን ስንኗፏቀቅ መጃጀታችን ነው..ስለ ጭለማ ማውራት ብርሃን አያመጣም የልዩነት ሃሳቦችን ትተን አንድ የሚያረጉን ነገሮች ላይ ትኩረት ብናረግ ጥሩ ቀን ይመጣል ብዬ አስባለሁ ገና ብዙ የቤት ስራ ያለብን ህዝቦች ነን፡፡ፈጣሪ ሃገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን! ዳዊት ነኝ ከሰላሌ ፍቼ
.
.
አሁን በሀገራችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለቀጣዩ ትውልድም የሚተርፍ መዘዝ ያለው በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው። ብዙ ግዜ እንደተባለው ይህች ሀገር ከቀጣዩ ትውልድ የተዋስናት እንጂ እኛ ብቻ ኖረን ምናልፍባት አይደለችም። ታድያ ዛሬ ፍቅር እና መቻቻልን ያላስተማርናቸው ልጆቻችን እና በእድሜ ታናሾቻችን ነገ ከየት አምጥተው ይኖሩታል? ከሁሉ በላይ ሰውነትን እናስቀድም። ጩኸታችን እና ስብከታችን ሁሉ ስለ ፍቅር ይሁን። ለምን? ምክኒያቱም የነገ ሀገር ተረካቢዎች ከኛ ይማራሉ። መጥፎም ሆነ መልካም ከታላላቆቻቸው ይማራሉ። ጥላቻን አውርሰን ሰላም የሌለው ህይወት እንዲኖሩ አንፍረድባቸው! ልዩ ከሻሽመኔ
.
.
እኔ በበኩሌ ሁሉም ሰው የየራሱን ስራ ቢሰራና ሀላፊነቱን ቢወጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አስባለው። ምክንያቱም ምንም ነገር ከግለሰብ ነው ሚጀምረው። ሁላችንም እሱ ምን አደረገ፤ እነሱ ምን አደረጉ ሳንል እኔ ምን አደረኩኝ ምን ማድረግ አለብኝ ብለን ብናስብና ለስራ ብንነሳ ከኛ ለውጥ ይጀምራል። ስለዚህ ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንወጣ ለስራም እንነሳ። ሔኖክ ነኝ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
.
.
እንደ ሚመስለኝ የአይማኖት አባቶች ትልቅ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል እራሳቸውን ከፖለቲካ አንጃ አውጥተው ስለ ሰላም መስበክ አለባቸው የትኛውም እምነት ግደሉ በድሉ ዝረፉ አይልም ።
የተረሳ ሆኗል ስለሰላም መስበክ ስለ አንድነት ማውራት ችላ ተብሏል ። ወጣቱ የበለጠ ሊሰማ የሚችለው የእምነት አባቶችን ነውና በዚላይ ቢሰራ ባይ ነኝ። ሳብር
.
.
ለዚህ ተጠያቂ ሁላችንም ሁነን ሳለን ለችግሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ለችግሩ ሌላ ባለቤት ፈልገን እጃችን ለመቀሰሰር መጣራችን ይበልጥ አባብሶታል። ሰውን አርክሰን ለሌሎች ነገር የተሻለ ዋጋ ሰጥተናል። ሁላችንም ጥፋቶቻችን እንመን ከዛ ይቅር እንባባል በመቀጠል ተባብረን እንስራ!
.
.
ወንድሞቼ ያነሱት ሀሳብ እንዳለ ሆኖ
በየአካባቢው የምኖር ሰዎች ችግር ወይም ግጭት ሳይባባስ ቶሎ ብለው ወዴ መፍትሄ መሄድ አለበት ላሳስብ እወዳለሁ። ምሳሌ ብንወስድ
በድሮ ጊዜ ነው አንድ ፎቅ ባለ አራት ደረጃ ከላይ በአራተኛው እሳት ይነሳና ይቃጠላል ሥስተኛ እኔ ምን አገባኝ ይላል ከዛን ወደ ሥስተኛው መጣ ይቃጠላል ሁለተኛ ምን አገባኝ ይላል እሱ ጋ እንደዚህው ተቃጣለ አንደኛ ላይ እኔ ምን አገባኝ እያለ ላለው እሱ ጋ መጣ #ምሳሌው እኔ ምን አገባኝ የምንለው ነገር ነገ የከፋ ነገር ያመጣብናል ስለዚህ #ትንሽ #ትልቅ #ተማሪ #ነጋዴ #ሹፈሩ ወዘተ በሀገራችን መስራት አለብን
አመሰግናለሁ :#ፀግሽ
.
.
የመጀመሪያው ጥፋተኛ እኔ ነኝ። ለምን ተጠራጣሪና ስግብግብ ስለሆንኩ። ለምን የምኖረውና የማስበው በተከለልኩበት የማንነት አጥር ውስጥ ስላለው። እስኪ ትጋትን ሲሆን እኔ ድክመትን ሲሆን እነ ሱ ከሚለው ቆልማማ አመለካከት እንላቀቅና" እኛ" በሚለው ተያይዘን እንጒዝ። የሸበበን ብሄር ያነቀን ጎስ ይስቀመጠንን ጎጠኝነት ትተን ከአጥሩ ባሻገር ያለው ሰፊውን የፍቅር ሜዳን እንመልከት። ክፉዎች ሊለያዩን ያጠሩብንን ግንብ ድልድይ እንገንባና ዳግም እንተያይ...የእውነት መሰረቱ መፋቀር ብቻ ነው..ሰውን ለማገልገል እንጂ ለምን ክብርን እሻለው...ትግላችንና ግዴታችን ፍቅር ይኑርበት... ሁሉን ማስተካከል የሚቻለው እርስ በእርስ በመዋደድ ብቻ ነው። ጌታነህ ከመቂ!
.
.
እሺ ወንድሜ፡ ዋናው የአሁኑ ለደረስንበት ውጥቅጥ መጀመሪያ የነበረው ከሁንም ያለው ራስ ወዳድነታችን ነው ፡ የምር እኛ በቀደድነው ቀዳዳ ሌቡች ይገባሉ ሀገርን ለማቃወስ እኛ አሁን ወላሂ መንቃት አለብን የድርጅት ደጋፊ ብቻ መሆን መዘዙ ይህ ነው አሁን ያለንበት ሁኔታ እውነትን እፈልግ ሀሳብ ያሸንፍ ለሀሳብ እድል እንስጠው ፡ አገሬ ኢትዮጲያ ለዘላለም በልጆችሽ ኮርተሽ ትኖራለሽ ፡ በርግጠኝነት እናሳካዋለን ፡ እኔ ባለሁበት ለዚህም ቁርጠኛ መሆኔን እገልፃለሁ፡ ሰላም ፍቅር ለኢትዮጵያ ህዝብ ቸው ፡ ዩኑስ ነኝ ከቡታጅራ
.
.
የሚጋፋ ሃሳብ ወይም የሌላዉን ወገን ህልዉና የሚነካ ንግግሮች እና ዘለፋዎች ከስነ-ስርዓት አልበኝነት የሚመጣ ሲሆን እያንዳንዳችን ሌላዉ ላይ ጣታችንን መቀሰር ትተን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ መክረን መመለስ ባንችል እንኳን ክፉ ከመናገር በመቆጠብ ታላቁን ሰላም እንጋራ፡፡ ኤልያስ፡ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር
.
.
እኔ እንደማስበዉ ከሆነ ለዚሁሉ ችግር ዋንኛው ተጠያቂ ት/ቤቶቻችን ናቸዉ፡ጥላቻን እንድናውቅ እያደረጉን ነው.ከዚ ቀደም የደርግን ስርአት እየተቸ ነበር ያስተማረን ደርግ ምንም ጥሩ ነገር እንዳልሰራ፡አሁንም ቢሆን ያለፈው ስርአት አንተች በጣም ብዙ ጥሩ ነገር አንደሰራም እንወቅ ባይ ነኝ፡ስለዚህ የትምህርት ስርአቱ ላይ መሠራት አለበት።
.
.
ህብረተሰብ የሚለውን ቃል ብንመረምር ህብረት እና ሰብ የሚሉት ቃላት ዉህድ ነው። "ሰብ" የሚለውም መጨረሻው እና ማሰሪያው ነው። ህብረታችን ቁምነገሩ ሰውነታችን ላይ ነው። ስለሆነም የህብረታችን ማሰሪያ የሆነውን "ሰውነት" ወደ ዉስጥ መመልከት ስንችል የምናስተውለው የአፈጣጠራችንን ረቂቅ ጥበብ፣ ሃሳብ ነው። ዘር፣ ሃይማኖት፣ ብሄር፣ እዚያ ዉስጥ አንዳቸውም ቦታ የላቸውም። ይህንን ስንገነዘብ የሰውን ልጅ ቅድሚያ በሰውነቱ ሲቀጥል በሃሳቡ እናየው ዘንድ እንችላለን።
.
.
ሰላም ሰላም የሀገሬ ህዝቦች ዘር ሳልቆጥር ቀለም ሳለይ ውውድድድ ነውው የማረጋቹ የማይረሳ የአድዋን ድል አስገኝታቹልናልና እና እኔ ምለው ሰላም ለማምጣት እርስ በእርስ ህዝብ ለህዝብ መደማመጥ እና ዘረኝነት አስወግዶ ሁሉንም አንድ የሚያረግ አስተሳሰብ በህዝብ ዘንድ መምጣት አለበት ይህ እንዲመጣ ደሞ የmedia ሺፋን ትልቁን ቦታ ይወስዳል እደዚሁም social midia ዎችም የራሳቸውን አስተዋፅሆ ያደርጋሉ በሰላም ላይ እንደማመጥ እንከባበር ሁሌም ሰላም ከኛ ጋር ናት ድል ሰላም ወዳድ ለሆነው የሀገሬ ህዝብ አቤል ነኝ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው ? - ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመውረር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብላለች። - ዛሬ ማለዳ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላጥ ጥቃት መክፈቷን አሳውቀዋል። የሚሳአኤል ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ሩሲያ ዛሬ ማለዳ ላይ የከፈተችው ጥቃት ኢላማ ያደረጉት የዩክሬን መሰረተ ልማቶችና የድንበር ጥበቃዎች ላይ ነው ብለዋል።…
የዩክሬን ቀውስ አስከፊውን የዓለም ጦርነት ይዞ እየመጣ ይሆን ?

🇷🇺 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 🗣

" ዶንባስ ክልል ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተጀምሯል። የወታደራዊ ዘመቻው ዋነኛ ዓላማ ላለፉት 8 ዓመታት በኬይቭ በሚገኘው መንግስት የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው የነበሩ ሰዎችን ነፃ ማውጣት ነው። "

🇺🇦 የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ 🗣

" ሩሲያ በማንኛውም ቀን አውሮፓ ውስጥ #ትልቅ_ጦርነት ልትጀምር ትችላለች። ሩሲያውያን እርምጃውን ሊቃወሙት ይገባል። ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ ሞከርኩ፤ ውጤቱ ዝምታ ሆነ። ሩሲያ ወደ 200 ሺ የሚጠጉ ወታደሮችና በሺዎች የሚቆጠሩ የውጊያ መኪናዎች በዩክሬን ድንበር አሏት። ሩሲያውያን በዩክሬን ጉዳይ እየተዋሹ ነው ስለሆነም ጥቃቱን ሊቃወሙ ይገባል "

🇺🇳 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 🗣

" ፕሬዝዳንት ፑቲን በ #ሰብኣዊነት_ስም ጦርህን ወደ ሩሲያ መልስ። ይህንን ካላደረክ ውጤቱ በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት ሊያስከትል ይችላል "

🇺🇸 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን 🗣

" ሩሲያ #በዩክሬን ላይ በምትፈጽመውን ወረራ ለሚደርሰው ጥፋትና ውድመት ዓለም ሩሲያን ተጠያቂ ሊያድርግ ይገባል። የዓለም ህዝብ በሩሲያ ጥቃት ጉዳት የሚደርስባቸው ዩከሬናውያንን በጸሎት ያስባል። "

🇬🇧 የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን 🗣

" ሩሲያ ደም አፋሳሹን መንገድ መርጣለች፤ ቀጣይ እርምጃ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መምህራን ምን አሉ ? • " የመምህራን ደመወዝ ይቆረጣል የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ አሳማኝ አይደለም " • " የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች አይልኩም " • " አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው ይጠብቃሉ፤ ግማሽ ደመወዝ ብቻ የሚከፈልበት ጊዜም አለ " የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው 36ኛው ጉባዔ ላይ፣ በክልሎች የበርካታ…
#የኢትዮጵያ_መምህራን_ማህበር #ቲክቫህኢትዮጵያ

የመማሪያ መፅሀፍት ጉዳይ

" ቅሬታችንን መንግሥት ይወቅልን " ያሉ #ተማሪዎች ፣ የመማሪያ መፅሀፍት ሶፍት ኮፒ እንኳን ማግኘት ቢቻል ማንበቢያ ስልክ ያስፈልጋል ፣ ስማርት ስልክ ደግሞ የቤተሰቦቻችን ገቢ  ዝቅተኛ በመሆኑ ሊገዛልን አይችልም ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አክለውም፣ በዚህ ሁኔታ እንዴት መማርና ውጤታማ መሆን እንችላለን ? ነው ወይስ ትምህርት መማር ያለባቸው የባለሃብት ልጆች ብቻ ናቸው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

36ኛውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን በጅግጅጋ በነበረ ውይይት የተማሪዎችን የመጽሐፍ እና የሶፍት ኮፒ አለምግኘት ጨምሮ ሌሎች መምህራን የሚያነሷቸውን ቅሬታዎች በተመለከ ምን የመፍትሄ ሀሳብ እንደተቀመጠ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ጥያቄ አቅርቧል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ሳውላ ጎፋ አካባቢ) ፕሪንተርም፣ ፎቶ ኮፒም የለውም " ብለዋል።

" አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የማባዣ ቁሳቁስ እንኳን የሌላቸው አሉና ሶፍት ኮፒ ብቻ ልኮ ተማሪዎች መፅሐፍ አግኝተዋል ማለት አይቻልም " ያሉት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት፣ " ሶፍት ኮፒ ደግሞ በሞባይል ነው የሚታየው፣ ሁሉም ተማሪ ደግሞ ለዛ የሚመጥን ስማርት ስልክ ላይኖረው ይችላል፣ አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል " ነው ያሉት።

" ተማሪዎች ሀርድ በእጃቸው ይዘው የሚያነቡት ሀርድ ኮፒ ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ዮሐንስ (ዶ/ር)፣ ይህንን በተመለከተም በጅግጅጋ በነበረው የማኅበሩ ምክር ቤት ክልሎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መፅሐፍ እጥረት እንዳለ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፅሐፍ እንዳልደረሰ ተነግሯል ብለዋል።

የተነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) " ወደ 40 ኮንቴነር ጂቡቲ ደርሷል፣ እንደውም ወደ መሀል አገርም እየተጓጓዘ ነው፣ በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች ይደርሳል " ማለታቸውን ይሐንስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የመምህራን ዝውውር ጉዳይ

ከዝውውር ጋር በተያያዘ መምህራን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ የሚደመጥ ሲሆን፣ ችግሩን ለመቅረፍ ምን ውይይት እንደተደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የማኅበሩ ፕሬዚዳንት፣  መምህራን የሚዘዋውሩበት የዝውውር ስርዓት እንዳለ ገልጸው ተከታዩን አክለዋል።

" ዝውውር ለመምህራን እንደ #ትልቅ_የመብት_ጉዳይ የሚታይ ነው። " የተለያዩ የአፈፃፀም ጉድለቶች እንዳሉ ምክር ቤቱ በጅግጅጋ በነበረው ስብሰባ ገምግሟል። በየደረጃው ተስተካክሎ በመመሪያው መሠረት እንዲፈጸም ሰፊ ውይይት አድርገንበታል። "

ተፈናቃዮችን ያስጠለሉ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ

" የተፈናቀሉ ዜጎች መጠለያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ አይተናል። በዛ አካባቢ በተለይ ትምህርት ለመስጠት አስቸጋሪ ይሆናል " ሲሉ ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) አስረድተዋል።

ኢሰመኮ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ባድረገው ሪፓርት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቃዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በሚያገረሽበት አማራ ክልል ውስጥ ትምህርት ቤቶች የተፈናቃይ መጠለያ ካምፖች እንደሆኑ መረዳቱን ማስገንዘቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በበኩሉ የተፈናቃይ መጠለያ በሆኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መምህራን ማስተማር እንዳልቻሉ ፣ የትምህርት ተቋማትም ውድመት እንደሚደርስባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልና መቆረጥ ጉዳይ

መምህራን የሰሩበት ደመወዛቸው #ስለማይከፈላቸው እና የሚከፈላቸውም ስለሚቆረጥባቸው በተለይም ደቡብ ክልል ላይ የሥራ ማቆም አድማ እስከማድረግ የደረሱበትን ሁኔታ በተመለከተ ምን እንደታሰበም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመምህራን ማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጥያቄ አቅርቧል።

ፕሬዝዳንቱ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " ቀደም ብሎ እዚያ አካባቢ ባጋጠመው ሁኔታ እኛም ለክልሉ መንግሥት ደብዳቤ ፅፈን ነበር፣ በዚያ መነሻ በወቅቱ ተከፍሎ ነበር። አሁን ኋላ ላይ ደግሞ ተመልሶ እንዳገረሸ ሰምተናል" ብለዋል።

" ምክንያቶቹ የተለያዩ ይሆናሉ። መምህራን የሰሩበትን በጊዜው ማግኘት አለባቸው " ያሉ ሲሆን " ደመወዙ የመምህራኑ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻቸውም፣ የልጆቻቸውም ጭምር ስለሆነ በየደረጃው ያለው መዋቅር ይህን ተከትሎ መፈጸም እንዳለበት ሁሌም እናሳስባለን " ሲሉ ገልጸዋል።

የደመወዝ አለመከፈልን በተመለከተ ለማኅበሩ ምን ያህል መምህራን ቅሬታ እንዳቀረቡ፣ ለስንቶቹ መፍትሄ እንደተሰጠ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ በአብዛኛው ቅሬታ ያለው በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል በተወሰነ መልኩ እንዲሁም በአፋርና በሌሎች አካባቢዎች እንድሆነ፣ ቅሬታው ከተለያዩ ወረዳዎች ስለሚመጣ ቁጥሩን ለመግለጽ እንደሚያስቸግር አስረድተዋል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት ፣ የ36ኛው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ምክር ቤት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን በጅግጅጋ በነበረው ፕሮግራም ውይይት ተደርጎባቸው የመፍትሄ ሀሳብ የተቀመጠላቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች፡-
- የመምህራን ዝውውር
- የመምህራን ጥቅማጥቅም
- የመምህራን የትምህርት ዕድል
- የመኖሪያ ቤት አቅርቦት
- መልካም አስተዳደር
- የትምህርት ጥራት
- የተማሪዎችን የውጤት ቀውስ
-  የጸጥታ ችግር በትምህርት ላይ ያስከተለው ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በተመለከተ ነው ብለዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia