TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የመሪጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው  ” - የዓይን እማኝ በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። አንድ ሟቾቹ መቀበራቸውን የተመለከቱ የዓይን እማኝ በሰጡት ቃል፣…
" 11 ንፁሃን ነው የተገደሉት " - የዶዶላ ከተማ አስተዳደር

በዶዶላ ባለፈው ሰኞ ዕለት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በተፈፀመ ጥቃት 11 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል አረጋግጧል።

የከተማው አስተዳደር ለሬድው ጣቢያው " በዕለቱ በድንገት በተፈፀመ ጥቃት 11 ሰዎች ሞተዋል። በጥይት ተመተው የተጎዱም አሉ። ከጥቃቱ ጀርባ በገደብ አሳሳ ፣ አዳባ፣ በክልል ደረጃም ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ቡድን አለ የሚል መላምት አለ ግን ምርመራ እየተካሄደ ነው " ብሏል።

ይህ ሁሉ ሰው #ሲገደል የፀጥታ ኃይሉ ለምን በስፍራው አልደረሰም ? ለሚለው ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ ፤ " ጥቃቱ የተፈፀመው በደነባ ክ/ከተማ ደብረ ቅዱሳን ጻድቁ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ነው። ይህ ሆን ብሎ የሃይማኖት አባትን እና ልጆቻቸውን የገደለው እርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ነው ብለን እንገምታለን። በጣም ታስቦበት የተፈፀመ ግድያ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ንፁሃኑ ግድያው የተፈፀመባቸው በቤታቸው እያሉ #በጥይት ተተኩሶባቸው እንደሆነና መንግሥት ግድያውን እንደሚያወግዝ የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

ለመሆኑ የጥቃቱ ፈፃሚዎች ተይዘዋል ? ለሚለው ጥያቄ ፥ የዶዶላ ከተማ አስተዳደር " ክትትል እየተደረገ ነው " የሚል ምላሽ ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥቷል።

ይህ የአስተዳደሩ ምላሽም አንድም የተያዘ ሰው እንደሌለ የሚጠቁም ነው።

በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ 2 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪና የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ነዋሪው ፤ አንድ መሪጌታ ከእነባለቤቱ እና ከሁለቱ ልጆቹ ጋ፣ አንድ ዲያቆን ከእነባለቤቱና እህቱ ጋር መገደላቸውን ፤ የመርጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ መቅረቱን ገልጸው ነበር።

@tikvahethiopia