TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስጠንቀቂያ‼️

#ሼር #Share

በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ለምትገኙ በሙሉ -- የተከሰተውን #ግጭት ለማርገብ እና ሰላም ለማስከበር የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ይሰራል።

አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ #የተከለከሉ ተግባራት፦

• ከጎንደር - መተማ መስመር 5 ኪ.ሜ. ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ #በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

• "ሰላም ለማስከበር" በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፍቃድ ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

#ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል #እርምጃ ይወሰድበታል‼️

የሰላም ጥሪ፦

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንድትሰሩ #መከላከያ_ሰራዊት ጥሪ አቅርቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መከላከያ_ሰራዊት በቤንች ማጂ ዞን ተዘግተው የቆዩ መንገዶችን እንዲከፈቱ አድርጓል። #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #መተከል አካባቢ ለሚገኙ የሀገራችን ዜጎች‼️ #ኢትዮጵያ #ETHIOPIA #ቤንሻንጉል

#መከላከያ_ሰራዊት
#ፌደራል_ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መከላከያ_ሰራዊት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገ-ወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታወቀ፡፡ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደዋል፡፡ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ አተኩሮ የተካሄደውን ውይይት ያስጀመሩት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሀመድ ናቸው፡፡ ከፍተኛ አመራሮቹ በቅርቡ በተቋሙና በአማራ ክልል አመራሮች ላይ የደረሰው አደጋ ታላቅ ቁጭት መፍጠሩን በመግለጽ በቀጣይ ድርጊቱ እንዳይደገም እንደሚሰሩ በውይይቱ ማጠቃለያ ባወጡት ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱና ለህዝቦች ሰላም መስዕዋትነት እየከፈለ የመጣ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው በቀጣይም የተለያዮ #ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገ-ወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፡ ሰራዊቱ ከምንጊዜም በላይ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት በሚያስችለው ቁመና ላይ እንደሚገኝና የተሰውት ጓዶች ህልፈት አባላቱን ለበለጠ #ጀግንነትና መስዋዕትነት የሚያነሳሳ እንጂ #የሚያዳክም እንዳልሆነ ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2013 ምርጫ ሂደት ሊያስተጓጉል ይችላል ?

የምርጫ ቁሳቁስ ማጓጓዣ ችግር አፋጣኝ እልባት ካላገኘ አገር አቀፉን የምርጫ ሂደት ሊያስተጓጉል ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

የኢትዮጰያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ያሳወቀው በመራጮች ምዝገባ መረጃ፣ በምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር በተወያየበት ወቅት ነው።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሰፊ አገርና ህዝብ ነገር ግን የመንገድ መሰረት ልማት ውስንነት ያለበት አገር ላይ ምርጫን በአግባቡ ለማካሄድ መንግስት ከፍተኛ እገዛ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ሁሉንም የአገሪቱ አካባቢ ሊሸፍን የሚችል የትራንስፖርት አቅም ያለው #መከላከያ_ሰራዊት መሆኑን የገለጹት ሰብሳቢዋ በትግራይ በነበረው ሁኔታ በተፈጠረው ጫና እገዛው መስተጓጎሉን ተናግረዋል።

ያለው የማጓጓዣ ችግር አፋጣኝ እልባት ካልተሰጠው የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስተጓጉል ይችላል በማለት ተናግረዋል ሰብሳቢዋ።

ምርጫ ቦርድ በመላ አገሪቷ 663 የምርጫ ክልሎችን ከፍቶ የምርጫ ቁሳቁሶችን እያጓጓዘ ሲሆን በቀጣይ ለ50 ሺህ ምርጫ ጣቢያዎች እንደሚያሰራጭ አስታውቋል።

ማጓጓዣው በየአካባቢው እንዳለው መሰረተ ልማት በየብስ ፣ በጀልባ እንዲሁም በበቅሎና ፈረስ ጭምር ሊሆን እንደሚችል ነው ያመለከቱት።

ለዚህም ደግሞ በየደረጃው ያሉ የክልል አመራሮች የመጓጓዣ ችግሩን ለመፍታት ከቦርዱ ጋር መተባበር እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጄነራሉ ምን አሉ ?

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ለመከላከያ ሰራዊት ቴሌቪዥን ፕሮግራም ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል።

ይኸው ቃለመጠይቃቸው ዛሬ ለህዝብ ተሰራጭቷል።

ጄነራሉ ምን አሉ ? በተለይም ስለ ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ጉዳይ ምን ሃሳቦችን አንስተው ተናገሩ ?

ጄነራል አበባው ታደሰ ፦

- መላ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን የምንፈልገው በሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል እንዲገነባ ህገመንግስቱ የሚፈቅደው #መከላከያ_ሰራዊትና #ፌዴራል_ፖሊስን ነው።

- በየክልሉ ያለው ልዩ ኃይል በሳይዙ ልክ አለው ፤ በሌላ አነጋገር ሀገር በሚመስል ደረጃ 14 እና 15 ሬንጀር አለው ይሄ ፈፅሞ አይቻልም።

- አሁን ያለው የክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ስራ ዛሬ የተጀመረ / በሞራል የተገባበት ሳይሆን ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዜ ጥናት ተደርጎበት ነው።

- የክልል ልዩ ኃይሎች ፦ የክልልን ፀጥታን ይጠብቁ ነበር ፣ ከእኛ (ከመከላከያ) ጋር ሆነው ይሞቱ ነበር ህይወታቸውን አሳልፈዋል ፣ ቆስለዋል ደምተዋል። ይሄ ኃይል ይሄን የመሰለ ትልቅ ኳሊቲ ነበረው።

- ከህገመንግስት አንፃር ስናየው እነዚህ ኃይሎች ህጋዊ አይደሉም ህገመንግስቱ እውቅና አይሰጣቸውም። ለክልል ኃይል የሚሰጠው መደበኛ ፖሊስን ብቻ ነው። ህገመንግስቱ የታጠቀ ኃይል የሚያውቀው አንደኛ መከላከያ፣ ሁለተኛ ፌዴራል ፖሊስ፣ ሶስተኛ መደበኛ ፖሊስ ነው ከዚህ ውጭ ህገመንግስቱ አይልም።

- የኃይል አገነባቡ (የልዩ ኃይል መዋቅር) ብሔር ተኮር ነው ፤ ለኦሮሞ ህዝብ እሞታለሁ ብሎ ቃል ይገባል አማራውስ ? ጉዳዩ አይደለም ማለት ነው በግልፅ አማርኛ ፤ አማራው ደግሞ ይመጣና ለአማራ ህዝብ እሞታለሁ ይላል ኦሮሞውስ ? ጉዳዩ አይደለም ። ብሄር ተኮር ስለሆነ ሀገር አቀፍ የሆነውን አብሮነት የመኖር ፤ የህዝቦችን አንድነት ይሸረሽረዋል።

- የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ፕሮግራም ወደ መከላከያ ሰራዊት ማስገባት፣ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ማስገባት፣ ወደ መደበኛ ፖሊስ ማስገባት ነው። በማን በራሱ ምርጫ፣ በምን ? ክብሩን ሞራሉን ፣ ጥቅሙን በማይነካ ሁኔታ።

- አፈፃፀሙ በተመለከተ ሁሉንም እኩል እደራጀዋለን ፣ በጥንቃቄም ይሰራል።

- አንደኛውን ክልል ኃይል እንዲኖረው ሌላውን ክልል ኃይል እንዳይኖረው አናድረግም። ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ አይታሰብም።

- የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ለምሳሌ የትግራይ የትግራይ ክልል እንደማንኛውም ክልል መደበኛ ፖሊስ ብቻ ነው የሚኖረው ፣ የታጠቀ ልዩ ኃይል የሚባል በፍፁም አይኖረውም።

- በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢና ዩኒቶች ካልሆነ በስተቀር አማራ ልዩ ኃይል የሚባለው በአብዛኛው ተቀብሎታል ፤ ይሄ በኮሚኒኬሽን ያለ ችግር ነው ይሄን የኮሚኒኬሽን ችግር እየፈታን ነው ያለነው። አፈፃፀሙ ላይ የታየው ጉድለት ይሄ ነው እንዲህ አይነት ነገር ሊኖር እንደሚችል እንጠብቃለን አስበንም ነው የገባነው። ከዛ  ውጭ ባወጣነው ፕሮግራም መሰረት ይሄን ኃይል ወደምንለው ፕሮግራም እናስገባዋለን ሁሉንም እኩል አድርገን።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-07