#update ቡራዩ⬇️
ከቡራዩ ከተማ ከተፈናቀሉት መካከል 1 ሺህ 700 ያህሉ ወደ መኖሪያ ቀያቸው
#መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ እንደገለጸው በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ በአሁኑ ወቅት መረጋጋት በመፈጠረቱ ነው በአዲስ አበባ ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው የነበሩት #ተፈናቃዮች መመለስ የጀመሩት።
በመጪው ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ እለት በመሆኑ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ሌላ ስፍራ የማዘዋወር ስራ መጀመሩን ቢሮው አክሎ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅትም ተፈናቃዮች ተጠልለው ከሚገኙበት 9 ትምህርት ቤቶች ወደ ሌላ ቦታ የማሸጋሸግ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።
©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ያሉ ተማሪዎች ሁኔታ !
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምንም አይነት የደህነት ስጋት እንደሌለባቸው ተናረገዋል።
መጀመርያ አከባቢ የጊቢ ጠባቂዎች (አጋር)፣ ምግብ አብሳዮች እና ፅዳት ሰራተኞች ጊቢውን ለቀው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ ያለውን ምግብ እያበሰሉ ለተወሰኑ ቀናት ተጠቅመዋል፡፡
አሁን ላይ ከፅዳት ሰራተኞች ውጪ ሌሎች ሰራተኞች #መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ጊቢውን ለቀው ወደየ ቤተሰባቻቸው መመለስ ከማሰብ ውጪ የተረጋጋ ስሜት ውስጥ ናቸው፡፡
በቂ ውሃ ምግብ እና መብራት እንዲሁም የገንዘብ ሰጪ ተቋማትን አለግኘታቸው ትልቁ ችግር ነው፡፡ ይሄ የሁሉም ካምፓስ ተማሪዎች ችግር ነው፡፡
ከዛ ውጪ ተማሪዎች ሰላም ናቸው። የመመረቂያ ፅሁፋቸውን እያቀረቡ ነው፡፡
መቐለ ከተማ ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ከእለት ወደ እለት እየተመለሰ መምጣቱም ተማሪዎች ወጣ ገባ እያሉ ነው።
ታክሲዎች በብዛት ስራ ጀምረዋል፡፡
የመቐለ ከተማ ነዋሪ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ብዙ ነገር ጎለበት እንኳ ተማሪን በራራ ልቡ እያስተናገዳቸው መሆኑን ተማሪዎች ተናግረዋል።
በተለይ መቐለ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች ጓደኞቻቸውን ወደየቤታቸው እየወሰዱ ያለውን ነገር እንዲጋሩ በማድረግ አስቸጋሪውን ጊዜ በትብብር እያለፉት መሆኑን አሳውቀዋል።
መከላከያ ሰራዊት የተማሪውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር ለዕለት ቀለብ የሚሰጠውን ኮሾሮ ለተማሪ እያጋራ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርስቲው ተማሪዎቹን ባለፈው ረቡዕ አስመርቆ ሊሸኛቸው ነበር በተለያዩ ምክንያቶች ይሄ አልሆነም፡፡
አሁን ላይ ከህክምና ተማሪዎች ውጪ ያሉ ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት ተመርቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡
በመቐለ ሁሉም ነገር ሰላም ነው።
(በጋዜጠኛ ኃይለሚካኤል ዴቢሳ - ከመቐለ)
@tikvahethiopiaBOT