TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ! የኢትዮጵያ ወጣቶች ለሌላውም የህብረተሰብ ክፍል #ማን እና #ለምን እንደጠራው በማይታወቅ ሰልፍ ላይ ባለመገኘት እንዲሁም ባለመታደም እራሳችሁን እና የምትወዷትና የምትሳሱላትን ሀገራችሁን #ከጥፋት ጠብቁ።

#Security_Alert- U.S. Embassy Addis Ababa, Ethiopia (September 18, 2018)

Location: Addis Ababa

Event: On September 19, the U.S. Embassy will be closed for routine services in anticipation of protests planned throughout Addis Ababa. Embassy employees are instructed to stay at home. U.S. citizens in need of emergency assistance should contact the after-hours emergency number below.

Actions to Take:

▪️Remain at home/in a secure location.
▪️Inform family and friends of your location as communications may be disrupted during this period.
▪️Monitor local media for breaking events.
▪️Avoid large crowds and demonstrations
▪️Be aware of your surroundings.
▪️Keep a low profile.

Assistance:

U.S. Embassy Addis Ababa, Ethiopia

+251-111-306-000

+251-111-306-911 or 011-130-6000 (after-hours)

[email protected]

State Department – Consular Affairs

888-407-4747 or 202-501-4444

📌የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃውን ከየት እንዳመጣው አልገለፀም።

🙏ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ይህ መልዕክት ለምታውቋቸው በሙሉ እየደወላችሁ በማድረስ ሀላፊነታችሁን ተወጡ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Security_Alert

መንበረ ሠላም የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በአሁን ሰዓት ከባድ ተኩስ እንዳለ ገልፀዋል።

ታጣቂዎች ወደ #ድባጤ ሰብረው ሊገቡ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቂ የሆነ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንደሌለ አሳውቀዋል።

* ይህ አካባቢ እስካሁን ድረስ ከስጋት ቀጠና አልተላቀቀም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Security_Alert

በደቡብ ክልል 'ጋቶ ቀበሌ' የፀጥታ ችግር መኖሩን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ዛሬም ከባድ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ 'ጉማይዴ' አካባቢ ከሰሞኑ የፀጥታ ችግር መኖሩን አባላቶቻችን አሳውቀዋል።

* የቲክቫህ አባላት ፣ አርሶ አደሮች በአካባቢው ላይ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጠር ጠይቀዋል። የዜጎች ደህንነት ያሳስበኛል የሚል የመንግስት አካል መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Security_Alert

በደቡብ ክልል 'ጋቶ፣ ፉጩጫ' እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ዛሬም (ማክሰኞ) የፀጥታ ችግር መኖሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀዋል።

ዛሬም የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ገልፀዋል።

በተመሳሳይ 'ጉማይዴ' አካባቢ ያለው የፀጥታ ችግር አሁንም እንዳልተፈታ አባላቶቻች ገልፀዋል።

* በዚህ አካባቢ ያሉ የሀገራችን ዜጎች በሰላም እጦት እጅጉን እየተሰቃዩ ነው ፤ መንግስት እጅግ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia