TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል። ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል። የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?…
 #Update

"...ታጋችዋን ታዳጊ ለማስለቀቅ ከከተማ እስከ ክልል የተቀናጀ የክትትልና ምርመራ ስራ እየሰራን ነው። በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችም አሉ " - የዓድዋ ከተማ ፓሊስ

የዓድዋ ከተማ ፓሊስ በታጋቿ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማብራሪያ ሰጥቷል።

መጋቢት 10/2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ ልዩ ቦታ ዓዲ ማሕለኻ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ የተሰወረችው ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ከታገተች 24 ቀናት ተቆጥሯል።

የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ ተስፋይ  ኣማረ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም በስልክ በሰጡት መረጃ ፥ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባትን የተማሪ ማህሌት ተኽላይ አጋቾችን በቁጥጥር ስር ለመዋል ፓሊስ ጥረት እንያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

የታዳጊዋ መታገት በማስመልከት በተሰቦችዋ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ሪፓርት ካደረጉበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ፓሊስ ጉዳዩ ለደቂቃ ያህል ችላ እንዳላለው የገለፁት የፓሊስ ዋና አዛዡ ፥ " ' ፓሊስ ለእገታው ትኩረት አልሰጠውም ' ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆችና በሚድያዎች የሚሰራጨው መረጃ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ይህን ያህል ከባድ የውንብድና ወንጀል ተፈፅሞ ፓሊስ እንዴት ችላ ይለዋል ? " ሲሉ የጠየቁት ዋና አዛዡ ተስፋይ አማረ ፥ ከከተማው እስከ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በመቀናጀት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ለመያዝ ሌት ተቀን እየተሰራ ነው ብለዋል።

" ታዳጊዋን ያገቱ ሰዎች ከእገታው በፊት ለረጅም ጊዜ ሲከታተሉዋት የቆዩ መሆናቸው ከቤተሰቦችዋ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል " ያሉት ዋና አዛዡ ፥ " የተወሰኑት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል። ለሚድያ መግለጫ ስላልሰጠን ብቻ ስራችን እየሰራን እንዳልሆነ ተደርጎ መውሰድ አግባብነት የለውም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በታዳጊዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ በተደጋጋሚ መረጃ ያደረሰ ሲሆን ከቀናት በፊት ቤተሰቦቿ በሰጡት ቃል ፥ አጋቾች ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው በጠየቁበት ዕለት ድምጿን ከሰሙ በኃላ ዳግም እንዳላገኟት እነሱም እንዳልደወሉ ፣በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች እንኳን እንደማያውቁ ፤ በዚህም መላው ቤተሰብ በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረው ነበር።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሚመራው የህወሓት ቡድን ጋር ያላቸው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደሚሰራ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን ተናግሯል። በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች መስከረም 20/2017 ዓ.ም በመቐለ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል። ውይይቱ ለሁለት የተከፈለው ድርጅት ለማዳንና የትግራይ ህዝብ…
#TPLF

" ህጋዊ እና ትክክለኛ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  

" ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል ሰብሰባ የተቀመጠው በምክትል ሊቀመንበር  አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  ሰብሰባውን ቀጥሏል።

የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ ካድሬዎች " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል ርእስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ተወያይተዋል።   

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ህጋዊ እና ትክክለኛ የድርጅቱ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ በውይይት መድረኩ ገልጿል።

" ድርጅቱ አሁን ለደረሰበት የመከፋፈል አደጋ ዋና መንስኤው በድርጅቱ ስር የሰደደው ፀረ ዴሞክራሲ አካሄድና ተጠያቂነት አለመኖር ነው " ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

" የድርጅትና የመንግስት አሰራር መደባላለቅ ይቁም " በማለት አቋም የያዘው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን " በነበረው ይቀጥል " ከሚለው በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ቡድን እንደ አንድ የመለያያ ነጥብ ሆኖ በመድረኩ ውይይት እንደተካሄደበት ታውቋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የተመራው 14ኛው ጉባኤ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦለት ያልተቀበለው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው በዱን አሁን በተራው " ህጋዊና ትክክለኛ " በማለት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እያደረገለት በሚገኘው 14ኛው ጉባኤ ከዶ/ር ደብረፅዮን ጎን የወገኑት " ከያዙት የተሳሳተ መንገድ በመውጣት ጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ " ከወዲሁ ጥሪ አቅርቧል። 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መሪነት የተካሄደው ጉባኤ ቀደም ብሎ ጉባኤውም ሆነ ውሳኔዎቹ ቅቡልነት እንደሌለው ማሳወቁ መዘገባችን ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል። " ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት…
#TPLF

ከዛሬ ጀምሮ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ ሁሉም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በጉባኤ በተሳተፉ ሹማምንት መቀየሩን በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ወስኛለሁ " ብሏል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓት ከሰጣቸው የስራ ሃላፊነት ተነስተዋል እንዴትና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርኩ ነው " ብሏል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት።   

ከየትኛው የፌዴራል መንግሥት አካል ጋር እየተወያየ እንደሆነ በግልጽ ያለው ነገር የለም።

ስለ ጉዳዩ እስካሁን በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚመራው ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም። 

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ፥ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች ፣ ቢሮዎች ፣ ኤጀንሲዎች ፣  ኮሚሽኖች የዞን አስተዳደሮች የሚገኙ በጉባኤ ያልተሳተፉ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በጉባኤ በተሳተፉ አባላቱን ሙሉ በሙሉ መተካቱ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት  ፦

- አቶ በየነ መክሩ 
- ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት 
- ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፋይ
- ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃዲቕ 

ከጊዚያው አስተዳደሩ ካቢኔ በማንሳት በ
- ዶ/ር አብራሃም ተኸስተ
- አቶ አማኒኤል አሰፋ
- ዶ/ር ፍስሃ ሃብተፅዮን
- አቶ ተወልደ ገ/ፃድቃን
- ወ/ሮ ብርኽቲ ገ/መድህን
- አቶ ይትባረክ አምሃ 
- ዶ/ር ፀጋይ ብርሃነ መተካቱ ገልጿል።

- አቶ ርስቁ አለማው
- አቶ ሰለሙን መዓሾ
- አቶ ሺሻይ መረሳ 
- አቶ ሃፍቱ ኪሮስ  ከዞን ዋና አስተዳዳሪነት በማንሳት

- በአቶ ተኽላይ ገ/መድህን
- በአቶ ወልደኣብራሃ ገ/ፃዲቕ 
- በአቶ ሺሻይ ግርማይ
- በአቶ ፍስሃ ሃይላይ
- በአቶ ሃይላይ ኣረጋዊ 
- በዶ/ር አብራሃም ሓጎስ ተተክተዋል ብሏል።

በተጨማሪ 
- አቶ ረዳኢ ሓለፎም
- ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
- አቶ ነጋ አሰፋ 
- ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር ከኤጀንሲ እና የኮሚሽን የስራ ሃላፊነት ወርደዋል ያለው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት በእነ ማን እንደተተተኩ ያለው የለም።

ይህ ዘገባ አስከተጠናቀረበት ቀንና ሰዓት
ድረስ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ከሚመራ ህወሓት በኩል የተሰጠ መልስ የለም።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርዓት አልበኝነት ለመቆጣጠር " የጥፋት ሃይል " ሲል በስም  ባልገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ። " ህግና ስርዓት ለማስክበር የተጀመሩ ጥረቶች በማጠናክር የህዝቡ ስጋት ከግምት ያስገባ…
" በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል ፤ ... ችግር ሲፈጠር ዝም ብለን አንመለከትም " - የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች

በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የፀጥታ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅድ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች አስታውቋል።

የፀጥታ ሃይሎች ባወጡት አጭር የፅሁፍ መግለጫ ፥ " መስከረም 27 ጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመለከቱ ሁለት ተፃራሪ መግለጫዎች መውጣታቸው ተከትሎ በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል " ብለዋል።

" የትግራይን ሰላም እና ደህንነት እናረጋግጣለን " ያሉት የፀጥታ ኃይሎቹ " በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር አንፈቅድም ፤ ችግር  ሲፈጠርም በዝምታ አንመለከትም " ሲሉ አሳውቀዋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በማንሳት በሌሎች 14 የድርጅቱ አባላት እንዲተኩ መወሰኑን ከገለፀ በኋላ  ጊዚያዊ አስተዳደሩ " የመንግስት ግልበጣ ነው " ያለው ተግባር የሚያርም " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ሲል ገልጿል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" በህዝቡ ውስጥ የመረበሽ ስሜት ተፈጥሯል ፤ ... ችግር ሲፈጠር ዝም ብለን አንመለከትም " - የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች በተፃራሪ መግለጫዎች ምክንያት በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የፀጥታ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅድ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች አስታውቋል። የፀጥታ ሃይሎች ባወጡት አጭር የፅሁፍ መግለጫ ፥ " መስከረም 27 ጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመለከቱ ሁለት ተፃራሪ መግለጫዎች መውጣታቸው…
መቐለ ?

የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል።

የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ይትባረክ ኣምሃ በክብር እንዳሰናበተ ተነግሯል።

አዲሱ ' የመቐለ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል ' የተባሉት ዶ/ር ረዳኢ በርሀ በድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና በተነፈገው 14ኛ የህወሓት ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ  አባላት ዝርዝር ስማቸው እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት  ቡድን ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 13  የቢሮ ፣ የኮሚሽን ፣ የኤጀንሲ እንዲሁም የዞን አመራሮችና አስተዳዳሪዎች ከሃላፊነት በማንሳት ባካሄደው ጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች " ለመተካት ወሰኛለሁ " ማለቱ ይታወሳል።

የፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አመራር ደግሞ እንቅስቃሴው የመንግስት ግልበጣ ነው ብሎ መግለጫውን በማውገዝ መግለጫውን ባወጡ የህወሓት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ላይ " ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ " ማለቱ ይታወሳል። 

በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስለ አዲሱ የመቐለ ከተማ ተሿሚ እስካሁን ያለው ነገር የለም። 

ይህን መረጃ እስከተዘጋጀበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ምዕራባዊ ዞን ጨምሮ 6 የትግራይ ዞኖች በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተሾሙ አመራሮች የሚመሩ ሲሆን መቐለ ከተማ ዛሬ በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑ አዲስ ከንቲባ ተሹሞላታል ተብሏል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
#Tigray

" ጠቅላይ ሚንስትሩ ያስቀመጡት የመፍትሄ አቅጣጫ ተግባራዊ አልሆነም " - የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ግብረ ሃይል ተወካዮች

የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ግብረ ሃይል ተወካዮች ከሰሞኑን ውይይት ተቀምጠው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ " ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተከማች የብድር ወለድና ቅጣት መልክ እንዲይዝ ባለፈው ዓመት የሰየሙት የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን እስካሁን ያስቀመጠው ተጨባጭ ነገር የለም " ብለዋል።

" ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት የአመራር አቅጣጫ የገንዘብ ሚንስቴር ፣ የብሄራዊ ባንክና ልሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ሃላፊዎች ያካተተ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ቢቋቋምም እስከ አሁን የሚዳሰሰ የሚጨበጥ ለውጥ አልመጣም " ሲሉ ገልጸዋል።

ተወካዮቹ ፥ " ከ7 ወራት በፊት በ2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አዲስ አበባ ከጋበዟቸው የንግድ ማህበረሰብ ያካተተ ልኡክ ጋር ባካሄዱት ውይይት ማጠቃለያ በጦርነቱ ጊዜ የተከማቸው የብድር ወለድና ቅጣት ተሰልቶ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መፍትሄ እንዲሰጠው አቅጣጫ ቢያስቀምጡም እስከ አሁን ጠብ የሚል መፍትሄ አለመጣም ይህም በጣም አሳዝኖናል " ብለዋል።

አበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የሰጡት የብድር ወለድ ከነቅጣቱ እንዲመለስ የንግድ ማህበረሰቡ ማስጨነቅ እንደጀመሩ በዚሁ ውይይት ወቅት ተነግሯል።

ተግባሩ በጦርነት ምክንያት የደቀቀው የክልሉ ኢኮኖሚያዊ አቅም ይበልጥ ጉልበት የሚያሳጣ መሆኑ በመገንዘብ አገራዊ የፓሊሲና የፓለቲካ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አይደለምና " አስቸኳይ ትኩረት እና መፍትሄ " እንደሚያሻው አፅንኦት ተሰጥቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የፌደራል መንግስት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የሚታደግ የመፍትሄ እርምጃ እንዲያስቀመጥ ተጠይቋል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
#ውቕሮ

° " እሁድ ተድራ ሓሙስ በጭካኔ ተግድላለች " - የውቕሮ ከተማ ነዋሪች 

° " ገዳዩ ሙሽራ እጅ ሰጥቷል፤ የድርጊቱ መንስኤ እየተጣራ ነው " - የውቕሮ ከተማ ፓሊስ

ከመቐለ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ትንሽዋ እና ደማቅዋ የውቕሮ ከተማ ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም የሃዘን ማቅ ለብሳ ውላለች።

በሃያዎቹ ዕድሜ የምትገኘው ሊድያ በአዲስ አበባ ከተማ በኮንስትራክሽን ሰራዎች የተሰማራች ወጣት ምሁር ነበረች።

ድል ባለ ሰርግ ለማግባትም ወደ ውቕሮ ትግራይ ተጓዘች።

እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም በውቕሮ ከተማ በደማቅ የሰርግ ስነስርዓት " የወደፊት የትዳር አጋሬ " ያለቸውን ወጣት አገባች።

" የሙሽሪት ሊድያና ባለቤትዋ ሰርግ ደማቅ ነበር " ይላሉ የውቕሮ ከተማ ነዋሪዎች።

ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ እሮብ ሙሽሪትና ሙሽራ በውቕሮ ከተማ በሚገኘው ባለ ኮኮብ ሆቴል በጫጉላ ሽርሽር  ነበሩ።

ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ለአራት ቀናት የቆየው ደስታ ወደ ሃዘን ተለወጠ።

ሙሽሪት ሊድያ በባልዋ ተገደለች ፣ መገደልዋ ለፓሊስ የጠቆመው ገዳይ ሙሽራ ነው።

ፓሊስ ግድያ ወደ ተፈፀመበት ቦታ ድረስ በመሄድ ፤ ተጠራጣሪ ሙሽራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ የቀጠለ ሲሆን ፤ ሙሽራው ሙሽሪትን አንቆ ነው የገደላት ብሏል።

ፓሊስ ጭካኔ የተሞላው የግድያ ተግባሩ መነሻው ምን እንደሆነ በተሟላ መልኩ አጣርቶ ጉዳዩ ለሚመለከተው የህግ አካል ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ማለቱ ተሰምቷል።

ግድያው ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የውቕሮ ነዋሪዎችን ሀዘን ላይ ጥሏል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች " ደስታና ሀዘን ተቀላቀለብን ፤ ሙሽሪት እሁድ ተድራ ሓሙስ በጭካኔ ተግድላለች " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia            
#Tigray

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " - የትግራይ ክልል የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ 

የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፤ " የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት በማላላት የአርስ በርስ ግጭት እንዲከሰት የሚሰሩት ግለሰቦች እና አካላት አንታገስም " ብሏል።

እንዲህ ያለው ተግባር ላይ ስለተሰማሩት ግለሰቦችና አካላት በግልጽ ስም ጠቅሶ ያለው ነገር የለም።

ቢሮው ፥ " በአገር ውስጥ እና በውጭ በመሆን በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በመጠቀም በሬ ወለደ ውሸት በመንዛት በክልሉ የፀጥታ ሃይልና ህዝብ መካከል ያለው አንድነት እንዲላላ እየተሰራ እያየን በትእግስት ለማለፍ መርጠናል " ብሏል።

" ከአሁን በኋላ ህግ እንዲከበር በጥብቅ ይሰራል " ሲል አስታውቀዋል ።  

" በፀጥታ ሃይሉ ጉድለት አለ የሚል አካል ተጨባጭ አሳማኝ መረጃ በማቅረብ ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል " ያለው ቢሮው " ይሁን እንጂ ፓለቲካ አስታኮ የሚነዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ውሸት በግለሰብም ሆነ በየትኛውም አካል አያሰጠይቅም ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቀዋል። 

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " ሲልም ገልጿል።

ቢሮው ፤ " የፀጥታ ሃይል የማንም የፓለቲካ ቡድን መሳሪያ አይደለም " ሲልም አክሏል።

የፀጥታ ኃይሉ በክልሉ ባለው የፓለቲካ መከፋፈል መካከል ገብቶ የአንዱ ደጋፊ የሌላው ተቃዋሚ እንዲሆን ታልሞ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መሆኑን የገለጸው ቢሮው " ይህ አይሳካም ፍፁም ተቀባይነት የለውም፤ ይህንን ተላልፎ የሚገኝ ግለስብና አካል በህግ እንዲጠየቅ በማድረግ የህግ ልእልና እንዲከበርና የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር እንሰራለን " ብሏል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

" ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " - ተገልጋይ

በትግራይ ክልል ፣ መቐለ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ የሉም ፤ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር ይገኛል።

ተገልጋዮች ከከንቲባ ማግኘት ያለባቸው አገልግሎት ለማግኘት ቢመላለሱም የሚያስተናግዳቸው የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ጠዋት መቐለ አስተዳደር ፅህፈት ቅጥር ግቢ ድረስ ተጉዞ አጭር ምልከታ አደርጓል።

በአስተዳደሩ ዋና በር በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተገለግጋሎች ሲገቡ ሲወጡ ይታዩሉ ፤ ፍትሻ በሚካሄድበት ቦታ ከተለመደው በተለየ ብዛት ያላቸው የፀጥታ አካላት ይስተዋላሉ።

5ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የዋና ከንቲባ ፅህፈት ቢሮ  (ከህዳር 22/2017 ዓ.ም ) እንደታሸገ ሆኖ ግራና ቀኝ የፓሊስ ደንብ ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከከንቲባ የሚሰጥ አገልግሎት ለማግኘት ከአንድ ወር በላይ የተመላለሰ ተገልጋይ አግኝቶ አስተያየቱ ተቀብሏል።

ተልጋዩ ፀጋዛኣብ ርእሰደብሪ ይባላል የመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ነው።

ያለውን የመሬት ጉዳይ አስመልክቶ ከንቲባ አግኝቶ ለማነጋገር ቢመላለስም እስካሁን እንዳልተሳከለት ገልጿል።

" በሁለቱም በኩል ያሉ የህወሓት አመራሮች ማሰብ ተሰኗቸዋል ? ፤ ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " ሲል በምሬት ተናግሯል።

ካለፈው ወርሀ ነሃሴ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ወደ ሁለት ቡድን መሰንጠቃቸው ያወጁት የደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን በየፊናቸው በየቦታው አመራር በመመደብና በመገለጫዎች መወራረፍ ቀጥለውበታል።

ባለፈው ወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የቀድሞ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ ተክቶ በደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እጩ አቅራቢነት በከተማው ምክር ቤት ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ረዳአ በርሀ (ዶ/ር) በጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ወድያውኑ ተቀባይነት ማጣታቸው ተከትሎ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ብርሃነ ገ/የሱስ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተሹመዋል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሸሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤቱና በክፍለ ከተሞች አመራሮች በቅጥር ግቢው በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጨምሮ ሚድያዎች በተገኙበት አቀባበል ቢደረግላቸውም ከነጋታው ጀምሮ ይህ ዜና አስከተጠናቀረበት ሰዓት ተመልሰው ቢሮ አልገቡም።

በወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) እንዲሁም ቢሮ ላይ የሉም።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክር ቤቶች በመጠቀም ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ " በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት " በማለት መቐለ ጨምሮ በትግራይ ስድስት ዞኖች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች በመሾም ህዝቡን ግራ አጋብተውታል።

ይህንን መሰል ግራ የገባው የሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አካሄድ ማብቅያው መቼ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia