TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመውጫ ፈተና ውጤት እየታየ ይገኛል።

በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ረፋድ ጀምሮ እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ውጤቱ መታየት ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ ለረጅም ሰዓታት በመንግስት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ብቻ ውጤታቸውን ማየት የቻሉ ሲሆን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ደግሞ #ከምሽት አንስቶ ውጤታቸውን ማየት ጀምረዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ " ውጤት መመልከቻው ድረገፅ ላይ ገብተው username ሲያስገቡ የሚያገኙት ምላሽ የተቋማቸው " የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም " የሚል እንዲሁም የአንዳንዶቹ " ያስገቡት ስም የማይሰራ " መሆኑን የሚገልፅ ነው።

ውጤታቸውን የተመለከቱ በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ደግሞ 50 እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም " fail / ወድቀዋል " የሚል ምላሽ እያገኙ መሆኑን በመግላፅ ትምህርት ሚኒስቴር በሲስተሙ ላይ ያለውን ችግር #እንዲያስተካክል ጠይቀዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፤ የመውጫ ፈተና የተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ሲሆኑ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ በመውጫ ፈተና አመርቂ ውጤት ካልተመዘገበባቸው / እጅግ በርካታ ተማሪዎች ከወደቁባቸው የትምህርት ክፍሎች አንዱ የ " Accounting and Finance " ሲሆን በፈተናው ላይ  ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች የፈተናው ምዘና ድጋሚ እንዲፈተሽ ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የ " Information Technology " ተማሪዎችም መሰል አቤቱታ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የተሰጠው ፈተናው ከነበረው ዝግጅት ጋር የሚራራቅ እንዲሁም ደግሞ ከ ተሰጣቸው ' ብሉለሪንት ' ጋር የማይቀራረብ በመሆኑ ሚኒስቴሩ እንዲያይላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም የ ' መካኒካል ምህንድስና ' ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማቅረባቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ወይም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን #ቅሬታ የሚያስተናግዱበት መንገድ ካለ ጠይቆ የሚያሳውቅ ይሆናል።

#ማስታወሻ ፦ የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username በማስገባት ነው።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia