TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ባህር ዳር⬆️

ከውጭ ሀገር ሆነው አርበኞች ግንቦት-7ን ይመሩ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡

አመራሮቹ ባሕር ዳር ሲገቡም የድርጅቱ የሀገር ውስጥ አመራሮች እና የክልሉ መንግሥት ተወካይ ተቀብለዋቸዋል፡፡

ከፍተኛ አመራሮቹ ወደ ባሕር ዳር የመጡበትን ዓላማ አስመልክቶም መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የአርበኞች ግንቦት-7 ሊቀ-መንበር ፕ.ር ብርሃኑ ነጋ ‹‹ሕዝቡ ለነጻነት ለከፈለው #መሰዋዕትነት ምሥጋና ልናቀርብ ነው›› ብለዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በበኩቸው ‹‹በባሕር ዳር በሚኖረን ቆይታ ስለድርጅታችን ቀጣይ አቅጣጫዎች እና ሥራዎች ለሕዝብ #የማሳወቅ ሥራ እንሠራለን›› ብለዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት-7 አመራሮች ነገ ቅዳሜ ረፋድ 2፡00 ጀምሮ በባሕር ዳር ዓለም-አቀፍ ስታዲዮም ንግግር ያደርጋሉ፤ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከቀኑ 8፡00 አንስቶ በአማራ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነገው እለት ሊካሔድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የድምጻዊ #ቴውድሮስ_ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት በአዲስ አበባ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት ተራዝሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ዘረኝነትን እንጠላለን!
#ጥላቻን እንጠላለን!
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እንወዳችኋለን!
.
.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ነገ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የኦነግ የድጋፍ ላይ #ችግር እንፈጥራለን በሚሉ ወጣቶች ላይ #እርምጃ እንደሚወስዱ አስታወቁ፡፡ ከዓለማው ዉጭ በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ፖሊስ #እርምጃ ይወስዳል ብለዋል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሰላ⬆️ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በአሰላ ከተማ ው ጥረት እንደነበረ የቻናላችን አባላት ገልፀዋል። ዝርዝር ጉዳዩን በቀጣይ የምመጣበት ይሆናል።

ማሳሰቢያ📌

ወጣቶች ከስሜታዊነት ውጡ አሁን ያለውን ለውጥ የማይፈልጉ አካላት እንዱጠቀሙባችሁ አትፍቀዱ። ሰከን ብላችሁ ተነጋገሩ። ካለ ኢትዮጵያ ምንም የለንም። ይህች ሀገር ከሌለች ስለምንም ነገር ማውራት አንችልም። እናት እና አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቱን መምከር እና በስሜት ከመነዳት ሊቆጥቡት ይገባል።

ፎቶ፦ የቻናላችን ቤተሰብ አባል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና #ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል፡፡

በተለያዩ አውቶብሶች ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን፣ የፒያሳ አካባቢ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያን #ለመዝረፍ እንቅስቃሴ መደረጉንና ፖሊሶችም በጥይት መበተናቸውን፣ ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

የፒያሳ ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተረኛ መኰንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 700 የሚሆኑ ወጣቶች ጭነው የመጡት መኪኖች በአካባቢው ወጣቶችና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ሪፖርተርም ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ተገኝቶ፣ በአማርኛ መግባባት የማይችሉ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች የሕክምና ዕርዳታ ሲጠብቁ ለማስተዋል ችሏል፡፡

በዳግማዊ በአፄ ምንልክ አደባባይ ሐውልትና አካባቢም በመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የነበረ ሲሆን፣ የፌዴራል አድማ በታኝ ፖሊስም ወደ አመሻሹ አካባቢ #ዓርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ወደ ጎዳና የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶችን #ሲበትን ተስተውሏል፡፡

በፒያሳ የሚገኙ ባንኮችና የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ ከመዘጋታቸውም በተጨማሪ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትም በመቋረጡ ብዙዎች ሲቸገሩ ታይተዋል፡፡

©ሪፓርተር
@tikvahethiopia @tsegabwolde
መግለጫ⬆️የሰማያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የጋራ መግለጫ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፦

📌ፈተና ያልተፈተኑ የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ- መስከረም 11 እና 12
ፈተና የሚጀመረው - መስከረም 14
የፈተና የሚጠናቀቀው - መስከረም 26
የምዝገባ ቀን - ጥቅምት 1 እና 2

📌5ኛ አመት ተማሪዎች ምዝገባ ቀን - መስከረም 23 እና 24

📌የ3ኛ ዐመት የሆልስቲክ ተፈታኝ ተማሪዎች፦

ጥቅምት 9 እና 10 የመግቢያ ቀን
ጥቅምት 12-24 የፋይናል ፈተና
ህዳር 5-10 የሆልስቲክ ፈተና
ከህዳር 11 በኋላ ባሉት ቀና ምዝገባ

©የተማሪዎች ህብረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወጣቶች⬇️

"ሰላም ፀግሽ! ትናንት ቀን ላይ 6 ሰዓት ገደማ ወደ 18 ማዞሪያ ዘመድ ጥየቃ ሄጄ ነበር፡፡ የሆነው ነገር አሳዝኖኛል! #እናቶች ህፃን ልጆቻቸውን ትተው እንደወጡ መግቢያ አተው፡፡ እኔም ያለ እቅዴ አደርኩ እኔ የነበርኩበት ቤት 3 ቤተሰብ አደሯል፡፡ 2 አራስ ልጅ ትተው ለጉዳይ ጠዋት የወጡ ናቸው፡፡ ሚያውቁት ሰው የሌላቸውን አስብ፡፡ እባካችሁ ወጣቶች ጊዜያዊ #ስሜት አይምራን! ሊከተል የሚችለውንም ሰከን ብለን እናስብ፡፡ ሀገር ወዳድ ዜጋ ለእናቶቹ፣ ለእህቶቹ፣ በአጠቃላይ ለወገኖቹ ሰላምና ነፃነት ቅድሚያ የሚሰጥ ነው፡፡ "ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ፡፡" መልካም ምሽት፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናትን ከላይ ባለው ማስታወቂያ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

©J
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች📌ነገ በመስቀል አደባባይ ለኦነግ አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በአዲስ አበባ #ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ።

በዚህም መሰረት፦

▪️ከቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣

▪️በኡራኤል፣ ባምቢስ አብዮት አደባባይ፣ ከአራት ኪሎ፣ ብሄራዊ ቤተመንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ከካዛንቺስ፣ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ፍል ውሃ፣

▪️ከንግድ ማተሚያ ቤት ኦርማ ጋራዥ፣ ፍልውሃ፣ ሃራምቤ ሆቴል፣ ከቴድሮስ አደባባይ፣ ኢሞግሬሽን፣ ፣ ሀራምቤ ሆቴል፣ ስታዲየም፣

▪️ከጎማ ቁጠባ፣ ብሄራዊ ትያትር፣ ስታዲየም፣ ሜክሲኮ፣ ከሰንጋ ተራ፣ በድሉ ህንፃ ስታዲየም፣

▪️ከሰንጋ ተራ፣ በለገሃር፣ ስታዲየም፣
በቂርቆስ አዲሱ መንገድ፣ በለገሃር ስታዲየም፣

በሀራምቤ ሆቴል፣ ጋንዲ ሆስፒታል፣ ወደ መስቀል አደባባይ፣

▪️ከአጎና ሲኒማ፣ በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መሰቀል አደባባይ ያሉ መንገዶች #ለጊዜው የተዘጉ መሆናቸውን አስታውቆአል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌

ከአዲስ አበባ ግጭቱ ጀርባ፦

በከተማዋ የሚታየዉ #የፀጥታ ችግር በቀን ጅቦች #ስፖንሰርነት ቅጥረኞች ያነሱት መሆኑ ታዉቋል። አለማዉ ህዝቡን በማባላት ወደ #ሥልጣን መመለስ ነዉ። ቅጥረኞች ሰልጥነዉ የተሰማሩ ከመሆናቸዉም በላይ በሞተር ሳይክል፣ በቤት መኪና እና በፕካፕ ገንዘብ እየተበተነላቸዉ መሆኑን የአይን እማኞች ገልፇል። ረብሻኞቹ ከሌላ ቦታ ተመልምሎ የመጡ ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣት የለበትም። በብዙ ቦታዎች ደግሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ግጭት እንዳይፈጠር ሲከላከል እንደነበር ታዉቋል። የግጭት ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ የፀረ-ለዉጥ ኃይሉ መሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ ተረጋግጧል! ባንዲራ #ሽፋን እንጂ መነሻ አይደለም። ሁለቱንም ባንዲራ የማይወዱ ሰዎች አንዱን ደግፎ ሌላዉን የተቃወሙ ያስመስላል።

ማስታወሻ፦

1. የረብሻኞቹ ፎቶ እና ቪዲዮ ይቀረፅ
2. የመኪኖቹ ታርጋ ይመዝገብ
3. ማስረጃ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ አድርሱ።

Oduu Ammee📌

Jeequmsi #Finfinnee waraabeyyii guyyaatiin kan qindeeffame ta'uu barameera. Jeeqxoti bakka biraatii filatamanii leenjifamuun bobbaafaman. Makiinaan maallaqa hiraa akka jiranis barameera.

Bakka jeequmsi jirutti suuraa fi viidiyoo jeeqxotaa waraabuu fi taargaa konkolaataa qabuu hin dagatinaa!

ምንጭ፦ አቶ ታዬ ደንደአ(የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia