TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️በነገው እለት አዲስ አበባ የሚገባውን የኦነግ አመራር ለመቀበል ከምሽት ጀምሮ አብዮት አደባባይ የሚገኙት #ቄሮዎች ምግብና መጠጥ እንዳላገኙ መገለጹን ተከትሎ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከላይ በምስሉ በምትመለከቱት መልኩ ዳቦና ውኃ ይዘው እየሄዱ ይገኛሉ። #ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው፤ ሌሎችም የከተማችን ወጣቶች አብዮት ለሚገኙት ወገኖቻችን እንድረስላቸው።

©ኤርሚያስ ቶኩማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን⬆️ሁሉም አዲስ አበባ ወጣት እና ሌላውም ነዋሪ ለመልካም ስራ እንዲነሳ ጥሪ ቀርብሏል። መስቀል አደባባይ የሚገኙ ወንድሞች እና እህቶቹን እንዲደግፍ እና ለፍቅር እንዲቆምም ጥሪ ቀርቧል።

ፍቅር ያሸንፋል!
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለፍቅር ተነሱ! ለአንድነት ተነሱ! በፈጣሪ ዘንድ ሁላችንም አንድ የሰው ልጆች ነን! ከሀገር፣ ከባንዲራ፣ ከብሄር፣ ከክልል፣ ከዘር ከሁሉም ነገር በፊት ሰውነት ይቀድማል!

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ-አሁን⬆️

እንደ #አቅማችን ያዘጋጀነውን እህል ውሀ መስቀል አደባባይ ምሽቱን ለሚያሳልፉ ቄሮዎች አድርሰን ከአስተባባሪዎቹ ጋር የማስታወሻ ፎቶ ተነስተናል።

ከኛ ቀደም ብለው ይሁን ከእኛም በኋላ ከየአካባቢው የመጡ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የምግብና የውሀ ችግር እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ #ትብብር እያደረጉ ነው።

አስተባባሪዎቹ እንዲህ አሉኝ "የውሀም የምግብም መስተንግዶ የአዲስ አበባ ልጆች ስላደረጉልን ተደስተናል። #ገለቶማ"
.
.
በሠላምና በፍቅር የነገው ዝግጅት እንዲጠናቀቅ ምኞቴ ነው። ቸር አምላክ ህዝብህን አደራ።

©ያሬድ ሹመቴ(የፊልም ዳይሬክተር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ-አሁን⬆️

የአዲስ አበባ ነዋሪ #ምሽት ሳይበግረው በነቂስ ወቶ ወገኑን በመደገፍና እራት በማብላት ላይ ይገኛል። ለወገን ደራሽ ወገን ነው። የፖለቲካዊ አስተሳሰብ ልዩነት #ከሰብአዊነት አይበልጥም። ሰው መሆን የሁሉ ነገር መነሻ ነው። ኢትዮጵያዊያን
እንዲህ ስንሆን ያምርብናል። galatoomaa!!!

©Dechasa Angecha Tadesse
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር⬆️የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በባህር ዳር ለሚገኙ የንቅናቄው ደጋፊዎች ዛሬ ንግግር ያደርጋሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia