TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrHagosGodefay

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 4 ሰዎች የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

- የረዳቶቹ ዕድሜ 28፣ 25 እና 24 ነው ፤ ሹፌሩ ደግሞ 33 ዓመቱ ነው።

- ታማሚዎቹ ምንም ምልክት የላቸውም።

- ወደ ክልሉ የሚገቡ ሰዎች ላይ ጠንካራ ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ ነው ግለሰቦቹ የተገኙት።

- እኚህ አራት (4) ሰዎች ወደ ትግራይ የገቡት ወደ ሚያዚያ 23 አካባቢ ነው።

- በአሁን ሰዓት የጤናቸው ሁኔታ ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ነው።

- ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ወደለይቶ ማቆያ የማስገባቱ ስራ #ተጠናክሮ ቀጥሏል።

- ዛሬ በክልሉ ጤና ቢሮ #ዘግየት ብሎ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ ከሰጡ በኃላ የተረጋገጠ በመሆኑ ነው (ወደ 7:00 አካባቢ ነው ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠው) ፤ ከ8:00 በኃላ በይፋ መግለጫ ተሰጥቷል።

#TIKVAHETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

የአራቱ ወጣቶች ኬዝ የማንቂያ ደውል ይሁነን!

ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ለኢትዮጵያውያን መልዕክት አላቸው ፦

"ሁሉም ሰው ሊነቃ ይገባል ፤ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችም ቫይረሱን (COVID-19) ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ መረዳት ያስፈልጋል። ወጣቶች ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሊይዛቸው እንደሚችል በማወቅ እራሳቸውን ሊጠብቁ ፣ የጤና ባለሞያዎችን ምክር ሊያዳምጡ ይገባቸዋል።"

ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ይህ መልዕክት ያስተላለፉት በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ ስለተያዙት 4 ወጣቶች አጠር ያለ ማብራሪያ በሰጡን ወቅት ነው።

በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ወጣቶች ምንም አይነት 'ምልክት የሌላቸው' ሲሆኑ በክልሉ በተሰራው ጠንካራ የክትትል ስራ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይ በዛሬው ሪፖርት ላይ የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ሁለቱም (2) #ከጅቡቲ ተመላሽ ሹፌሮች ናቸው።

- እድሜያቸው 30 እና 38 ዓመት ነው።

- በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው።

- ምንም ምልክት አይታይባቸውም።

- ከጅቡቲ ወደ ትግራይ ክልል የገቡት ሚያዚያ 29 ነው።

ዛሬ አመሻሹን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ 10:00 ነው ውጤቱ #የደረሰው ፤ በ24 ሰዓቱ የፌደራል ጤና ሚስቴር መግለጫ ያልቀረበው በዚህ ምክንያት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrHagosGodefay የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡን አጭር መረጃ ፦ - ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 4 ሰዎች የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። - የረዳቶቹ ዕድሜ 28፣ 25 እና 24 ነው ፤ ሹፌሩ ደግሞ 33 ዓመቱ ነው። - ታማሚዎቹ ምንም ምልክት የላቸውም። - ወደ ክልሉ የሚገቡ ሰዎች ላይ ጠንካራ ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ ነው ግለሰቦቹ…
#DrHagosGodefay

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ የሰጡን ተጨማሪ መረጃ ፦

- ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 መያዙ ከተረጋገጠው ከጅቡቲ ተመላሽ ሹፌር (የ33 ዓመቱ) ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው 62 ሰዎች ተለይተው ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። እስካሁን ድረስ ከመካከላቸው ምልክት ያሳየ ሰው የለም።

- ከጅቡቲ ወደ ትግራይ ክልል የሚመጣ እያንዳንዱ ሹፌር ኳራንታይ እየተደረገ ምርመራ በመደረግ ላይ ይገኛል። በዚህ ጠንካራና የተቀናጀ ስራ ነው በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ማግኘት እየተቻለ የሚገኘው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል (ማይ ካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ) ኮቪድ-19 ስለተገኘባቸው ግለሰቦች የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የ20፣ 26 እና 55 ዓመት እድሜ ያላቸው ናቸው።

- ሶስቱም (3) የመጡት #ከሱዳን ነው።

- አንደኛው ታማሚ ሚያዚያ 29፣ ሁለተኛው ታማሚ ሚያዚያ 30 ፣ ሶስተኛው ደግሞ በግንቦት 1/2012 ዓ/ም ነው ወደ ትግራይ የገቡት።

- ሶስቱም ግለሰቦች ምንም አይነት ምልክት የለባቸውም።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሶስቱ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ነግረውናል።

ሁለቱ (2) ከማይካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ ፣ አንድ (1) ሰው ከመቐለ ላይቶ ማቆያ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አሳውቀውናል።

ዛሬ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሶስቱም (3) ሰዎች ምንም አይነት ምልክት #የለባቸውም

ዶክተር ሓጎስ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አሁንም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ፤ ዜጎችም በመንግስት የሚስጡ መመሪያዎችንና በጤና ባለሞያዎች የሚተላለፉ ምክሮችን ሳይዘናጉ እንዲተገብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia